Recently Posted News
  ቡና በደደቢት ላይ ሲነግስ ጊዮርጊስ የሆሳዕናን የቁልቁለት ጉዞ አፋጠነ ሳዲቅ ሴቾ የዓመቱ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሃትሪክ ባለቤት ሆነቡና በደደቢት ላይ
ግንቦት 06, 2008

ቡና በደደቢት ላይ ሲነግስ ጊዮርጊስ የሆሳዕናን የቁልቁለት ጉዞ አፋጠነ

ሳዲቅ ሴቾ የዓመቱ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሃትሪክ ባለቤት ሆነ

በይርጋ አበበ

ትናንት በተካሄዱ ሰባት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች አምስቱ በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ ሁለት ጨዋታዎች በኣቻ ውጤት ተጠናቀዋል። ወደ ሆሳዕና ያቀነው የ12 ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮንና የዚህ ዓመት የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሳላዲን ሰይድ ሁለት ጎሎች ሃድያ ሆሳዕናን አሸንፎ ተመልሷል። ሳላዲን ቅዱስጊዮርጊስን በድጋሚ ከተቀላቀለ በኋላ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ሶስት አደረሰ ማለት ነው። ፈረሰኞቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 40 በማድረስ አሁንም በመሪነቱ ላይ ሲቀመጡ ሃድያ ሆሳዕናዎች ወደማይቀረው ወራጅነታቸው የሚያመሩ ይመስላል።

 አዲስ አበባ ላይ ከአመሻሹ 11፡30 ላይ የተገናኙት ቡና እና ደደቢት ነበሩ። በውጤቱም ቡና በሳዲቅ ሴቾ ሶስት ጎሎች ታግዞ በደረጃው ሰንጠረዥ ሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠበትን ውጤት አስመዘገበ። ዋና ጎል አዳኙን ያቡን ዊሊያምን በጉዳት በማጣቱ የአጥቂ ችግር አለበት ተብሎ ሲታማ የቆየው ኢትዮጵያ ቡና ለረጅም ወራት ጎል ማስቆጠር ባለመቻሉ ሲተች በነበረው ሳዲቅ ሴቾ ሃትሪክ ደረጃውን ከፍ ሲያደርግ በመጀመሪያው ዙር በደደቢት ደርሶበት የነበረውን ሽንፈትም ማወራረድ ችሏል። በውድድር ዓመቱም ሃትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሆኗል። ለሳዲቅ ሶስተኛ ጎል አምበሉ መስዑድ መሀመድ የነበረው ድርሻ ከፍተኛ ሲሆን ከደጋፊውም አድናቆት ተችሮታል።

የጥቁር ቀበቶ እና በቀለም ትምህርት ደግሞ የመጀመሪያ ድግሪ ባለቤት የሆነው ሳዲቅ ከአምስት ቀናት በፊት ክለቡ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በተጫወተበት ዕለት ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ ሲያሳይ ታይቶ ነበር። በወቅቱም አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ተጫዋቹ ወደ ሚፈለገው ደረጃ ባይደርስም መሻሻል እያየሁበት ነው ብለው ተናግረው ነበር። ሳዲቅም አሰልጣኙን አላሳፈራቸውም በደደቢት ላይ ሃትሪክ ሰርቶ አንድ ጎል ደግሞ ያላግባብ በዳኛ ስህተት ተሽሮበት ቨጨዋታው ላይ ነግሶ አምሽቷል።

በዚሁ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በተለይ የኢትዮጵያ ቡናዎቹ አብዱልከሪም መሃመድ፣ አህመድ ረሺድ፣ እያሱ ታምሩ እና አማኑኤል ዮሃንስ ከአምበሉ መስዑድ መሀመድ ጋር የነበራቸው ጥምረት አስደናቂ ነበር። ኤሊያስ ማሞም ቢሆን ምርጥ እንቅስቃሴ ሲያሳይ አምሽቷል። ከእነዚህ ተጫዋቾች በተጨማሪ ለተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች መረቡን አላስደፍር ያለው ግብ ጠባቂው ሀሪስተን ከተከላካዮቹ ኤፍሬም ወንድወሰን እና ወንድይፍራው ጌታሁን ጋር የነበረው ጥምረት መልካም ሆኖ ታይቷል።

በሌሎች ጨዋታዎች ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ አዳማ ከነማን አንድ ለዜሮ ሲያሸንፍ ጎሏን መሀመድ ሼርፈዲን ነው በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው። በቅርቡ ብሔራዊ ቡድኑን ለማሰልጠን የተዋዋለው ገብረመድኅን ሀይሌ መከላከያን ይዞ ወደ ሀዋሳ ተጉዞ ሁለት ለባዶ ተሸንፎ ተመልሷል። ለውበቱ አባተ ቡድን ጎሎቹን ተከላካዩ ሙጂብ ቃሲም እና ወጣቱ አጥቂ ፍርዳወቅ ሲሳይ ናቸው ያስቆጠሩት።

የመውረድ ስጋት ውስጥ የገቡት አርባምንጭ ከነማ እና ኤሌክትሪክ ያደረጉትን ጨዋታ ባለሜዳው አርባምንጭ ሶስት ለባዶ በማሸነፍ ደረጃውን በአንድ ማሻሻል ችሏል። ለጋሞጎፋ ዞኑ ክለብ ተሾመ ታደሰ ሁለቱን ሲያስቆጥር ቀሪያን ሴሴ ሀሰን በራሱ ጎል ላይ አስቆጥሮለታል። ሲዳማ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይርጋለም ላይ ተጫውተው አንድ እኩል በመለያየት አንድ አንድ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ለሲዳማ አሪክ ሙራንዳ አስቆጥሮ መሪ ቢያደርግም ቀውላላው ተከላካይ ቶክ ጀምስ ባንክ ነጥብ እንዲጋራ ያስቻለች ጎል አስቆጥሯል።

ድሬዳዋ ከነማ አሁንም በሜዳው ያለመሸነፍ ግስጋሴው ገፍቶበታል። ትናንት ከቀትር መልስ ወላይታ ድቻን አስተናግዶ ባዶ ለባዶ ተለያይቷል። በዚህ ዓመት በሜዳው የሽንፈትን አስከፊነት ያልተጎነጨ ብቸኛው ክለብም እሱ ብቻ ሆኗል።


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!