Recently Posted News
  የማለፍ እድሉን በሌሎች ትከሻ ላይ የጣለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የሌሴቶ ጨዋታ
ግንቦት 25, 2009

በይርጋ አበበ

ለጋቦኑ የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ከጠንካራው የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን እና ከደካማዎቹ ሌሴቶ እና ሲሸልስ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ነጥብ እና አምስት የጎል እዳ የማለፍ እድሉን አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቶታል። ብሔራዊ ቡድኑ በተለይ ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ነጥብ መጣሉ በርካቶችን ያስገረመ ሲሆን ከዚህ የባሰው ደግሞ አልጄሪያ ላይ በአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ሰባት የጎል ናዳ ወርዶበት መመለሱ የብሔራዊ ቡድኑን ተስፋ ያጨለመ ሲሆን የእግር ኳስ ቤተሰቡን አንገትም ያስደፋ ክስተት ነበር።

ለዚህ ሁሉ የብሔራዊ ቡድኑ ውድቀት የመጀመሪያ ተጠያቂ የነበሩትን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን በእግር ኳስ ቤተሰቡ እና በመገናኛ ብዙሃን ጫና ከኃላፊናቸው ያስነሳው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በምትካቸው አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌን መሾሙ ይታወቃል። አሰልጣኝ ገብረመድኅን የብሔራዊ ኃላፊነቱን ከተቀበሉ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁትም “በአር ጊዜ ታዕምር መስራት ባንችል እንኳ አንገቱን የደፋውን የእግር ኳስ ቤተሰብ እንዲነቃቃ ማድረግ እንችላለን” ሲሉ መናገራቸው ብሔራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ዘመን ምን ያህል እንደወደቀ አመላካች ነው።

አሰልጣኝ ገብረመድኅን በመግለጫቸው አያይዘውም “የማለፍ እድላችን በእኛ ማሸነፍ እና በሌሎች ምድብ የሚገኙ ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው ቡድኖችን መሸነፍ እንጠብቃለን። የመጀመሪያውን የቤት ስራ ለመስራትም እኛ በቀሪዎቹ ጨዋታዎቻችን አጥቅተን በመጫወት ለማሸነፍ እንሰራለን” ሲሉ ተናግረዋል። ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ ሲያዘጋጁ የቆዩትና በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደረጉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን “የወዳጅነት ጨዋታ ለማካሄድ በዝግጅቱ ታሳቢ ተደርጎ ነበር። ፌዴሬሽኑም ይህን ለማሳካት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም። እኔ ለምን አልተሳካለትም ብዬ አልከፋም ሆኖም የወዳጅነት ጨዋታ ብናገኝ ኖሮ መልካም ነበር” ሲሉ ገልጸዋል። በዝግጅት ወቅት የቡድኑ ተጫዋቾች ያሳዩት ተነሳሽነት አስገራሚ መሆኑን የገለጹት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሲሆኑ አምበሉ ሳላሃዲን ሰይድ በበኩሉ ሜዳ ውም ሆነ ሜዳ ውስጥ የሚፈቃቀር ስብስብ አለን ሲል ተናግሮ ነበር።

የቡድኑ የመጀመሪያ አምበል ሳላዲን ሰይድ በመጎዳቱ እና ሁለተኛው አምበል ስዩም ተስፋዬ ደግሞ በፓስፖርት ጉዳይ ምክንያት ወደ ሌሴቶ የማያመራ ከሆነ ቡድኑን ሶስተኛው አምበል ጌታነህ ከበደ እንደሚመራው አሰልጣኙ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በተያያዘ ዜና የፓስፖርት ጉዳይ ሳያልቅለት በመቅረቱ ከቡድኑ ውጭ ሊሆን የነበረው የሀዋሳ ከነማው ተከላካይ ደስታ ዮሃንስ በመጨረሻ ወደ ሌሴቶ ማቅናቱን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። ለብሔራዊ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የመመረጥ እድል ያገኘው የመስመር ተካላካዩ በአዚህ ዓመት ከሀዋሳ ከነማ ጋር ስኬታማ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ወደ ካናዳ ለመሄድ በኬኒያ የሚገኘውን የካናዳ ኤምባሲ የቪዛ ጥያቄ አቅርቦ የነበረው ስዩም ተስፋዬ ፓስፖርቱ ኬኒያ በመሆኑ ከቡድኑ ጋር የሚያደርገው ጉዞ እንደተስተጓጎለ ሶከር ኢትዮጵያ ተጫዋቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም በበኩሉ የስዩምን ጉዳይ ተከታትሎ ለአንባቢያን የሚያቀርብ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሌሴቶ ዋና ከተማ ማሴሩ ይዟቸው የሄደው የቡድኑ አባላት እነዚህ ናቸው።

ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው እና አቤል ማሞ።

ተከላካዮች

አስቻለው ታመነ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ያሬድ ባዬህ፣ አህመድ ረሺድ፣ ደስታ ዮሃንስ እና የ2008 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ይሆናል ተብሎ የሚጠበወቅ አብዱልከሪም መሀመድ ናቸው።

አማካዮች

ኤሊያስ ማሞ፣ ታደለ መንገሻ፣ ሽመልስ በቀለ፣ ሽመክት ጉግሳ፣ አስራት መገርሳ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና ጋቶች ፓኖም ናቸው።

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ፣ ታፈሰ ተስፋዬ እና ዳዊት ፈቃዱ ናቸው።
የማለፍ እድሉን በሌሎች ትከሻ ላይ የጣለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የሌሴቶ ጨዋታ

ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
ESU YA HAWASSA LIG [627 days ago.]
 GOOD

Adem [618 days ago.]
 በጣምጡሩነዉ

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!