Recently Posted News
  ፋሲለደስ የሚያስተናግደው የፈረሰኛውና የቢራው ፍልሚያፋሲለደስ የሚያስተናግደው የፈረሰኛውና የቢራው ፍልሚያ
መጋቢት 28, 2008

በይርጋ አበበ

በየምክንያቱ የሚቆራረጠው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ተስተካካዮችን ሳያካሂድ ነው የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቀው። ከሁለቱ ተስተካካይ ጨዋታዎች መካከል አንዱ ዛሬ በጎንደሩ ፋሲለደስ ስታዲየም ይካሄዳል። ተጋጣሚዎቹ ደግሞ ከደረጃው ግርጌ ሁለተኛ ላይ እና ከደረጃው አናት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ዳሽን ቢራ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ናቸው። ጨዋታውም ከቀትር በኋላ 9፡00 ሲሆን የሚከናወን ይሆናል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ስለጨዋታውና ስለቡድኖቹ ወቅታዊ ብቃት ያደረገውን መጠነኛ ዳሰሳ ከዚህ በታች እንዲህ ቀርቧል።

የጨዋታው ወሳኝነት

በስፖርት ዓለም መሸነፍ ለበጎ ይሆናል ተብሎ አይጠበውቅም። ምክንያቱም አንድ ቡድን በጨዋታ ተሸነፈ ማለት ለዋታው ከተመደቡት ሶስት ነጥቦች ምንም ሳያገኝ ወጣ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ተሸናፊው በባዶ ከመውጣቱም በላይ አሸናፊውን የሶስት ነጥብ ጌታ ስለሚያደርገው በአሸናፊውና በተሸናፊው ቡድኖች መካከል በአንድ ጨዋታ ብቻ ልዩነቱ የስድስት ነጥብ ይሆናል ማለት ነው። ለዚህም ነው በስፖርት ዘርፍ በተለይም በእግር ኳስ ስፖርት መነፍ እጅግ መራር የሚሆነው።

ዛሬ በሚካሄደው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም በተለይ ለባለሜዳው ዳሽን ቢራ ውጤቱ አስፈላጊነቱ እጅግ ከፍተኛ ነው። ምክንያቱም ዳሽን ቢራ ዛሬ ማሸነፍ ከቻለ ነጥቡን 16 በማድረስ እንደ ኢትዮጵያ ቡና እና አርባ ምንጭ ከነማ ያሉትን ቡድኖች ከኋላው አሰልፎ የመጀመሪያውን ዙር እንዲያጠናቅቅ ያስችለዋል። ነገር ግን ይህ ባይሆንና ዳሽን ቢራ በደጋፊዎቹ ፊት የሽንፈት ጽዋን የሚጎነጭ ከሆነ ፕሪሚየር ሊጉ ሲጀመር አንስቶ ግርጌውን የሙጥኝ ብሎ ከቆየው ሆሳዕና ሀድያ ጋር ጉርብትናውን ያጠናከራል። ይህም ማለት በዚህ ወቅት ጀምሮ ከደረጃው ግርጌ ሆና ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የሚፍጨረጨር ከሆነ በዓመቱ መጨረሻ ምንልባትም የከፋ ውጤት ሊያስመዘግብ ያስችለዋል።

ውጤቱ ለዳሽን ቢራ የህልውናው ጉዳይ ይሁን እንጂ ለፈረሰኞቹም እጅግ በጣም ያስፈልጋቸዋል። ምክንያቱም የ12 ጊዜ የሊጉ ሸምፒዮናዎች በዚህ ዓመት 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን ሲያከብሩ ዋንጫውን ይፈልጉታል። የሊጉን ዋንጫ ለማግኘት ግን መንገዳቸው ቀላል እንዳይሆን ያደረገው በአሁኑ ወቅት ሊጉን እየመራ ያለው ደደቢት ተጠናክሮ መቀረቡ ነው። ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ፈረሰኞቹ የደደቢትን ግስጋሴ ለማስቆምና የሊጉን መሪነታቸውን ለመረከብ የአንድ ጨዋታ ሙሉ ሶስት ነጥብ ብቻ ይበቃቸዋል። ስለዚህም ወደ መሪነት ለመመለስ ዛሬ በዳሽን ቢራ ላይ የበላይነትን ለመውሰድ በሙሉ አቅማቸው እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።

የቡድኖቹ ወቅታዊ ብቃት


በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሩ ጉዞ አድርገው በወቅቱ የአህጉሪቱ ሀያል ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ሶስት ለሁለት በሆነ ድምር ውጤት ተሸንፈው ጉዟቸው የተገታባቸው ፈረሰኞቹ በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ውስጥ ካሉ ክልቦች መካከል በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ክለብ ያደርጋቸዋል። ቡድኑ በየ ቦታው በቂ ተጠባባቂዎችን ከመያዙም በላይ አብዛኞቹ የቡድኑ አባሎች ለረጅመ ጊዜ አብረው የቆዩ መሆናቸውና የክለቡ አመራሮችም ዘወትር ለድል የተራቡ በመሆናቸው የፈረሰኞቹ ብቃት ዘወትር እየታደሰ ሰሄድ እንጂ ሲወርድ አይታይም።

በአንጻሩ የዳሽን ተራራው ክለብ በዚህ ዓመት አጀማመሩን አሳምሩ ወደ መሃል ግን ወገቤን ብሎ በደረጃው ግርጌ ላይ ሆሳዕና ሀድያን ብቻ በልጦ 13ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገድዷል። የክለቡ ስብስብ ጥራት የሌለው ከመሆኑም በላይ በየዓመቱ ተጫዋችና አሰልጣኝ የመቀያየር ባህሉ በየዓመቱ ረብጣ ብር የሚያወጣው ክለብ በየዓመቱ ላለመውረድ የሚጫወት አድርጎታል። የዚህ ዓመት የክለቡ ጉዞም ከወራጅ ለመዳን እንጂ ለዋንጫ የሚጫወት እንደማይሆን ግልጽ ነው።

ማጠቃለያ

በ1632 በነገሱትና በገናናው የጎንደር ንጉስ አጼ ፋሲለደስ ስም የተሰየመው የጎንደሩ “ፋሲለደስ ስታዲየም” ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያካሂዳል። የጨዋታው ወሳኝነት ደግሞ ሜዳ ላይ ከሚመዘገበውም ውጤት የዘለለ ነው እሱም ዳሽን ቢራ ሊጉን ከተቀላቀለበት ጊዜ ጀምሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሜዳው ሲጫወት በሰላም ተጠናቆ አያውቅም። ዛሬስ ቢራው እና ፈረሰኞቹ በምን አይነት መንገድ ጨዋታቸውን ያጠናቅቃሉ?


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Gezegeta [684 days ago.]
 ይሄ ገፊ የውሸት ፌክ አሰልጣኝ ተብዬ ከተሾመ ጀምሮ ፊፋ በየወሩ በሚያወጣው የፊፋ ኮካ ኮላ የሃገራት ደረጃ ኢትዮጵያ 123 ኛ ደረጃን ይዛለች በማርች ወር 120 የነበረችው ኢትዮጵያ ከባለፈው ወር ሶስት ደረጃዎችን ወርዳ 123 ኛ ሆናለች፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ጁነዲን እና ዮሃንስ በሚገርም ፍጥነት ወደቁልቁል እያወረዳችሁን ነው በርቱልን !!!

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!