Recently Posted News
  የቴስታውንጉስወደጨዋታተመለሰየቴስታውንጉስወደጨዋታተመለሰ
ሚያዚያ 04, 2008

በይርጋአበበ

በኤሊባቡር ዞን በደሌ ከተማ ተወልዶ ያደገውና ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ ጋር ስኬታማ ጊዜ አሳልፎ ሀዋሳ ከነማን የተቀላቀለው ግዙፉ አጥቂ ተመስገን ተክሌ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ክለቡ መመለሱን የኢትፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ገለጹ። ከጥቂት የእረፍት ጊዜያት ቆይታ በኋላም ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ይጠበቃል።

ለመሆኑ የተመስገን ጉዳት ምንድ ነው?

በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሰውነታችን ላይ መጠነኛ ጉዳት ሲገጥመን ቶሎ ታክመን ከመዳን ይልቅ ጉዳዩን በይደር ማቆየትና በራሱ ጊዜ እንዲድን ማድረግ የቆዬ ልማዳችን ነው ማለት ይቻላል። በተመስገን ተክሌ ላይ የተፈጠረውም ከዚህ የተለየ አይደለም። እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ በተመስገን እግር ላይ የደረሰው ጉዳት በጉልበቱ ላይ ሲሆን ጉዳቱን በጊዜ ታክሞ መፍትሄ ለማግኘት ከመፈለግ ይልቅ በቸልተኝነት ስላየው ጉዳቱ እየቆዬ ሲሄድ በእግሩ ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርስበት ችሏል። ጉዳቱ እየከፋ ሲሄድም ግዙፉ አጥቂ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመሄድ ህክምናውን ለመከታል ተገድዷል።

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ተመስገን

            እግር ኳስን በትውልድ ከተማው በደሌ ተጫውቶ ስኬታማ መሆን የቻለው አጥቂው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ክለቦች አቅንቶ ለኢትዮጵያ መድን፡ ኒያላ እና ደደቢት ተቻውቷል። ከደደቢት ጋር ያለውን ቆይታ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ደቡብ ክልል መዲናዋ ሀዋሳ ከነማ በማቅናት እስካሁኑ ሰዓት ድረስ በዚሁ ክለብ እየተጫወተ ይገኛል። በሀዋሳ ቆይታውም በተደጋጋሚ ጊዜ ለቡድኑ ወሳኝነታቸው ከፍተኛ የሆኑ ጎሎችን በማስቆጠሩ በደጋዎችና በክለቡ አመራች የተወደደ ተጫዋች ነው ተመስገን ተክሌ።

            ለሀዋሳ ከነማ ለስድስት ወራት ብቻ ፈርሞ የነበረው የቴስታው ንጉስ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ጨዋታዎች ባሳየው ብቃት የተማረኩት ቀጣሪዎቹ የልጁን አገልግሎት ከስድስት ወራት በላይ እንዲቆይ ፈለጉ። ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን ስምምነት አደረጉና ተጫዋቹ የሀዋሳ ከነማ ወሳኝ ተጫዋች ሆነ። ክለቡ ባፈው የውድድር ዓመት ለመውረድ ጫፍ በደረሰበት ወቅት ግን ተመስገን ተክሌ ብቻውን 11 ጎሎችን በማስቆጠር ክለቡን ከመውረድ ደጋዎችን ደግሞ ከውርደት ታድጓል።

            በአገራችን እግር ኳስ በተለይም በዚህ ወቅት በግንባር ገጭቶ ጎል የሚያስቆጥር ተጫዋች በሌለበት ሊግ ውስጥ ግዙፉ አጥቂ ግን በርካታ ጎሎችን በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር ተለይቶ ይታወቃል። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው ሀወሳ ከነማ አራት አጥቂዎቹን በብቃት መውረድ ምክንያት ማሰናቱን ተከትሎ የአጥቂ ችግር ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት ግን ተመስገን ተክሌ ደርሶለታል። በዚህ ዓመት አንድም ጨዋታ አካዶ የማያውቀው ተመስገን ተክሌ ከጉዳት መልስ በቀድሞ ብቃቱ ላይ ቶሎ ላይገኝ ቢችልም ሊጉ ገና የውድድር ዓመቱ አጋማሽ ላይ በመሆኑ ተመስገንም ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ በመሄድ ለቡድኑ ወሳኝ እንደሚሆን ግን አያጠራጥርም።

ውድ አንባቢያን ተመስገን ተክሌን በስልክም ሆነ በአካል ካገኘነው ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንደምንመለስ ቃል እንገባለን።

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!