Recently Posted News
  17ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አራት ጎሎች ብቻ ተቆጥረውበት ተጠናቀቀ17ኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር አራት ጎሎች ብቻ ተቆጥረውበት ተጠናቀቀ
ሚያዚያ 26, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትናንት በተካሄዱ ስድስት ጨዋታዎችና ትናንት ተጀምሮ ዛሬ ረፋዱ ላይ በተጠናቀቀ አንድ ጨዋታ ቀጥሎ ውሎ አራት ቡድኖች ሲያሸንፉ ሶስት ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ከሰባት ጨዋታዎች አራት ጎሎች ብቻ የተቆጠሩበት ሳመንትም ሆኗል። 

ወደጨዋታዎቹ ዝርዝር ስንመለስ ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ያቀናውና የ12 ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አምበል ዳዊት እስጢፋኖስ ባስቆጠራት ጎል ተሸንፎ ተመልሷል። ከሶከር ኢትዮጵያ ባገኘነው መረጃ ለማወወቅ እንደቻልነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ማራኪ የኳስ ቅብብል የታየበትና በጊዮረጊስ የጎል ሙከራ የበላይነት የነበረበት ጨዋታ ነበር። ጊዮርጊሶች ያገኟቸውን በርካታ የጎል ሙከራዎች ወደ ጎልነት የሚቀይር አጥቂ ቢያገኙ ኖሮ ነጥብ ይዘው ሊመለሱበት የሚችሉበት ጨዋታ እንደነበርም በስፍራው የተገኙ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ተናግረዋል። ድሉን ተከትሎ ድሬዳዋ በ25 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በ17 ጨዋታ ሶስት ጊዜ ብቻ የተሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ36 ነጥብ አሁንም በደረጃው አናት ላይ ተምጧል። 

ወደ አርባ ምንጭ ያቀናው መከላከያ እና ወደ ጎንደር ያቀናው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎል ማስቆጠር ሳይችሉም ሳይቆጠርባቸውም ባዶ ለባዶ በሆነ ተመሳሳይ ውጤት አጠናቀዋል። በቅርቡ ዋልያዎቹን በጊያዊነት ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቀው ገብረመድኅን ሀይሌ የሚያሰለጥነው መከላከያ በ21 ነጥብ አስረኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ንግድ ባንክ በበኩሉ በ22 ነጥብ ዘጠንኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከንግድ ባንክ ጋር ነጥብ የተጋራው ዳሽን ቢራ በ18 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ላይ ሲረጋ አርባምን ከነማም በተመሳሳየ ነጥብና የጎል ክፍያ 11ኛ ደረጃን እንደያዘ ቀጥሏል።

ሀዋሳ ከነማ በድጋሚ በሜዳው ነጥብ የጣለውም በትናንቱ የሊጉ መርሃ ግብር ነው። የውበቱ አባተ ቡድን በሜዳው ወላይታ ድቻን አስተናግዶ ያለ ጎል አቻ ተለያይቷል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ነጥቦችን ሰብስቦ የነበረው ሀዋሳ ከነማ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቶ በመውጣት የአሸናፊነት ጉዞው እንዲገታ አድርጓል። ከአቻ ውጤቱ በኋላ በተሰራው የደረጃ ሰንጠዥ ወላይታ ድቻ 26 ነጥቦችን ይዞ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከነማ በበኩሉ በ24 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

ትናንት ከቀትር በኋላ ተጀምሮ ዛሬ ረፋዱ ላይ የተጠናቀቀው የሲዳማ ቡና እና የሃድያ ሆሳዕና ጨዋታ በሲዳማ ቡና አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በከባድ ዝናብ ምክንያት የተቋረጠውን ጨዋታ ዛሬ እንዲቀጥል ሲደረግ ለሲዳማ ቡና በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያውን ሙሉ ሶስት ነጥብ ያስገኘች ጎል ያስቆጠረው ሳውሬል አልሪሽ ነው። ሲዳማ ቡና ባለፈው ሳመንት ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ሲጫወት በተመሳሳይ ከባድ ዝናብ በመጣሉ ጨዋታው በማግስቱ እንዲቀጥል ተደርጎ ነበር የተጠናቀቀው። የይርጋለሙ ክለብ በ23 ነጥብ ስምንተኛውን ደረጃ ሲይዝ ሀድያ ሆሳዕና ግን ሰባት ነጥብ ብቻ ይዞ 14ኛ ደረጃን በብቸኝነት ተቆጣጥሮታል።

አዲስ አበባ ስታዲየም ከቀትር መልስ ያስተናገደው የደደቢትና አዳማ ከነማ ጨዋታ በደደቢት አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በመሸነፉ የውጤት ደዌ ውስጥ ለቆየው ደደቢት የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው ከጉዳት በቅርቡ ያገገመው ዳዊት ፈቃዱ ነው። ውጤቱን ተከትሎ ደደቢት በ29 ነጥብ አዳማ በ27 ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ሊይዙ ችለዋል።

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ የተካሄደው አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና ኤሌክትሪክን ከአመሻሹ 11፡30 የገጠመበት ነው። ዋና አሰልጣኙ በህመም ምክንያት ቡድናቸውን ባልመሩበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ በተመሳሳይ አንድ ለባዲ ያሸነፈበትን ውጤት አስመዝግቧል። ቡና ወሳኝ አጥቂውን ለሶስት ሳምንታት በጉዳት እንዲያጣ በተገደደበት ጨዋታ ጋቶችፓኖም በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሮለታል። ኤሌክትሪክ ሁለተኛው ዙር ከተጀመረ በኋላ አንድም ጊዜ አላሸነፈም አንድም ጎል አላስቆጠረም። ቡና በ27 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤሌክትሪክ በነበረበት 13ኛ ደረጃ ተረጋግቶ ተቀምጧል።

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!