Recently Posted News
  ኢትዮጵያ ቡና በወቅታዊ የደጋፊዎች ጉዳይ ላይ ነገ መግለጫ ይሰጣል
ግንቦት 18, 2009

በይርጋ አበበ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖውን እያሳደረ ያለው የደጋፊዎች ስነ ምግባር እና እሱን ተከትሎ እየደረሰ ያለው የንብረትና የአካል ጉዳት ነው። ይህ እንደ ካንሰር በእግር ኳሱ ላይ የተጋረጠው አደጋ በተለይ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ክለቦች እና ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ሂደው ጨዋታቸውን በሚያደርጉ ክለቦች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ሄዷል። ለአብነት ያህልም በአዳማ በቦዲቲ በአርባ ምንጭ እና በጎንደር የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከተጋጣሚ ቡድን ደጋፊዎች ጋር የሚፈጥሯቸው እሰጣገባዎች ይጠቀሳሉ።

ባለፉት ሰባትና ስምንት ዓመታት የችግሩን አሳሳቢነት ችላ ብሎ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሁንም የችግሩ አሳሳቢነት የገባው አይመስልም። ምክንያቱም በቅርቡ በጎንደር ከተማ ዳሽን ቢራ እና ኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሜዳ ላይ በአቻ ውጤት ቢጠናቅቅም ከሜዳ ውጭ ግን በጨዋነት የተጠናቀቀ ጨዋታ ሊሆን አልቻለም። የሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች በፈጠሩት አምባጓሮ በርካታ ዜጎች በአካላቸው ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ይህ የደጋፊዎች ግጭት በሁለቱ ክለቦች ቀጣይ ግንኙነትም ሆነ በአገሪቱ እግር ኳስ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ጠባሳ በቀላሉ መታለፍ የማይኖርበት ሲሆን ፌዴሬሽኑም አጥፊውን አጣርቶ ተመጣጣኝ እና ለእግር ኳሱ ይበጃል የሚለውን ውሳኔ ሊያሳልፍ የሚገባው ይሆናል። ዳሽን ቢራ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ለሁለት የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ለግጭቱ ምክንያቱ “የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በእኛ ክለብ እና በፋሲል ከነማ ክለብ መካከል መለያየትን የሚፈጥር ስድስብ በመሳደባቸው ነው” ሲል መግለጫ ልኳል። ሆኖም በቡና በኩል በይፋ ባይወጣም በውስጥ ባገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው ሁለቱ ክለቦች ሲጫወቱ ቡና ሁለተኛዋን ጎል አግብቶ አቻ ሲሆን የዳሽን ቢራ ደጋፊዎች በዳኛው ላይ በወረወሩት ቁስ ዳኛውን መፈንከታቸውን አስታውቀው የግጭቱ መጀመሪያ ከጨዋታው መጠናቀቅ በፊት እንደሆነ አሳውቀዋል።

በእነዚህና ሌሎች ተያያዥ የወቅቱ የደጋፊዎች አመል ዙሪያ ኢትዮጵያ ቡና ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በደሳለኝ ሆቴል መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ዝርዝሩን ከመግለጫው በኋላ ይዘን እንመለሳለን።

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Gezegeta [635 days ago.]
  አይዞኝ ዳሽኖች ዘንድሮ አይን ያወጣ እገዛ ከፌዴሬሽንና ከዳኛ ለቡላ ገለባ እየተመለከትን ነው ። ዱርዬው ቡላ ገለባ ወደ ሜዳ ገብቶ የሚጫወተው በ 12 ተጫዋቾች ከዳኛና ከፌዴሬሽኑ ጋር በመሆን ነው ። ለዛም እኮ ነው በሚገርም ፍጥነት penality and offside የሆኑ ኳሶችን እንዲያስቆጥሩ እየተፈቀደላቸው ከወራጅ ቀጠና ከፍ ያደረጓቸው ። ምን እሱ ብቻ ያለ ህግና ያለ ፈቃድ ያልተመዘገበን ተጫዋች ባሻቸው ሰዓት በማስገባት እያሰለፉ ሲያጫውቱ ከፌዴሬሽኑ አንዳችም ቅጣት አይደለም ማስጠንቀቂያ እንኳን አልተሰጣቸውም ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ቡላ ገለባ ደጋፊ ባለጌ ጋጠወጥ ስድ ድንጋይ ወርዋሪ ተሳዳቢ የለም ። አ.አ ላይ ስድብ የለመደች ምላስ ጎንደር ላይ ዋጋዋን አግኝታ ተመልሳለች ። የቡላ ገለባን ብልግና ፌዴሬሽኑ ዳኞች የስፖርት ተመልካቹ ጭምር የሚያውቀው ነገር ነው ። አመራሩ ፍንዳታ...+..ተጫዋቹ ፍንዳታ..+...ደጋፊው ፍንዳታ የሆነ ፍንዳታ ክለብ ቢኖር = ቡላ ገለባ ወይም ድንጋይ ከነማ የተባለ ክለብ ቡና ነው !

daig dawit [608 days ago.]
 አሪፋ ነው

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!