Recently Posted News
  ከሽንፈትም በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈት
መጋቢት 17, 2008

ክፍል አንድ 
በይርጋ አበበ

የአልጄሪዋ ብሊዳ ከተማ ሙስጦፋ ቻኪር ስታዲየም የአልጄሪያን እና ኢትዮጵያን ጨዋታ እያስተናገደ ነው። አልጄሪያዎች በእንግዳው ቡድን ላይ ፍጹም የበላይነት ወስደው ተደጋጋሚ የጎል ሙከራ እና ጫና መፍጠር ጀመሩ። ገና ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ይወረወሩ የነበሩ የአልጄሪያ ሚሳኤሎች “እንኳንስ ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ” የሚባለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይና ግብ ጠባቂ ክፍል በአልጄሪያ አጥቂዎች የሚሰነዘርበትን ጥቃት መቋቋም የቻለው ለ30 ደቂቃዎች ብቻ ነበር። ከ30ኛው ደቂቃ ጀምሮ ግን በቀሪዎቹ 60 ደቂቃዎች የጎል ናዳ ሲወርድበት አመሸ። ለመሆኑ ለሽንፈቱ ኃላፊነት መውሰድ ያለበት ማን ነው? ሽንፈቱ በዚህን ያህል የጎል ልዩነት እንዴት ሊሰፋ ቻለ? እና የቡድኑ የእለቱ ብቃት በተለይም በአንዳንድ ተጫዋቾች አቋም ምን ይመስል ነበር? የሚሉትን ጥያቄዎች ከዚህ በታች አስተያየት ከሰጡ የስፖርት ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ስፖርት ተመልካቾች እና ከጽሁፉ አዘጋጅ ሀሳብ ጋር በማገናኘት አቅርበነዋል።

የቡድኑ የእለቱ ብቃት በተለይም በአንዳንድ ተጫዋቾች አቋም ምን ይመስል ነበር?

አሰልጣኘ ዮሃንስ ሳህሌ ብሔራዊ ቡድኑን ማሰልጠን ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ መጫወት ለእነሱ ብቻ የተፈቀደላቸው እስኪመስላቸው ወይም አገሪቱ ውስጥ ከእነሱ ውጭ ሌላ ተጫዋች የለም እንዴ እስኪሳይብል ድረስ ተደጋጋሚ ፊቶችን ማየት ተለምዷል። አንድ ቡድን ለረጅም ጊዜ አብሮ በመሰባሰብ ልምምድ መስራት እና መጫወት ችግር የለውም እንዲያውም ጥቅሙ የጎላ ነው። የተጫዋቾች ለውጥ አለመኖር ጎጂ የሚሆነው የተጫዋቾቹ ብቃት ወርዶ ከቡድኑ አለመቀነሳቸው ነው። አሁን አሰልጣኘ ዮሃንስ ሳህሌ በያዙት ቡድን ውስጥ የታየውም ብቃታቸው የወረዱ ተጫዋቾች ለአንድ ዓመት ያህል ያለምንም ለውጥ በቋሚነት ሲጫወቱ መመልከታችን ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአገሩ ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ዋንጫም ሆነ በጎረቤት አገር ተዘጋጅቶ በነበረው አራተኛው የቻን ዋንጫ ላይ የታየው ቡድን ብቃቱ የወረደ፣ ሞራሉ የሌለው፣ ለመጫወት ፍላጎት የማይታይበት፣ ከዚህም አልፎ ስፖርታዊ ዲስፕሊን የጎደለው ሆኖ ነበር የታየው። “ ይህ ቡድን የትም አይደርስም አሰልጣኙም ሆነ ፌዴሬሽኑ በጊዜ መልስ ሊያስቀምጥ ይገባል” ሲሉ በርካቶች አስተያየታቸውን ሰጥተው ነበር። ነገር ግን ቡድኑ እንዲስተካከል አሰልጣኙም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ በነበረው ላይ “የሙጥኝ” ብሎ መቀጠልን ነው የመረጡት። ይህም በመሆኑ በዘወትር አገራዊና እግር ኳሳዊ ጠላት ተብለው በሚጠሩት አረብ አገሮች አንዷ በሆነችው አልጄሪያ የሰባት ለአንድ ሽንፈት ማስተናገድ ግድ ሆነ። በአልጄሪያው ጨዋታ እነማን ጥሩ ነበሩ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የትኞቹ ተጫዋቾች በተለየ መልኩ ለዋልያዎቹ ሽንፈት ተጠያቂ ይሆናሉ? ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። ምክንያቱም ሁሉም የቡድኑ አባላት ጥሩ አልነበሩምና።

ለዚህ ጥያቄ በመጀመሪያ ሊጠቀስ የሚችለው የቡድኑ አማካይ ክፍል ነው። በአማካይ ክፍል ላይ የተሰለፉት የኢትዮጵያ ቡናው ጋቶች ፓኖም እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ራምኬል ሎክ በእለቱ ያሳዩት ብቃት በእጅጉ የወረደ ነበር። አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ግን ራምኬልን ወይም ጋቶችን ከመቀየር ይልቅ በእረፍት ሰዓት በሀይሉ አሰፋን ነበር መቀየር የፈለጉት። ይህ ደግሞ በተለይም የጋቶች እስከ 80ኛው ደቂቃ ሜዳ ላይ መቆየት አልጄሪያዎችን ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው ችሏል። ምክንያቱም ጋቶች በትናንትናው ጨዋታም ሆነ በሌሎች ያለፉት የክለብ እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎቹ ለቡድን አጋሮቹ ጨዋታን ከማቅለል ይልቅ ለተጋጣሚ ቡድን የተመቸ አጨዋወትን የሚከተልና ጥፋት ከመስራት የማይመለስ ተጫዋች በመሆኑ ነው።

ከእነዚህ ሁለት ተጫዋቾች በተጨማሪ ደግሞ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለደካማው ተከላካይ ክፍላቸው ያሬድ ባዬህንና አሉላ ግርማን ከመጠቀም ይልቅ የሲዳማ ቡናውን አንተነህን እና የኢትዮጵያ ቡናውን አብዱልከሪም መሃመድን መጠቀም ቢችሉ ኖሮ ሽንፈቱ ባይቀር እንኳን የጎሉ መጠን ሊቀንስ እንደሚችል ይታመናል ሲሉ ይናገራሉ። በተለይ የፈረሰኞቹ ተከላካይ አሉላ ግርማ ለክለቡ ከቲፒ ማዜምቤ ጋር በሳምንት ሁለት ጊዜ መጫወቱ እና ልጁም በግሉ በመከላከል በኩል ካለበት ድክመት አኳያ ከእሱ ይልቅ የቡናው አብዱልከሪም መሰለፍ ቢችል የተሻለ እንደነበረ ይገልጻሉ። ሆኖም አሰልጣኙ የመረጡት አሰላለፍ ያ በመሆኑ ቡድኑ የአገር አደራ ተሸክሞ በውርደት ሊመለስ ችሏል።

ይቀጥላል!!


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Gezegeta [697 days ago.]
 ከነ ስሕተቱም፣ ከነ ጠባዩም፣ ከነጉድለቱም፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ጀግና ነው፡፡ አበሻን በአንድ እግሩ ያስቆመ፤ ለሃያ አራት ሰዓታት የመግቢያ ትኬት ፍለጋ ያሰለፈ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የብሔራዊ ቡድኑን ዐርማ የያዙ ቲሸርቶች እንዲቸበቸቡ ያደረገ፤ ሕዝብ እንደ መንጋ ንብ አንድ ዓይነት ዜማ እንዲያዜም ያስቻለ፤ ሽማግሌን እንደ ሕጻን ያስጨፈረ፤ ሕጻንን እንደ ሽማግሌ ያስተከዘ፤ የፓርቲና፣ የዘር፣ የእምነትና የባህልን አጥር አስጥሶ ወገንን በአንድነት ገመድ ያስተሣሠረ፤ ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ ተረስተን ነበረ፤ ረስተንም ነበረ፤ ርቀን ነበረ፤ ተርቀንም ነበረ፤ ተርተን ነበረ፤ ተረት ሆነንም ነበረ፤ እግርን ከኳስ አውጥተን ለሩጫ ብቻ አውለነው ነበረ፤ እንዲያ በሩጫ ዓለምን አስደምመን፣ ኳስ ሜዳ ግን ዘጠና ደቂቃ መሮጥ አቅቶን ደክሞን ነበረ፡፡ ሕዝባችን ከካምቦሎጆ ኳስ ወደ ዲ ኤስ ቲቪ ኳስ ፊቱን አዙሮ ነበረ፡፡ ይህንን ቀይሮ በአፍሪካ ምድር ከ31 ዓመታ በኋላ ብቅ እንድንል ያደረገ፤ በዓለም መድረክ ‹እኛም አለንበት› እንድንል ያስቻለ - ይኼ ሰው ጀግና ነው፡፡ Long Live for Sewinet Bishawe Yohanes is fake and loser coach !

felexsami [697 days ago.]
 Yohanes eko endemaychil geltse new man endeshomew yetawekal ! koy gin Yohanes instructor new weys contractor ???!!!

Melaku [696 days ago.]
 እንደ ዮሃንስ አይነት arrogant አሰልጣኝ በህይወቴ አይቼ አላውቅም ሲበዛ እራሱን እንደ ተራራ በባዶ ሜዳ ላይ የቆለለ ግን ባዶ የሆነ ሰው ከባለሙያዎች ከሕዝቡ የሚሰጠውን አስተያየት ምክር ፈፅሞ የማይቀበል ግትር እኔ ብቻ አውቃለሁ ባይ ግን ባዶነቱን ያጋለጠ ባዶ አሰልጣኝ ! ፌዴሬሽኑ በምን መስፈርት ከማንስ ጋር አወዳድሮት እንደሾመው እሱን ብቻ ነው ማወቅ የምንፈልገው ?! ዮሃንስ እኮ ለዚህ ብሔራዊ ቡድን እንደማይመጥን በተጨባጭ እሱ እራሱ እዚሁ ሃገራችን ላይ በተዘጋጀ የደካሞች ውድድር ሴካፋ ላይ አይተነዋል የዛኔ ነበር ልክ ሴካፋ እናዳለቀ መባረር የሚገባው ገና ቡድናችን ቻን ሄዶ ሳይቀለድበት በእነ አልጄሪያ ታሪክ የማይረሳው ውርደት ሳንከናነብ በፊት ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ተቃጠልን ተቃጠል ዮሃንስ የስራህን ይስጥህ !!!

Gamo [696 days ago.]
 ጋቶች ማለት አቋሙ ከወረደ ቆየ ግን ለምን እንደሚመርጠው ግርም እኮ ነው የሚለን ልጁ በክለቡም ላይ የሚያሳየው አቋም በጣም የወረደ እንደሆነ ለማንም ስፖርት ተመልካች ግልፅ እያለ ዮሃንስ ግን በምን አይነት መነፅር እያየው ሁልጊዜ እንደሚጠራው ቤስት አድርጎም እያሰለፈው እንደሚያስበላን ይገርመኛል

solomon A [696 days ago.]
 ማክሰኞ ከፍተኛ ተቃውሞ እናሰማለን የሃንስ ላይ እሱም እቺን ነገር ይጠብቃታል ማክሰኞ የሚገባበት ጉድጓድ ነው የሚጠፋው እርግጠኛ ነኝ ከመቀመጫው አይነሳ እራሱን ይደብቃል

Fikeru [696 days ago.]
 ይሄ ማፈሪያ የሆነ አሰልጣኝ እሱን ብሎ ኢንስትራክተር በኮች ሰውነት ቢሻው ደራታችንን ነፋ አንገታችንን ቀና ያደረግነውን አንገታችንን እንድንደፋ እንድናቀረቅር እንድናፍር አደረገን

Binman-Coffee [696 days ago.]
 ጨዋታውን እንኳን አይቶ አንብቦ ማስተካከል መቀየር የማይችል አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ነው ትሉኛላችሁ ! ኧረ አይደለም ኧረ አይነፋም ! ውይይይይይይይይ ተቃጠልን 7 ጎልልልልልልል ኧረ ዮሃንስ እኔ አንተን ብሆን ከብሔራዊ ቡድኑ እራሴን ብቻ ሳይሆን የማገለው እራሴንም ጭምር ነበር ከዚች ምድር ላይ የማጠፋው ::

Mamush [696 days ago.]
 7 ጎልልልልልልልልል ኧረ ይደብራል ያሳፍራል የሶማሊያ ውይም የጅቡቲ ብሔራዊ ብድን እንኳን ይሄን ያክል ጎሎች አያስተናግድም

bikila [694 days ago.]
 yohanis yemibal aselitagncheguara asyazen bewunet meshenef yale new gin metekem yemigebahn techawach satitekem asafari shinfet mekebel betam yigermalina ebakachihu ahunm alimeshem sewunet bishawun kech argut

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!