Recently Posted News
  ፈረሰኞቹ ዛሬ ማለዳ ወደ ሉሙምባሼ አቀኑ
መጋቢት 08, 2008

በይርጋ አበበ

ለአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ፈረሰኞቹ 18 ተጫዋቾችን እና ሌሎች አምስት የአሰልጣኞች እንዲሁም የህክምና ታፎችን በድምሩ 23 ይዘው ዛሬ ማለዳ ወደ ሉሙምባሼ አቀኑ። ቡድኑ ወደ ኮንጎ ሲያቀና ተከላካዩ ዘካሪያስ ቱጂ እና አጥቂው ሳላዲን ሰይድ አልተካተቱም።

ባህ ዳር ላይ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አካሂደ ሁለት እኩል የተለያዩት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቲፒ ማዜምቤ የመልስ ጨዋታቸውን የፊታችን እሁድ የሚያካሂዱ ይሆናል። በመልሱ ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ወይም የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን ወደ ምድብ ድልድሉ በቀጥታ የሚያመራ ይሆናል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ሉሙምባሼ ላይ ማሸነፍ ወይም ሶስት እኩል መለያየት ይጠበቅበታል።

ወደ ሉሙምባሼ ያቀናው የፈረሰኞቹ ጦር ሙሉ ስም ዝርዝር

ሮበርት ኦዶንካራ እና ዘሪሁን ታደለ የግቡን ክልል የሚጠብቁ

የተከላካይ መስመሩ ተሰላፊዎች አስቻለው ታመነ፣ አይዛክ ኢሴንዴ፣ ደጉ ደበበ፣ መሃሪ መና፣ አበባው ቡታቆ ፣ አሉላ ግርማ እና ቢያድግልኝ ኤሊያስ ናቸው።

ምንያህል ተሾመ፣ ተስፋዬ አለባቸው፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ በሀይሉ አሰፋ፣ ምንተስኖት አዳነ ና አቡበከር ሳኒ የአማካይ መስመሩን ይመሩታል።

ሳላዲን ሰይድን በፈቃድ ምክንያት እና ብሪያን አሙኒን በጉዳት ወደ ኮንጎ ይዞ ያልተጓዘው የፈረሰኞቹ ጦር የፊት አውራሪነቱን ሚና ይወጡልኛል ብሎ ተስፋ የጣለባቸው ሶስት ተጫዋቾች ሲሆኑ እነሱም ምክትል አምበሉ አዳነ ግርማ፣ በቅርቡ ፊርማውን ያኖረው ጉድዊን ቺካ እና ራምኬል ሎክ ናቸው።

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Mamush [706 days ago.]
 Goooooooood luck ou belive club ethiopian foot ball ambassador St.George fc !!!

መላኩ [706 days ago.]
 መልካም እድል ለሃገራችን ጀግናው ክለብ መኩሪያችን ማጌጫችን ለሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ

Shimamu [705 days ago.]
 ቡና ከጊዮርጊስ ብዙ ነገሮች መማር አለበት ጠንክሮ መስራት ሁልጊዜ ማልቀሱን አቁሞ የውስጥ ችግሮቹን መፈተሽ ይኖርበታል በአሁኑ ሰዓት ቡና የጊዮርጊስ ሳይሆን የ ሃድያ ሆሳህና ተፎካካሪ ነው:: በጣም ያሳፍራል ይሄን ያህል ደጋፊ የያዝ ቡድን ላለመውረድ ሲጫወት :: ቅዱስ ጊዮርጊስ በእውነቱ ሊከበር የሚገባው ክለብ ነው የአፍሪካ ሻምፒዮኑን ቲፒ ማዜንቤን ያንቀጠቀጠ ያስደነገጠ ወኔያም ቡድን ነው :: የሃገራችን ክለቦችም ሆኑ ብሔራዊ ቡድናችን ጠንክረው ከሰሩ የማንም ክለብ ወይም ብሔራዊ ብድን የደረሰበት ደረጃ የማንደርስበት ምንም ምክንያት አይኖርም ::

Gezegeta [703 days ago.]
  የፈረሰኞቹ እና የቲፒ ማዚምቤ ጨዋታ በዚህ መልኩ ቢጠናቀቅም ውጤቱ በደርሶ መልስ በነበረው እንቅስቃሴ የአምናው የአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ ሻምፒዮን አሸናፊ እና የአለም ክለቦች ተካፋይ የሆነው ቲፒ ማዚምቤ በሜዳ ላይ ብቃቱ ብቻ ሳይሆን በእድለኝነት ጭምር ተጠቃሚ መሆኑ የማይካድ ነው፡፡ Always St.George fc Ethiopian Foot Ball Ambassador ! VVVVVVVVVVVVV Proud of Ethiopia !!!

Daniman [703 days ago.]
 ጨዋታው አለቀ ቲፒ ማዜንቤ 1-0 ቅዱስ ጊዮርጊስ አጠቃላይ ውጤት (3-2) ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ባንችልም የአፍሪካ ቻምዮኑን ቲፒ ማዜንቤን መፈተናችን ግን ‪‎ሊያኮራን‬ ይገባል ። ተሸንፎም የሚያኮራ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንግዜም ጊዮርጊስ !!!

felexsami [703 days ago.]
 ጨዋታው በቲፒ ማዜንቤ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል። በ89ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረው በድምር ውጤት 3ለ2 በማሸነፍ ወደ ተከታዩ ዙር አልፈዋል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የወቅቱን ሻምፒዮን በሚገባ ፈትኗል በዚህም ኩራት ይሰማኛል። ብራቮ ሳንጅዬ !!!

Mali [703 days ago.]
  ቅዱስ ጊዮርጊስ የወቅቱን ሻምፒዮን በሚገባ ፈትኗል በዚህም ኩራት ይሰማኛል Forever St.George fc ብራቮ ሳንጅዬ !!!

Yoni-Sanjawe [703 days ago.]
 ልጆቻችን ኮርተንባችኋል በሰላም ተመለሱልን ከዚህ ጨዋታ ትልቅ ትምህርት ነው ያገኛችሁት እውነት እላችኋለሁ ግምቶችን ሁሉ ፉርሽ አድርጋችኋል፡፡ ምንግዜም ጊዮርጊስ !!!

Mali [701 days ago.]
  @ Sirak and EJ :- ምድረ ወረኛ ምቀኛ ሁላ የአፍሪካ ቻምዮኑን ቲፒ ማዜንቤን መፈተናችን ጥንካሬያችንን እንደሚያሳይ ለማንም ግልፅ ነው :: አንድ የረሳችሁትን ነገር ላስታውሳችሁ አሁን በቅርብ ለ Mo Ibrahim Foundation ከቲፒ ማዜንቤ BBBB ብድን ጋር አዲስ አበባ ላይ ተጫውታችሁ 3 ለ 1 ተገልባችሁ ሃገራችንን ማሰደባችሁን የረሳችሁት መሰለኝ :: ገና ምን አይታችሁ የኛ ክለብ አላማ ልክ እንደ ቲፒ ማዜንቤ የአፍሪካ ሻምፒዮን መሆን እንጂ እንደ እናንተ የሃገር ውስጥ ዋንጫ በልተን በክፍት መኪና ላይ ተንጠልጥለን ልክ የአለም ዋንጫን እንዳሸነፈ ቲም ሃሃሃሃሃሃ ዘንድሮማ መውረዳችሁ የማይቀር ነው 2009 ላይ ጃል ሜዳ ነው የምትጫወቱት ሃሃሃሃሃሃ

yigermal wudu [672 days ago.]
 የሰላዲን ችግር ምንድን ነው?

zebust.george [617 days ago.]
 ሁግዜም st.george

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!