Recently Posted News
  ሊጉን ለማድመቅ የጓጉት አራቱ አዲስ ፊቶች
ነሐሴ 04, 2008

ፕሪሚየር ሊጉን ለማድመቅ የጓጉት አራቱ አዲስ ፊቶች

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ 16 ክለቦችን ለመሳተፍ እቅድ መያዙን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕናን እና ዳሽን ቢራን ወደ ታች አውርዶ ሁለት ክለቦችን ከአማራ ክልል አንድ ክለብ ከኦሮሚያ እና አንድ ሌላ ክለብ ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲያድጉ አድርጓል። ሊጉን የተቀላቀሉት አራቱ ክለቦች ማለትም ፋሲል ከነማ ወልድያ ከነማ ጅማ አባ ቡና እና አዲስ አበባ ከነማ ሲሆኑ እነዚህ ክለቦች ለፕሪሚየር ሊጉ ምን አዲስ ለውጥ ይዘው መጥተዋል ለሚለው ጥያቄ ስለ ክለቦቹ የተለየ ኳሊቲ ከዚህ በታች አቅርበናል።

ፋሲል ከነማ

ከአዲስ አበባ 760 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው እና የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነበረችው ጎንደር የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ መገኛ ናት። ክለቡ ፕሪሚየር ሊጉን በዚህ ዓመት ይቀላቀል እንጅ እግር ኳስን የተቀላቀለው ግን ከ46 ዓመታት በፊት ነበር። ወደ ላይኛው ሊግ መውጣት ብርቅ ሆኖበት የኖረው የጎንደሩ ቡድን በዚህ ዓመት ሊጉን የተቀላቀለ ይሁን እንጂ ላለፉት አራት ዓመታት በተከታታይ የምድቡ መሪ ሆኖ ዓመቱን ቢጨርስም የብሔራዊ ሊግ ክለቦች የመዝጊያ ውድድር ወይም ቶርናመንት ላይ በለስ አልቀናው እያለ ወደ ላይ ሳያድግ በነበረበት እንዲቆይ ሲገደድ ቆይቷል። ዘንድሮ ግን ክለቡ የረጅም ዓመታት ህልሙን እውን ማድረግ ችሏል። ፋሲል ከነማ በቀጣዩ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ስለሚኖረው ቆይታ ሙያዊ ምልከታቸንን ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

የክለቡ ጠንካራ ጎን

ክለቡን ላለፉት አምስት ዓመታት አሰልጣኘ ዘማሪያም ሲያሰለጥነው ቆይቷል። በቅርቡ ከሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ይሳቅ ጌታሁን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው አሰልጣኙ “ከክለቡ የመሰናበት ስጋት ያድርብሃል ወይ” ብሎ ሲጠይቀው “200 ፐርሰንት እንደማልሰናበት እርግጠኛ ነኝ” ሲል በልበ ሙሉነት ተናግሯል። ይህ አሰልጣኝ በክለቡ ስለሚኖረው ቆይታ እርግጠኛ ሆኖ የተናገረው በሌላ በምንም ምክንያት ሳይሆን የሚሰራውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ብቻ ነው። የፋሲል ከነማ ወይም በቅጽል ስማቸው “አጼዎቹ” የመጀመሪያው ጠንካራ ጎናቸው ብቃት ያለው አሰልጣኝ መያዛቸው ነው።

ሌላው የክለቡ ጥንካሬ ክለባቸውን ደግፈው የማይጠግቡ ሁልጊዜም ከክለባቸው ጀርባ ደማቅ ቀይና ነጭ ማሊያቸውን ለብሰው የሚያበረታቱት ደጋፊዎቹ ናቸው። ክለቡ በጎንደር ከተማ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የአማራ ክልል የሚወደድ በመሆኑ ህዝባዊ ክለብ ነው። የጎንደሮቹ ደጋፊዎቹም ካላቸው ጠንካራ አደጋገፍ በተጨማሪ ቡድናቸውን በገንዘብ ለማጠናከር ከኪሳቸው እስከ አስተሳሰባቸው ያላቸውን ለማዋጣት የማይሰስቱ ናቸው። ይህ የክለቡ ትልቅ ጥንካሬ ነው።

አጼዎቹ በቀጣዩ ዓመት ሊጉን ሲቀላቀሉ በመጡበት እግራቸው ወደ ታች እንዳይመለሱ ብርታት ይሆናቸዋል ተብሎ የሚታሰበው ክለቡ በጊዜ ፕሪሚየር ሊጉን በመቀላቀሉ በርካታ የፕሪሚየር ሊግ ልድ ያላቸውን ተጫዋቾች በዝውውር መስኮቱ ማስፈረሙ ነው። በዚህም ምክንያት ቡድኑን በጊዜ ማጠናከር የቻለው አሰልጣኝ ዘማሪያም ፕሪሚየር ሊጉ ሲጀመር ያለ ምንም መደነባበር ቶሎ ወደ ሪትም ሊገባ የሚችል የቡድን ስብስብ ይኖረዋል ማለት ነው።

የክለቡ ድክመቶች

ጎንደር ከአዲስ አበባ 760 ኪሎ ሜትር ከአዳማ 860 ኪሎ ሜትር ከሀዋሳ 900 ኪሎ ሜትር እንዲ እንዲህ እያልን ብንሄድ ፋሲል ከነማ በቀጣዩ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ለመወዳደር ከሜዳው ሲወጣ በ15 ጨዋታዎች ከ15 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ በአየር እና በመሬት ሊጓዝ ግድ ይለዋል። ክለቡ ጉዞውን በአየር ላይ የሚያደርግ ከሆነ የፋይናንስ ወጭውን የሚፈታተን ሲሆን በመኪና መንቀሳቀስን የሚመርጥ ከሆነ ደግሞ በተጫዋቾች አካል ብቃት ላይ መውረድ ያደርሳል። ይህ ርቀት አንድ በመካከለኛ ደረጃ ላይ ከሚገኝ የአዲስ አበባ ክለብ ጋር ሲነጻጸር አድቫንቴጅ እንዲወሰድበት ያደርገዋል።

አጼዎቹ ይህን አስበው በጊዜ መፍታት ከቻሉ በቀጣዩ ዓመት ሊጉን ከሚያደምቁት ጥቂት ክለቦች ማለትም ከወላይታ ድቻ ጅማ አባቡና ድሬዳዋ ከነማ ሀዋሳ ከነማ እና አዳማ ከነማ ጋር የሚመደቡ ይሆናል።

ከሊጉ የመውረድ እድል 1/500

የሊጉን ዋንጫ የማንሳት እድል 1/50

ይቀጥላል!!


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!