Recently Posted News
  ሆሳዕና ሀድያ ከፕሪሚየር ሊጉ ሲወርድ የሊጉ መሪዎች ሁሉም ነጥብ ጣሉ
ግንቦት 14, 2008

በይርጋ አበበ

ትናነት ከቀኑ 9፡00 ሲሆን በሰባት የአገራችን የተለያዩ የክልል ከተሞች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተካሂዶባቸዋል። በሰሜን የጎንደሩ ፋሲለደስ ስታዲየም ዳሽን ቢራን ከኢትዮጵያ ቡና አገናኝቶ ከውዝግብና ከጠብ ጋር በታጀበ መልኩ ጨዋታው ተጠናቋል። የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በጠብ እንዲታጀብ ያደረገው የቡናው ሳዲቅ ሴቾ ያስቆጠራት ሁለተኛ ጎል ከጨዋታ አቋቋም ውጭ በመሆኗ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በረብሻ የተቋረጠው ጨዋታ ከ14 ደቂቃዎች በኋላ ቀጥሎ ተካሂዶ ሁለት እኩል በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል። ዳሽን ቢራ በኤዶም እና ይተሻ ግዛው አማካኝነት ሁለት ጊዜ መምራት ቢችልም ለቡና ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ጎሎችን ማስቆጠር የጀመረው ሳዲቅ ሴቾ ሁለቱንም የአቻነት ጎሎች አስቆጥሯል።

ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ያቀናው ቅዱስ ጊዮረጊስ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ አጠናቋል። በዚህ ውጤት መሰረት የወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ ለስምንት ተከታታይ ሳምንታት መረቡን ሳያስደፍር እንዲወጣ አድርጎታል።በተከታታይ የሽንፈት ጽዋን መጎንጨት አመሉ እየሆነ የመጣው ደደቢት ትናንትናም ወደ አርባ ምንጭ ተጉዞ ሁለት ለአንድ ተሸንፎ ተመልሷል።

ሆሳዕና ላይ የተገናኙት ንግድ ባነክ እና ሀድያ ሆሳዕና በፍሊፕ ዳውዝ ሁለት ጎሎች ንግድ ባንክ ባለሜዳውን አሸንፎ ተመልሷል። ሀድያ ሆሳዕናም በንግድ ባነክ መሸነፈን ተከትሎ ወደነበረበት ብሔራዊ ሊግ ተመልሷል። በቀጣዩ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ከማይወዳደሩ ክለቦች አንዱ መሆኑን በጊዜ አረጋግጧል።

ሀዋሳ ከነማ በሜዳው ኤሌክትሪክን አስተናግዶ ሶስት ለሁለት አሸንፎ ሸኝቶታል። አስቻለው ግርማ  አንዷን እና ፍርዳወቅ ሲሳይ ሁለት  ጎል ለሀዋሳ ከነማ ሲያስቆጥሩ ፒተር ንዋድኬ እና ደረጀ ሀይሉ ለኤሌክትሪክ ጎሎችን አስቆጥረዋል። ድሉን ተከትሎ ሀዋሳ ነጥቡን 30 በማድረስ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ተሸናፊው ኤሌክትሪክ በ22 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በቅርቡ የዋልያዎቹ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ በዋና አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የተመረጠው ዘላለም ሽፈራው የሚያሰለጥነው ሲዳማ ቡና በሜዳው አዳማ ከነማን አስተናግዶ በበረከት አዲሱ ብቸኛ ጎል አንድ ለባዶ አሸንፏል። ብሔራዊ ቡድኑን ለማሰልጠን የተመረጠው ገብረመድህን ሀይሌ ቡድኑን ይዞ ወደ ድሬዳዋ አቅንቶ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ሁለት እኩል ተለያይቶ ተመልሷል። ለድሬዳዋ ጎሎቹን በላይ አባይነህና ፉአድ ኢብራሂም ሲያስቆጥሩ ለመከላከያ ደግሞ በሀይሉ ግርማ እና መሀመ ናስር አስቆጥረዋል።

እስከ ትናነት ምሽት ድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ከአንደኛ እስከ አራተኛ የነበሩት ክለቦች በሙሉ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ያሸነፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባነክ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባሳለፍነው ሳመንት አራተኛ ደረጃን ይዞ የነበረው ደደቢት በ29 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሊጉን ከላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ44 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ35 እና አዳማ ከነማ በ33 ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን ሲይዙ ዳሽን ቢራ በ23 ኤሌክትሪክ በ22 እና መውረዱን ያረጋገጠው ሀድያ ሆሳዕና በ7 ነጥብ ከ12ኛ እስከ 14ኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል።

 

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name) [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [66 days ago.]
 arachni_text)

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!