Recently Posted News
  “ለቢሊዳው ጨዋታ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የምወስደው እኔ ራሴ ነኝ” አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ
መጋቢት 21, 2008


በይርጋ አበበ

ባሳለፍነው ዓርብ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4፡30 ሲሆን በአልጄሪያዋ ቢሊዳ ከተማ የተካሄደውን የአልጄሪያ እና የኢትዮጵያ ጨዋታ በሰፊ የግብ ልዩነት ባለሜዳዎቹ ማሸነፋቸው ይታወሳል። ውጤቱን ተከትሎም በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያን እግር ኳስ የሚከታተሉ መገናኛ ብዙሃንና የስፖርቱ ደጋፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ ሰንብተዋል።

    
ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ዝግጅት ክፍልም በቅዳሜ ዝግጅቷ “ከሽንፈትም በላይ የሆነው የዋልያዎቹ ሽንፈት” በሚል ርዕስ አንድ ሰፋ ያለ መጣጥፍ አዘጋጅታ ለአንባቢያን አቅርባ ነበር። በወቅቱ የኢትዮፉትቦል ዝግጅት ክፍል ለንባብ ባበቃችው አርቲክል ለከፋው ሽንፈት ምክንያቶችንና ተጠያቂዎች እነማን ናቸው የትኞቹ ተጫዋቾችስ ለብሔራዊ ቡድን የማይመጥን ብቃት ይዘው አገራቸውን አሳፍረዋል የሚሉ መጠይቆችን አቅርበን ለተወሰኑት መልሰ ለመስጠት ሞክረን ነበር።

በዛሬው ዝግጅታችን ደግሞ ትናንት አመሻሹ ላይ በካምቦለጆ ተካሂዶ ሶስት እኩል በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በኋላ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል የተወሰኑትን እነሆ ብለናል።

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ አልጄሪያ ላይ ለተመዘገበው የከፋ ውጤት “ውጤቱ እኛን የሚመጥን አይደለም። ለዚህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂው እኔው እራሴው ነኝ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን አያይዘውም ከሜዳ ውጭ የሆኑ ሌሎች ምክንያቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል። በተለይ ለአንድ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለ20 ሰዓታት እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር እንዲጫወቱ መደረጉ ለውጤቱ መክፋት ተጨማሪ ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ተናግረዋል። ሆኖም አሰልጣኙ ለዚህ የከፋ ውጤት ኃላፊነቱን ከመውሰዳቸውም በዘለለ “የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በተለይ ስለ ቡድኑ የአልጄሪያ ጉዞ ሲናገሩ “አንድ ሰው 20 ሰዓት ሳይተኛ መኪና መንዳትም ሆነ አውሮፕላን መንዳት አይችልም። እግር ኳስን ያህል ትልቅ ስፖርት እና አልጄሪያን ያህል ትልቅ ቡድን ስትገጥም ደግሞ በቂ ዝግጅት እና እረፍት ማድረግ ይገባሃል እንጂ በዚያ መልኩ ተጉዘህ መሆን አልነበረበትም” ሲሉ ገልጸዋል።  

አሰልጣኝ ዮሃነስ ሳህሌ ትናንት ምሽት ቡድናቸው ስላሳየው የተሻለ ብቃት ተጠይቀው ሲመልሱም “በእኔ ግምት ፔናሊቲው እስከተሰጠብን ሰዓት ድረስ ሙሉ በሙሉ እኛ የተሻልን ነበርን። ቡድኑ ዛሬ ተሻሽሎ የቀረበውም በተጋጣሚያችን አጨዋወት ላይ መሰረት በማድረግ ነው። ለዚህም ቢሊዳ ላይ የአልጄሪያን አጨዋወት ማለትም በክንፍ በኩል አጥቅተው እንደሚጫወቱ ስላወቅን ነው። ተጫዋቾቼ ላሳዩት ብቃትም ላመሰግናቸው እወዳለሁ” ብለዋል። በእለቱ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ታደለ መንገሻን ቀይረው ስላስወጡበት ምክንያት ተጠይቀው “በመድከሙ ብቻ ነው የቀየርኩት እንጂ ሌላ ምክንያት አልነበረኝም” ብለው መልሰዋል።

በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎችና በተለይም ታላላቅ የዌብሳይት መገናኛ ብዙሃን “አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከኃላፊነታቸው ለመነሳት መልቀቂያ አስገብተዋል። የአዲስ አበባው ጨዋታ የእሳቸውን ቆይታ የሚወስን ይሆናል” የሚሉ ዘገባዎች ተዘግበው ነበር። በዚህ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበላቸው አሰልጣኝ ዮሃንስ “በሌለ ነገር ላይ የምናገረው ነገር አይኖርም። መልቀቂያም አላስገባሁም” ሲሉ በአጭሩ መልስ ሰጥተዋል።

ዋልያዎቹ በአራት የአፍሪካ ዋነጫ ማጣሪያዎች በአንድ ጨዋታ ተሸንፈው፣ በሁለት አቻ ወጥተውና አንድ ጨዋታ አሸንፈው አምስት ነጥብ ይዘዋል እና አምስት የጎል እዳ ይዘው ከምድባቸው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።  

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Tekleab Tekeste [693 days ago.]
 Ethiopian Ahunim Tesfa mequrex Ayasfeligim mebertat newuna daily practise.chigirochin bemexeyayeq meftat new ayizowachihu...!

Tekleab Tekeste [693 days ago.]
 Ethiopian Ahunim Tesfa mequrex Ayasfeligim mebertat newuna daily practise.chigirochin bemexeyayeq meftat new ayizowachihu...!

Tekleab Tekeste [693 days ago.]
 Ethiopian Ahunim Tesfa mequrex Ayasfeligim mebertat newuna daily practise.chigirochin bemexeyayeq meftat new ayizowachihu...!

Gezegeta [693 days ago.]
 ግርም ድንቅ የሚለው የሚያቃጥለው የዚህ ሰውዬ አስተያየት ነው:: በሰራው ቡድን.... ኧረ ቡድን ሳይሆን በድን ስፖርት አፍቃሪው ተቃጥሎ ! በሚሰጣቸውም አስተያየቶች ተቃጥለን ! እስከመቼ እንችለዋለን ?! "በዕለቢሊዳው ጨዋታ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የምወስደው እኔ ራሴ ነኝ” ha ha እና ማን እንዲሆንለት ነበር የሚፈልገው ?! ha ha ”አሁንም የማለፍ ተስፋችንን አልተሟጠጠም” ha ha 7 ጎሎች አስተናግዶ ከደርዘን በላይ ደግሞ "ሶስት ነጥቦች ብቻ ነው ያጣነው” ha ha "ሁለተኛ ሆነን እናልፋለን” ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ እንዴት ያቃጥላል ይህ ሰውዬ ባካችሁ !!! ጥሩ ሁለተኛ ሆነን ብናልፍ እንኳን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ምንም ነገር ከዚህ ሰውዬ አንጠብቅም ! የባሰ ከ 7 በላይ ጎሎች አንገት የሚያስደፋ የሚያሳፍር ውጤት ይዞልን ይመጣ ይሆናል እንጂ ምክንያቱም እናውቀዋለና አይተነዋላ ! ሃገራችን ላይ በተዘጋጀው የደካሞች ውድድር ሴካፋ ላይ ምን አይነት አሳፋሪ ቲም እንዳሳየን እንዲሁም ቻን ላይ pls leave us alone pooooor Looser Yohanes !

Mali [693 days ago.]
 አላውቅም እውነት ግን እሱ ኢንስትራክተር ነው ወይስ ኮንትራክተር ኧረ ባካችሁ አጣሩልን የትላንትናው ጨዋታ ላይ ማን ኦፍ ዘ ማች ማን ነው ተብለው ሲጠየቁ የአልጄሪያው ኮች ጎርኩፍ የዋልያው አማካይ ታደለ መንገሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይታያቹ እንግዲህ ይሄ ልጅ በዮሃንስ የመሰለፍ እድል የተነፈገ ተጫዋች ነው ትላንትናም አስራት ስለተጎዳ ነው የግዱን ያስገባው አይ ዮሃንስ ቀልድብን አንተ ምን ታደርግ ፌዴሬሽኑ ነው ሳትችል ትችላለህ ብሎ የሾመህ ::

Samuel Bezabeh [693 days ago.]
 እኔ ኳስ ማየት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ እንደ ዮሃንስ አይነት ትቢተኛ ግትር ቀሽም አሰልጣኝ አይቼ አላውቅም ::

Sisay-Awassa [691 days ago.]
 አይ ዮሃንስ 7 ጎሎች አስተናግደህ ተመልሰህ ብሔራዊ ቡድኑን አዋርደህ ያጣነው 3 ነጥብ ነው ትላለህ ማፈሪያ ስንት መመረጥ የሚገባቸው ልጆችን በግትርነትህ የሰውነት ቢሻው ቡድን ውስጥ ስለነበሩ ብቻ የራስህን ክሬዲት ከፍ ለማድረግ ስለፈለክ የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ብለክ ስንቶቹን ልጆች ገፋሃቸው ሃገራችንንም አዋረድካት አሰደብካት :: አስራት መገርሳን ባለቀ ሰዓት በህዝቡ ግፊት በሚዲያው ግፊት ብትጠራውም ግፍ ከተፈፀመባቸው ተጫዋቾች አንዱ ነበር ግን ማንነቱን እያሳየክ ያለ ጀግና ነው::ኧረ ስንት ልጆች አሉ እነ አዲስ ... ምንያህል ተሾመ .....ምንተስኖት .... አበባው ቡታቆ.... ተስፋዬ አለባቸው ....ቡድኑን መጥቀም እየቻሉ በአንተ ግፍ የተፈፀመባቸው በሃይሉ አሰፋን የመሰለ ልጅ እንኳን እንዴት አድርገህ መጠቀም እንዳለብህ ገና አላወክም ::

Cameron [464 days ago.]
 Hello my name is Cameron and I just wanted to drop you a quick note here instead of calling you. I came to your “ለቢሊዳው ጨዋታ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ የምወስደው እኔ ራሴ ነኝ” አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ page and noticed you could have a lot more traffic. I have found that the key to running a successful website is making sure the visitors you are getting are interested in your subject matter. There is a company that you can get keyword targeted visitors from and they let you try the service for free for 7 days. I managed to get over 300 targeted visitors to day to my site. https://fsuh.de/yourls/C

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!