Recently Posted News
  ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ለአባይ ዋንጫ ይጫወታሉ
መጋቢት 16, 2008

በይርጋ አበበ

በአምስት ዓመታት ጊዜ ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ ቃል ተገብቶለት የነበረውና በአሁኑ ሰዓት የግንባታው 43 በመቶ የተጠናቀቀው የአባይ ግድብ አምስተኛ ዓመት በዓል የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በእግር ኳሳዊ ክንውኖች ይከበራል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከግድቡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ድቻ እንዲጫወቱ መርሃ ግብር መያዙን የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ።

ግድቡ በ2003 ዓ.ም ግንባታው ተጀምሮ አንደኛ ዓመቱን በ2004 ዓ.ም ሲያከብር በተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ተሳታፊ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር። ወላይታ ድቻ በበኩሉ ባለፈው ዓመት ከኤሌክትሪክ ጋር ተጫውቶ በባዬ ገዛኸኝ ጎል አሸናፊ መሆን ችሎ ነበር። በዚህም መሰረት የእሁዱ ጨዋታ የሁለት አሸናፊዎች ጨዋታ ይሆናል ማለት ነው።

ሁለቱ ክለቦች ጨዋታውን እንዲያካሂዱ የተመረጡት በርካታ ደጋፊ ስላላቸው መሆኑ ተገልጿል። ጨዋታው ከቀኑ አስር ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል ሲል ፌዴሬሽኑ የላከልን መረጃ ያመለክታል። የመግቢያ ዋጋው ይፋ አልተደረገም።

 

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!