Recently Posted News
  የአርሴናሉ የቀድሞ ዝነኛ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ መጣ
ግንቦት 03, 2008

የአርሴናሉ የቀድሞ ዝነኛ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ መጣ

ቆንጂት ተሾመ ለኢትዮፉትቦል

በእንግሊዙ አርሴናል የእግር ኳስ ክለብ ታሪክ “አይረሴ” የሚባል ምርጥ ውጤት ያስመዘገበው ቡድን አባል ነው፡፡ በክለቡ ወርቃማ ዘመናት ለቡድኑ ውጤት የጎላ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከልም አንደኛው ነው፡፡ አሁን ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር በመምጣት ለሀገሪቱ እግር ኳስ እድገት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ሆኗል፡፡ ለሁለት ቀናትም ጉብኝት በማድረግ ከኢትዮጵያና የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ጋር በቅርበት ይተዋወቃል እንግሊዛዊው ማርቲን ኩዌን፡፡

አርሴናል በ2004 አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ የሊጉን ዋን ባነሳበት ወቅት የቡድኑ አባል የነበረው ኩዌን በተለይ ከእነ ቶኒ አዳምስ ዊንተርበርን እና ሊ ዲክሰን ጋር የነበረው የተከላካይ መስመር ጥምረት በክለቡ ታሪክ ከሚነሱ ስኬታማ ውህደቶች ተጠቃሽ ነው፡፡

ማርቲን በስድስት ወራት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ የቀድሞ የአርሴናል ተጫዋቾች ከሬይ ፓርሎር ቀጥሎ ሁለተኛው ሲሆን፣ በቀጣይ ጊዜያትም መሰል የአርሴናል ኮከቦች የአትሌቶች መፍለቂያ ወደ ሆነችው ምድር እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡ ይህን መንገድ ያመቻቸው ደግሞ ዳሸን ቢራ ፋብሪካ ነው፡፡ ዳሸን ቢራ ከአርሴናል ኮከቦችንና ባለሞያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ማድረግ ድርጅቱ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር በተፈራረመው ስምምነት አንደኛው አካል ነው፡፡ ይህም በዳሸን ክለብና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ የእግር ኳስ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡

ፋብሪካው ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሀን በላከው መረጃ ላይ እንዳስታወቀውም የማርቲን ኩዌን የኢትዮጵያ ጉዞ የሀገሪቱን የእግር ኳስ ልማት ለማገዝ የሚያስችል ነው፡፡ የቀድሞው ተጫዋች ለሁለት ቀናት በሚኖረው የኢትዮጵያ ቆይታም በአዲስ አበባና በጎንደር ጉብኝቶችን ያደርጋል፡፡

የማርቲን የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት የዳሸን ቢራ ፋብሪካ መቀመጫ በሆነው በጎንደር ከተማ የሚጀመር ሲሆን፣ የተለያዩ ታሪካዊ መስህቦችን በመዘዋወር ይመለከታል፡፡ የጎንደር ጉብኝቱ ከኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ታሪኮችና እሴቶች ጋርም በቅርበት የሚተዋወቅበት አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዳሸን ቢራ የገንዘብ ድጋፍ በጎንደር ከተማ የተገነባውን የእግር ኳስ ሜዳ የሚመረቅበት ልዩ ስነስርአት በክብር እንግድነት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ከከተማዋ ታዳጊ የእግር ኳስ ሰልጣኞችን በማግኘት ማበረታታት የጉብኝቱ አንደኛው አካል ነው፡፡

የሁለተኛው ቀን የማርቲን ኮዌን ጉብኘት በአዲስ አበባ ሲሆን፣ በዋናነትም ነገ ሀሙስ በብሔራዊ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኞችን መጎብኘትና ማነቃቃት ነው፡፡ በወቅቱም የኢትዮጵያ ጉብኝቱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ማርቲን ኩዌን በአሁኑ ወቅት የስካይ ስፖርት ቴሌቪዥን ጣቢያ የእግ ኳስ ተንታኝ ሆኖ እየሰራ ሲሆን ከስምንት ወራት በፊት ስለ ቀድሞ ክለቡ አርሴናል ተጠይቆ ሲናገርም በዚህ ዓመት የሊጉን ዋጫ እንደማያነሳ መተንበዩ በርካቶችን ያነጋገረ ክስተት ነበር፡፡

 

 

 

 


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
kena Duguma [615 days ago.]
 yamerele

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!