Recently Posted News
  የታላላቆቹ ክለቦች የሰሞነኛ ዝውውር ዜናዎች
ሐምሌ 25, 2008

የታላላቆቹ ክለቦች የሰሞነኛ ዝውውር ዜናዎች

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 ዓ.ም ተሳታፊ ክለቦች ቁጥር 16 ሲሆን ከአሁኑ 13ቱ ክለቦች ታውቀዋል። በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታተም ቀሪዎቹ ሶስት ክለቦች ይታወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም መሰረት ክለቦቹ ራሳቸውን የማጠናከር ስራ እየሰሩ ሲሆን ከአሁኑም የሚፈልጓቸውን ክለቦች በማስፈረም ላይ ይገኛሉ። ሰሞኑን ከተፈጸሙና ትልቅ ትኩረት ከሳቡ ዝውውሮች እና ጭምጭምታዎች መካከል የተመረጡትን ከዚህ በታች አቅርበናል።

አዳማ ከነማ

አዳማ ከነማ ኮከብ ተጫዋቹን ታከለ አለማየሁን በዓይን ጉዳት ምክንያት አገልግሎቱን የማያገኝ መሆኑ ለክለቡ ቤተሰብ ትልቅ መርዶ ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ኮከብ ተጫዋቾችን ከሌላ ክለብ በማዘዋወር ቡድን በማጠናከር ላይ ይገኛል። ከዚህ በፊት ዳዋ ሁጤሳን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያስፈረመው የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቡድን ሰሞኑን ደግሞ ክለብ አልባውን አዲስ ህንጻን ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። የተከላካይ መስመሩን ለማጠናከር ደግሞ ሙጂብ ቃሲምን ከሀዋሳ ከነማ ከነማ አስፈርሟል።

ከዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ኮንትራታቸው የተጠነቀቁትን ተጫዋቾች ያሰናበተ ሲሆን የመጀመሪያው ተሰናባች የሆነው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ዮናታን ከበደ ነው። ዘላኑ አጥቂ ከአዳማ ከነማ ጋር ለ18 ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀዋሳ ከነማ አቅንቷል።

ኢትዮጵያ ቡና

በዚህ የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ ከሚገኙ ክለቦች መካከል ግንባር ቀደሙ ኢትዮጵያ ቡና ነው። ቡና ከዚህ ቀደም ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ውላቸው ከተጠናቀቁት ተጫዋቾች መካከል ደግሞ ኤሊያስ ማሞን እና ኤፍሬም ወንድወሰንን ውል አድሷል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አምበሉን መስዑድ መሀመድን ውሉን እንዲያድስ እያግባባ ያለው ቡና የቀድሞውን አምበሉን ዳዊት እስጢፈፋኖስንም በድጋሚ ለማስፈረም እየሞከረ መሆኑን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ከዳዊት በተጨማሪ ደግሞ የዳሽን ቢራወን አማካይ አስራት መገርሳን እንዲሁም የደደቢቱን ሳሙኤል ሳኑሜን እና ከውጭ ክለቦች ጋር ሙከራ አድርጎ ያልተሳካለትን ፍሊፕ ዳውዝን ለማስፈረም እይተንቀሳቀሰ መሆኑንም ሰምተናል።

 

 

ቅዱስ ጊዮርጊስ

በዚህ የዝውውር መስኮት በሩን ዘግቶ እየሰራ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው ማለት ይቻላል። ያለፈው ዓመት የሁለትዮሽ ዋንጫ ባለቤቱ እና የ80 ዓመቱ አንጋፋ ክለብ በዚህ የዝውውር መስኮት ያነሳበተው እንጂ ያስፈረመው ተጫዋች እስካሁን ይፋ አልሆነም። ዳዋ ሁጤሳን ለአዳማ ከነማ የሸጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ መስመሩን በኳስ ፈጣሪ ተጫዋቾች ለማጠናከር ካለው ፍላጎት የተነሳ ከአርባ ምንጩ ታደለ መንገሻ እና ከመከላከያው ፍሬው ሰለሞን ጋር ስሙ ሲያያዝ ቢቆይም እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም።   ኮንትራቱ የፊታችን ጥቅምት የሚጠናቀቀው ተከላካዩ አይዛክ ኢሴንዴም እስካሁን ውሉን አለማደሱን ሰምተናል።

ሌሎች

ሀዋሳ ከነማ እንደ አስቻለው ግርማ እና ሙጂብ ቃሲም አይነቶቹን ቋሚ ተሰላፊዎቹን በዚህ የዝውውር መስኮት አጥቷል። ለዓመታት የክለቡ ምልክት ሆኖ የቆየውን ሙሉጌታ ምህረትንም በጡረታ ያጣ መሆኑ ከተረጋገጠ ወራት ተቆጥረዋል። ግብ ጠባቂው ዮሀንስ በዛብህም ቢሆን ማረፊያውን ኢትዮጵያ ቡና አድርጓል።

ከላይ የተጠቀሱትን ተጫዋቾች ያጣው የውበቱ አባተ ቡድን ያሬድ ዝናቡን ከደደቢት እንዲሁም ዮናታን ከበደን ከአዳማ ከነማ አስፈርሟል። ሌሎች ተጫዋቾችንም ማስፈረም የቻለ ሲሆን ፍሬው ሰለሞንንም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ተሻምቶ ለማስፈረም ከጫፍ መድረሱን ሰምተናል። አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነ ማሪያም የቀድሞውን የቡና አማካይ ዮናስ ገረመውን ለአንድ ዓመት አስፈርሟል። ዮሃንስ ሳህሌን አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረው ደደቢት በበኩሉ እስካሁን ኤፍሬም አሻሞን ከንግድ ባንክ ያስፈረመ ሲሆን ምናልባትም ያሬድ ባዬህን እና ጋቶች ፓኖምን ሊያስፈርም ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። ወጣቱን ተከላካይ ተካልኝ ደጄኔን እና ያሬድ ዝናቡን ደግሞ ለሀዋሳ ከነማ አሳልፎ ሰጥቷል።

 

 


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!