Recently Posted News
  2ኛው የተራራ ላይ ሩጫ በስኬት ተጠናቀቀ
ነሐሴ 06, 2007

ፈለቀ ደምሴ

ለሁለተኛ ጊዜ ትሪያ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው የተራራ ላይ ሩጫ ውድድር በአብያተ ሻላ ሃይቆች ፓርክ ላይ ተካሂዶ ባማረ እና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በቦርድ ሰብሳቢው አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም እና በዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃለአብ ጌታነህ መስራችነት የተጀመረው ይህ የተራራ ላይ ሩጫ በርካታ ዓላማዎችን ይዞ የተነሳ ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት ይህ ዝግጅት ልዩ ልዩ ሀገራዊ ጠቀሜታዎችን አስገኝቷል፡፡ በዋናነት በሰዎች እና የቤት እንስሳት መብዛት ምክንያት እየተመናመኑ ያሉትን የአብያተ እና ሻላ ሃይቆች ብሔራዊ ፓርክ የዱር እንስሳት ለመታደግ የሚመለከታቸው አካላት እንዲያስቡበት እና ህብረተሰቡን እንዲያስተምሩበት እድል ፈጥሯል፡፡ ቱሪስቶች እና የውጪ ጋዜጠኞች ወደ አገራችን እንዲመለከቱም አስችሏል፡፡ በአሜሪካ እና አውሮፓ ተወዳጅ የሆነው ይህ የተራራ ላይ ሩጫ ከመዝናኛ እና ስፖርታዊ ጥቅሙ በተጨማሪ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃን ማጠናከር እና በጉዳዩ ግንዛቤ መፍጠር ዓላማ ያለው በመሆኑ በዚህ ዝግጅት የተካፈሉና ስፖንሰር ያደረጉ አካላት ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ከውድድሩ የመመዝገቢያ ክፍያ የሚገኘው ገቢ 20% ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥቅም የሚውል ሲሆን በውድድሩ ላይ ለአሸናፊዎች የሚሰጡት የሜዳልያ እና የዋንጫ ሽልማቶች የአካባቢው ወጣቶች የተሰራ መሆኑ ወጣቶቹን የሚያበረታታ ነበር፡፡


ባለፈው ዓመት በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር አሸናፊ የነበሩ አትሌቶች ስፔን ሀገር በሚደረግ ተመሳሳይ ውድድር እንዲካፈሉ ተደርጓል፡፡ የዘንድሮ አሸናፊዎች ደቡብ አፍሪካ ላይ በሚደረግ ተመሳሳይ ውድድር እንደሚካፈሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ በውድድሩ ከዘጠኝ ሀገራት የመጡ ከ110 በላይ ተወዳዳሪዎች ተካፍለዋል፡፡ ከእነዚህ ተወዳዳሪዎች ውስጥም በአምናው ውድድር የተሳተፉ ይገኙበታል፡፡

እሁድ ነሐሴ 3 ቀን ከጠዋቱ 12፡30 የተጀመረው ይህ ውድድር በአራት ምድብ የተከፈለ ነበር፡፡ እነዚህም የ12፣ የ21 እና የ42 ኪሎሜትር የተራራ ላይ ውድድር እና  የሕፃናት ውድድር ናቸው፡፡ ውድድሩ በጣም አዝናኝ እና ደማቅ ነበረ ሲሆን በኢፌዲሪ አየር ኃይል  ትብብር ሄሊኮብተር ቅኝት እና የቪዲዮ ቀረፃ ተደርጎለታል፡፡ የተራራ ላይ ሩጫ ከሌሎች የጎዳና ላይ ሩጫዎች እና ከማራቶን የሚለይበት በርካታ ህጎች አሉት፡፡
ይህ ውድድር ከፍተኛ አቅምና ፍላጎት የሚጠይቅና ከባድ በመሆኑ አዘጋጆች የትጥቅ፣ የመጓጓዣ፣ የሆቴል መስተንግዶ፣ የጥበቃ፣ የህምምናና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን አስቀድመው ያሟሉ በመሆኑ በውድድሩ ወቅት ቆሻሻ መጣል የማይፈቀድ ሲሆን ከመነሻው ጀምሮ በተወሰኑ ርቀቶች ላይ የተቀመጡ የቆሻሻ መጣያ እቃዎች አሉት፡፡ እርዳታ የሚያሻውን ተወዳዳሪ ትቶ መሄድም የተከለከለ ነው፡፡ በተወሰኑ ርቀቶች ላይ ድጋፍ ሰጪዎች እና የህክምና ባለሙያዎች ስላሉ ምንም አይነት የተለየ የድጋፍ ከሌላ ወገን መጠየቅ የተከለከለ ነው፡፡ በሌሎች ሰዎች ድጋፍ ውድድሩን በብስክሌት፣ በሞተር፣ በፈረስ እና በተለያዩ መጓጓዣዎች መጠቀም አይፈቀድም፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ህጎች የጣሰ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
 


በውድድሮቹ በተለያዩ ምድቦች በሁለቱ ፆታዎች የተመዘገቡት ውጤቶችም የሚከተሉት ናቸው፡ -

1. የ42 ኪሎ ሜትር ወንዶች
1. ጌቱ ንጉሱ 2:38:05
2. ፀጋዬ Dagusge 2:38:47.65
3 በለጠ መኮንን 2:41:39.55

2. የ42 ኪሎ ሜትር ሴቶች
1. ቀነኒ አሰፋ 3:18:12.66
2. ራሄል ወርቁ 3:25:05.60
3. ህይወት ሽታዬ 3:31:22.36

3. የ21 ኪሎ ሜትር ወንዶች
1. ተስፋዬ ተገኝ 1:00:09.97
2. ገነሞ አቡ 1:00:11.14
3. አዲሱ ኩራባቸው 1:00:11.37

4. የ21 ኪሎሜትር ሴቶች
1. ረቂቅ በቀለ 1:00:11.27
2. ገዳምነሽ መኮንን 1:43:09.11
3. እመቤት ታደሰ 1:43:18.85

5. የ12 ኪሎ ሜትር ወንዶች የጎዳና ላይ ሩጫ 12k Men mass runners
1. ዳዊት መብራቱ 1:06:28.94
2. በረከት ወ/ገብርኤል 1:44:14.21
3. አበባው ደጀኔ 1:46:50.72

6. የ12 ኪሎ ሜትር የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ 12 Female mass runners
1. አዲ ገመዳ 1:50:57.72
2. ሶፊያ Liesker 2:07:53.30
3. መቅደስ ዝናቡ 2:14:16.88


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
aqjeftmt [825 days ago.]
 1

Jhon [746 days ago.]
 It,s verey nice.

Brhanu Gebru [682 days ago.]
 ኢትዮጵያ ሃገራችን በሩጫ ትልቅ ተስፋ ኣሏት:: ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ጥሩ ውጤት ኢያስመዘገቡ ያሉ ወጣቶች ክብርና ምስና ይገባቸዋል!!!! እግዚኣብሄር ከነሱም ጋር ይሁን!!!!

xkplqkah [658 days ago.]
 1

ewedmyhf [658 days ago.]
 1

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!