Recently Posted News
  ኢትዮጵያ ቡና ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት ከዓለም አቀፍ ውድድር ውጭ ሆነኢትዮጵያ ቡና ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት ከዓለም አቀፍ ውድድር ውጭ ሆነ
ሚያዚያ 03, 2008

ኢትዮጵያ ቡና ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት ከዓለም አቀፍ ውድድር ውጭ ሆነ

በይርጋ አበበ

ከአምስት ዓመት በፊት በ2003 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አንስቶ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ተካፋይ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ቡና ከዚያ ዓመት በኋላ በየትኛውም አህጉራዊ ውድድር መሳተድፍ አልቻለም ነበር። ይህንን መጥፎ ታሪኩን በቀጣዩ የውድድር ዓመት ለመቀየር ይጥራል ተብሎ የነበረው ቡና ግን ካለፉት ጥቂት ዓመታት ውድቀቱ የተማረ አልመሰለም። ትናንት በተካሄደው የጥሎ ማለፉ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በአዳማ ከነማ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አራት ለሁለት ተሸንፎ ከውድድሩም ሆነ ከአህጉራዊ ተሳትፎ ተስፋው ውጭ ሆኗል። ይህ ጨዋታም ቡና በዚህ ዓመት በሶስት አጋጣሚዎች ውጤቱን በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ለመወሰን የተገደደበት ጨዋታ ነው። ለመሆኑ ቡና በእነዚህ አምስት የውድድር ዓመታት ወደ ኋላ የተጓዘው ለምን ይሆን?

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ኢትዮፉትቦል ዶትኮምን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃንና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሙያዊ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል። በክለቡ ውጤት ላይ ሁሉን አቀፍ ተጠያቂነት ያለበት የክለቡ የቦርድ አመራር ግን መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ሌሎች የድክመታቸውን ምክንያቶችና ሰበቦችን ከማቅረብ የታቀቡበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል። ትናንት በተካሄደው የጥሎ ማለፉ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታም የድራጋን ፖፓዲች ልጆች በአዳማ ከነማ ላይ የጨዋታ እና የጎል ሙከራ የበላይነትን ቢይዙም የእግር ኳስ የመጨረሻ ወሳኝ በሆነው በአሸናፊነት ላይ ስማቸውን ማስመዝገብ ግን አልቻሉም።

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችም የቡድናቸው ተደጋጋሚ ውጤት አልባ ጉዞ አሳስቧቸው ሳይሆን አይቀርም ከክለባቸው ስራ አስኪያጅ እስከ ቦርድ ሰብሳቢው ድረስ ያሉ አመራሮቻቸውን ሳይቀር ስም እየጠሩ ሲወቅሱ የታዩት። በተለይም የውጤቱ መክፋት አንገታቸውን ያስደፋቸው ደጋፊዎች የክለባቸውን ተጫዋቾች ይዞ ይጓዝ የነበረውን የቡድኑን ሰርቢስ መንገድ ላይ አስቁመው የሀይል እርምጃ እስከመውሰድ ሲገላገሉ ታይተዋል። ይህ ሁሉ የክለቡ ውድቀት አመላካች ውጤት ለምን ከቡና ቤት መጣ? ብሎ መጠየቅና ወደ መፍትሔ መሄድ አሁን የሁሉም የክለቡ አባላት የቤት ስራ ይመስለናል።

በሌላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን በሸይቩ ጂብሪል እና ቢኒያም በላይ ሁለት ግቦች ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ተቀላቅሏል። በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀሉክለቦች ሶስት ሲሆኑ እነሱም ያለፈው ዓመት የዋንጫ ባለቤት መከላከያ፣ አዳማ ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆኑ ቀሪው ተሳታፊ ቡድን ደግሞ ከአርባ ምንጭ ከነማ እና ከፈረሰኞቹ አሸናፊው ሲለይ ይታወቃል።

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Biruk [682 days ago.]
 ይሄ ወረኛ ቀናተኛ ስራ ሳይሆን ወሬን የሚያውቅ ክለብ ሌሎች በስራ ጥለውት የሄዱትን ክለቦች ዘወትር የሚሳደብ የሚንቅ የማያከብር ሁሌም ለሽንፈቱ ዳኛን ፌዴሬሽንን ሳሩን ቅጠሉን ዝናቡን ሰበብ የሚያደርግ ደጋፊው ተጫዋቹ አመራሩ ፍንዳታ ! እኔ ግርም የሚለኝ የዚህ ክለብ ለሃገራችን እግር ኳስ እያደረገ ያለው ጥቅም ምኑ ላይ ነው ? ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ስድባቸው ድንጋያቸው ባሰብን እኮ:: በቡና ክለብ ደጋፊ ሰርቪሱ ያልተሰበረበት ያልተደበደበ ያልተፈነከተ ያልተሰደበ ክለብ እስቲ አለ ?! ለነገሩ የፌዴሬሽኑ ድክመት ነው እንጂ ይሄ ክለብ ስንት እና ስንት አስከፊ ጥፋቶች እየፈፀመ በዝምታ ታልፏል :: ፌዴሬሽኑ ለምን ይሄን ክለብ እንደሚፈራው ግርም ይለኛል !!!!!!!!!!!!!!!! ስንት በዳኛ የተበደሉ ግፍ የደረሰባቸው ክለቦች እንዳሉ እየታወቀ ቡና የተባለው ክለብ በ አንድ ጨዋታ ላይ ኢሊጎሬ ተከለከልኩ ብሎ ኡ፤ኡ፤ኡ፤ኡ ስላለ ዳኛን አንድ አመት መቅጣት ምን ይሉታል ?!!!!!!!!!!!!!!!!!!! የሌሎች ክለቦች እንባስ መቼ ነው የሚታፈሰው ? ኧረ መቼ ነው ?!!!!!!!!!! ሌሎች ክለቦችን ፌዴሬሽኑ እንደ እንጀራ ልጅ ማየት የሚያቆመው መቼ ነው ?!!!!!!!!!! አሁን በቅርቡ እንኳን ቡና የተባለ ክለብ ለይቅርታ የሚከብድ ህጉን ጥሶ ህጉን ተላልፎ ተጫዋች አሰልፎ ተገኝቷል ግን ፌዴሬሽኑ ባላየ ባልሰማ አልፎታል:: ለምን ዳሽን ቢራ : ሃዲያ ሆሳህና :እና አርባምንጭ ከነማ ህጉ ይከበር ብለው ፌዴሬሽኑን ወጥረው ለምን እንዳልጠየቁ ግርም ነው የሚለው ! ኧረ ህጉ ይከበር ፌዴሬሽኑንም እራሱንና ህጉን ያስከብር ወይም ቦታውን ይልቀቅ መስራት ለሚችሉ ሰዎች !!!

Gezegeta [682 days ago.]
 ኡፍፍፍፍፍፍፍ ምናለ ወርዶ ብንገላገለው ይሄ ፍንዳታ ወረኛ ቀናተኛን ክለብ ቡላ ገለባን

Samifelex [681 days ago.]
 ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ 13 ኛ ጊዜ ሻምፒዮን ሊሆን ነው በጣም ይገርማል እንደ ቡላ ገለባ አይነቱ ወረኛ ክለብ ደግሞ ቁጭ ብሎ ያወራል መፎካከር ሲያቅተው:: ኧር ተፎካከሩ ባካችሁ የፕሪም የር ሊጉ መስራች ብትሆኑም ሻምፒዮን የሆናችሁት ግን አንድ ጊዜ ብቻ ነው:: በጣም ያሳፍራል የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ነን ትሉ የል እንዴ ?! መፎካከር በወሬ ብቻ ነው እንዴ ?! ብና ገለባ አደገኛ እያላችሁ ት ዘምሩ የል እንዴ ?!

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
Comment:  *
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!