Recently Posted News
  አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን ተክትለው ደደቢትን እነማን ይቀላቀላሉ?
ሐምሌ 11, 2008

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌን ተክትለው ደደቢትን እነማን ይቀላቀላሉ?

በይርጋ አበበ

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድንና ዋናውን ብሔራዊ ቡድን አሰልጥነው ውጤት አልባ ጉዞ አድርገው ለስንብት የተዳረጉት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የቀድሞ ክለባቸውን ደደቢትን ተቀላቅለዋል። ከዚህ ቀደም ደደቢትን በቴክኒክ ዳይሬክተርነትና በአሰልጣኝነት ለሁለት ጊዜያት ማገልገል የቻሉት አሰልጣኙ ከዋልያዎቹ የስንብት ደብዳቤ ሲቆረጥላቸው በሩን ከፍቶ የተቀበላቸው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ ነው። አሰልጣኙ ሰማያዊ ለባሾቹን ማሰልጠን ሲጀምሩ የትኞቹን ተጫዋቾች ያዘዋውራሉ? የሚለው ነጥብ በበርካታ የስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ መወያያ ሆኗል።

በታዳጊ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ በዋናው ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ሲደርሱ የኮቺንግ ስታፋቸውን በራሳቸው ምርጫ ሲያዋቅሩ ሁለቱንም ጊዜያት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝንና ዓሊ ረዲን በረዳትነት መምረጣቸው ይታወሳል። ተጫዋች በመምረጥም ቢሆን በተለይ ዋናውን ብሔራዊ ቡድን በሚያሰለጥኑበት ወቅት ለራሳቸው አጨዋወትና ለሚሰጧቸው ትዕዘዛት በቀናነት ለመፈጸም ዝግጁ የሆኑ ተጫዋቾችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሲጠቀሙ ታይተዋል። ደደቢትን ሲያሰለጥኑ ከወጣት ቡድኑ ወደ ዋናው ቡድን እንዲያድግ ያደረጉትን ተከላካዩን ተካልኝ ደጀኔን ለብሔራዊ ቡድን የጠሩ ሲሆን እንደ ስዩም ተስፋዬ፣ ዳዊት ፈቃዱ፣ በረከት ይሳቅ እና ታሪክ ጌትነት አይነት ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድን ለመምረጥ የፈለጉትም ከልጆቹ ወቅታዊ ብቃት በዘለለ ከተጫዋቾቹ ጋር አብረው በመስራታቸው ልጆቹን ስለሚያውቋቸው በመሆኑ እንደሆነ በስፋት ሲነገር ቆይቷል።

አሰልጣኙ አሁንም ደደቢትን ለማሰልጠን ሲስማሙ ወደ ክለቡ የትኞቹን ተጫዋቾች ሊያዘዋውሩ ይችላሉ የሚለውን ሀሳብ በተመለከተ በበርካታ የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው ተጫዋቾች መካከል ሶስቱን ከዚህ በታች ዘርዝረናቸዋል።

1.      ጋቶች ፓኖም

እግር ኳስን በጉልበት የሚጫወተው ወጣቱ የኢትዮጵያ ቡና አማካይ ተከላካይ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ይወደዳል። የእግር ኳስ ቴክኒኩ ደካማ እንደሆነ የሚነገርለት ጋቶች በጨዋታ መሀል በተደጋጋሚ ጊዜ ግጭት የሚፈጥር ቢሆንም ለአሰልጣኝ ዮሃንስ አጨዋወት እና ትዕዛዝን ተቀብሎ ተግባራዊ በማድረግ በኩል የተወደሰ ነው።

በዚህም ምክንያት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሰማያዊዎቹን ስራ በይፋ ከመጀመራቸው በፊት ጋቶች ፓኖምን በክለባቸው መልበሻ ክፍል ማየት ይፈልጋሉ። ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አጭር የኮንትራት ውል ያለውን ጋቶችን ደደቢቶች የሚወስዱት ከሆነም በምትኩ አስራት መገርሳ የቡናን ካምፕ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

 

2.      ያሬድ ባዬህ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ ለተጫዋቾች ዝውውር እና ለአሰልጣኞች ደመወዝ ከሚከፍሉት ከአንድ እጅ እጣት በታች ክለቦች መካከል አንዱ ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ ነው። ባለፈው የውድድር ዓመት 40 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት ወደ ውድድር የገባው ዳሽን ቢራ ግን በዓመቱ መጨረሻ አርባ ጎል እንኳን ማስቆጠር ተስኖት ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱ ይታወቃል። ክለቡ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ተከትሎ ምናልባትም ሊፈርስ እንደሚችል እየተነገረ በመሆኑ በርካታ ታላላቅ ተጫዋቾቹ ወደ ሌሎች ክለቦች ያመራሉ።

ከእነዚህ የዳሽን ቢራ ታላላቅ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ወጣቱ ተከላካይ ያሬድ ባዬህ ሲሆን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የዚህ ተከላካይ አድናቂ ናቸው። ብሔራዊ ቡድን ሲያሰለጥኑ በተደጋጋሚ የመሰለፍ እድል የሰጡት ሲሆን በአጨዋታውም ደስተኛ እንደሆኑ ደጋግመው ተናግረዋል። የአሰልጣኙ ቀዳሚ ተመራጭ በመሆኑ እና ዳሽን ቢራ ወደ ታችኛው ሊግ የሚወርድ በመሆኑ ያሬድ ባዬህ በቀጣዮቹ ሳምንታት ወይም ቀናት ውስጥ የደደቢት ንብረት ሊሆን ይችላል።

 

3.      አስቻለው ግርማ

የቀድሞው የሱሉልታ ከነማ የመስመር ተጫዋች ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ቡናን በመልቀቅ ሀዋሳ ከነማን ተቀላቅሎ ነበር። ለሀዋሳ ከነማ ለአንድ ዓመት ብቻ መፈረሙን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ከኮንትራት ነጻ ሆኗል። ከሽመክት ጉግሳ ጋር ስምምነት እንደሌላቸው የሚነገርላቸው አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በብሔራዊ ቡድን ጠንቅቀው የሚያውቁትን አስቻለው ግርማን ለደደቢት ሊያስፈርሙት ይችላሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ሳሙኤል ሳኑሜ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ድርድር መጀመሩን ተከትሎ የሚፈጠረውን ክፍተት ለመድፈን የመከላከያውን ሙሉዓለም ጥላሁንን ወይም ከሀዋሳ ከነማ ጋር ስኬት አልባ ጉዞ ማሳለፉን ተከትሎ የትችት ናዳ እየወረደበት ያለውን በረከት ይሳቅን ወደ ደደቢት ሊያዘዋውሩ እንደሚችሉም ይገመታል። እጆቹ ኳስ መያዝ የሚከብዳቸው እየተባለ የሚተቸውን ታሪክ ጌትነትን ለመተካትም ከሙገር ሲሚንቶ ጋር ውሉን የጨረሰውን አቤል ማሞን ለማዘዋወርም ሳይከጅሉ እንዳልቀረ ተነግሯል።

ማስታወሻ፦ ከዚህ በላይ የተቀመጠው መዘርዝር በስፖርት አፍቃሪው እና በተወሰኑ ምንጮች የደረሱን መረጃዎች እንጂ የተረጋገጡ መረጃዎች አይደሉም።

 

 

 


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!