Recently Posted News
  በፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ ሳምንት እነማን ይገናኛሉ?በፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ ሳምንት እነማን ይገናኛሉ?
ሚያዚያ 17, 2008

በፕሪሚየር ሊጉ 16ኛ ሳምንት እነማን ይገናኛሉ?

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብር ከተጀመረ ሁለት ሳንታትን ያስቆጠረ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ሁለቱንም ጨዋታዎቻቸውን ያሸነፉት ክለቦች ቁጥር ውስን ነው። የአዲስ አበባው ኢትዮጵያ ቡና እና የደቡቡ ሀዋሳ ከነማ ብቻ ናቸው። ቀሪዎቹ ክለቦች ግን በአንደኛው ጨዋታ ነጥብ ተጋርተው ወይም ተሸነፈዋል። እንደ ደደቢት፣ ኤሌክትሪክ እና ሲዳማ ቡና አይነቶቹ ደግሞ በሁለቱም ጨዋታዎቻቸው ሽንፈትን አስተናግደዋል። ሊጉ ነገ ማክሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በክልል ከተሞች ቀጥሎ ይውላል። በዚህ መርሃ ግብር መሰረት እነማን ይፈተናሉ የትኞቹስ ቀላል ጨዋታ ያደርጋሉ የሚለውን ከዚህ በታች ባለው ፕሮግራም መሰረት አንባቢ ፍርዱን ማስቀመጥ ይችላል።

አዳማ ከቡና

አዳማ ከነማ ወጥ አቋም ማሳየት ባይችልም ከታላላቅ ቡድኖች ጋር ሲገናኝ ካለው የተፎካካሪነት ባህል እና በሜዳው ያለው የማሸነፍ ሪከርድ ተደማምሮ ነገ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ለእንግዳው ቡድን ፈተና ሊሆን ይችላል። የአጥቂ ችግር ያለበት የድራጋን ፖፓዲች ስብስብ በአጥቂው ያቡን ዊሊያም ላይ ብቻ ጥገኛ መሆኑ እና ተከላካዩ ወንድይፍራው ጌታሁን ባለፈው ሳመንት በቀይ ካርድ የተሰናበተ መሆኑ ለአዳማ ከነማ መልካም ዜና ነው። በአንጻሩ የአሸናፊ በቀለ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂው ጆሴፍ ፔንዛ በቀይ ካርድ የወጣበት በመሆኑ ለቡናዎች መልካም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ጨዋታው ነገ ከቀትር መልስ በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኤሌክትሪክ

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ቡድኖች የሚገኙበት ደረጃ አራምባ እና ቆቦ የሚባል ነው። ፈረሰኞቹ በነጻነት ሊጉን ከአናት ሆነው ሲጋልቡ ኮረንቲው በበኩሉ ሀይሉን ተገፎ ግርጌውን ተጠግቶ ተቀምጧል። ሆኖም ግን ሁለቱ ክለቦች ሲገናኙ ካላቸው የቀየ ተቀናቃኝነት እና በአንድ ከተማ መገኘታቸውን ታሳቢ ስናደርግ ጨዋታው ቀላል ሊሆን እንደማይችል ይጠበቃል። በዚያ ላይ ደግሞ ኤሌክትሪክ ጨዋታውን ማሸነፉ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ እነዲገባ የሚያደርገው በመሆኑ ለኤሌክትሪክ የህልውና ጨዋታ ነው ማለት ይቻላል።

መከላከያ ከደደቢት

እነዚህ ቡድኖች ሲገናኙ ለመሸናነፍ የሚያደርጉት ፉክክር ከባድ ነው። በዚያ ላይ ሁለቱም ቡድኖች ባለፈው ሳመንት የሽንፈት ጽዋን የተጎነጩ መሆኑ የነገውን ጨዋታ ተጠባቂ ያደርገዋል። የመከላከያ ተጫዋቾች የአሰልጣኛቸው ገብረመድኅን ኃይሌ ልጅ ባሳለፍነው ሳምንት በድንገተኛ ሞት መለየቷን ተከትሎ አሰልጣኙ ሀዘን ላይ ይገኛል። ገብሬ በልጁ ሞት ምክንያት ሀዘን ላይ መቀመጡን ተከትሎ ተጫዋቾቹ ለአሰልጣኛቸው መጽናኛ ደደቢትን ለማሸነፍ ይገባሉ። ደደቢት በበኩሉ ካለፉት ወራት ወዲህ ያለውን የዋዠቀ አቋም ለማስተካከል መከላከያን እንደመነሻ ሊጠቀምበት ይችላል።

የደቡብ ደርቢ ሆሳዕና ሀድያ ከሀዋሳ ከነማ

ሀዋሳ ከነማ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ በዚህ ዓመት ያደረጋቸውን የሊግ ጨዋታዎች በሁለት መልኩ ሊገለጽ ይችላል። በሊጉ አጀማመር ላይ መልካም የነበው የደቡብ ክልል መዲናው ክለብ መሃል ላይ ግን ፍጹም ወርዶ ከታሰበውና ከተጠበቀው በታች ሆኖ ተገኘ። እንደገና ወደ መሀል ከወደቀበት ተነስቶ በአሁኑ ሰዓት በደረጃው አምስተኛ ላይ ሊቀመጥ ችሏል። ተጋጣሚው ሆሳዕና ሀድያ በበኩሉ ከአጀማመሩ ጀምሮ ወደታች የሚያደርገውን ጉዞ ያለ ተቀናቃኝ እየተጓዘበት ይገኛል። በ15 ጨዋታዎችም ስድስት ነጥቦችን ብቻ ይዞ ከሀዋሳ ከነማ በ16 ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ27 ነጥብ አንሶ ግርጌው ላይ ተኝቶበታል።

ነገ በሆሳዕና ስታዲየም የሚገናኙት ሁለቱ ቡድኖች በዚህ የነጥብና የከፍታ ደረጃ ላይ ሆነው ቢሆንም የእግር ኳስ ነገር አይታወቅምና ውጤት መተንበዩ ይከብዳል።

ድሬዳዋ ከሲዳማ ቡና

ሁለቱ ቡድኖች ያለፈውን ሳምንት በሽንፈት ያጠናቀቁ ክለበ ች ናቸው። ድሬዳዋ ከነማ ሊጉን በዚህ ዓመት የተቀላቀለ ቢሆንም እያሳየ ያለው አቋም መልካም መሆን አስገራሚ ሆኗል። በአንጻሩ ሲዳማ በቡና በየዓመቱ ለዋንጫ ተጠብቆ በደረጃው አጋማሽ ላይ ሆኖ ማጠናቀቅ ልምዱ አድርጎታል። እነዚህ ክለቦች ነገ ከቀትር መልስ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ወላይታ ድቻ ከዳሽን ቢራ

ሁለቱ ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉት በተመሳሳይ የውድድር ዓመት ቢሆንም በሊጉ እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ግን የተለያዬ ነው። ዳሽን በርካታ ገንዘቦችን ለተጫዋቾች ዝውውር እያወጣ ቢያስፈርምም ውጤቱ ግን ኮከቦቹን ለሌላ ክለብ አሳልፎ ከሚሰጠው ወላይታ ድቻ ያነሰ እንጂ የበለጠ ሆኖ አያውቅም። በዚህ ዓመትም ዳሽን 12ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወላይታ ድቻ ግን አራተኛ ደረጃ ላይ ነው ያለው። ሁለቱ ክለቦች ነገ ቦዲቲ ላይ ሲገናኙም ይህን ያህል ልዩነት በመካከላቸው አስቀምጠው ነው።

ንግድ ባንክ ከአርባ ምንጭ ከነማ

በዚህ ዓመት ለሊጉ ዋንጫ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከነበሩ ክለቦች መካከል ቀዳሚው ንግድ ባንክ ነበር። እንደ ሸይቩ ጂብሪል እና ፍቅረየሱስ አይነት አማካይ ተጫዋቾችን ከነባሮቹ ጋር የቀላቀለው የጸጋዬ ኪዳነማሪያም ቡድን ሜዳ ላይ ግን የተጠበቀውን ያህል ሆኖ አልተገኘም። ጸጋዬ ኪዳነማሪያም የሚያሰለጥናቸው ክለቦች መሀል ሜዳ ላይ የኳስ ቁጥጥርን ከፍጥነት ጋር አቀላቅለው የሚጫወቱ ተጫዋቾችን በብዛት የሚይዝ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም በዚህ ዓመት ግን ንግድ ባንክ ከተጠበቀው በታች ሆኖ ተገኝቷል። ሆኖም ነገ የሚገጥመው አርባ ምንጭ ከነማም እንደ ታደለ መንገሻ እና እንዳለ ከበደ አይነት የኳስ አርቲስቶችን ቢይዝም የፊት መስመሩ ደካማ በመሆኑ ማሸነፍ የተሳነው ሆኖ ተገኝቷል። ንግድ ባነክ ባለፈው ሳምንት ደደቢትን አሸንፎ ነጥቡንና ደረጃውን ያሻሻለው ንግድ ባንክ ከአርባ ምንጭ ከነማ ቀላል ፉክክር ይጠብቀዋል ተብሎ አይታሰብም። ጨዋታው ግን ማራኪ እንደሚሆን ይጠበቃል።

 

 

 ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
abebe [663 days ago.]
 I do not like Saint George.

abebe [663 days ago.]
 I do not like Saint George.

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!