Recently Posted News
  ግምቶቹን ፉርሽ ያደረገው የአስራት መገርሳ ዝውውር ምክንያት
00, 0000

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በመብራት ኃይል እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለውና አሁንም እያሳረፈ ያለው አስራት መገርሳ ለኢትዮጵያ ቡና ይፈርማል ተብሎ ሰፊ ግምት ቢሰጠውም ለደደቢት መፈረሙ ታውቋል። አመለ መልካሙ እና ግዙፉ አማካይ ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ተከትሎ ማረፊያው ቡና እንደሚሆን ተጫዋቹም ሆነ ቡናዎች እምነታቸው የሰፋ ነበር። ሆኖም ተጫዋቹ ከቡናማዎቹ ይልቅ ሰማያዊ ለባሾቹን ምርጫው ያደረገበት ምክንያት ምን ይሆን? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተገቢ ስለሆነ ከዚህ በታች ያሉትን ነጥቦች እንመለከታለን።

የተሰላፊነት እድል

የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ለሚከታተል እግር ኳስ ተመልካች ሁሉ ግልጽ የሚሆነው ነገር ቢኖር አስራት መገርሳ ለኢትዮጵያ ቡና የመጫወት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ይህን ፍላጎቱንም ለክለቡ አመራሮችና ለሚቀርባቸው የቡና ሰዎች ተናግሯል። በተለይ የቡናው የህክምና ባለሙያ ይስሃቅ ሽፈራው እና አምበሉ መስዑድ መሀመድ ተጫዋቹ ለቡና እንዲጫወት ያደረጉትን ማግባባት አስራትም ተቀብሏቸው እንደነበረ ነገር ግን ከዳሽን ቢራ መልቀቂያ አለማግኘቱ ምክንያት እንደሆነ ከቡና የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። ይህ ሁሉ ለእውነት የቀረበ ግምት እያለ አስራት ግን የመጨረሻ ማረፊያውን ያደረገው ለ2005 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮናዎች ነው። ለዚህ ምክንያት ተደርጎ ከሚነሳው የእግር ኳስ ምክንያት አንዱ ከቡና ይልቅ በደደቢት ሰፊ የመሰለፍ እድል መኖሩን ተገንዝቧል ማለት ይቻላል።

ከሳምንት በፊት በኢትዮፉትቦል ዶትኮም ላይ የዚህ ጽሁፍ አንባቢ ስለ ቡና የዚህ ዓመት የተጫዋቾች ስብስብ ሲተነትን “ለአሰልጣኝ ኦሽኬ ፈታኙ ስራ የሚሆነው በመሃል ሜዳው ላይ ማንን አስቀምጠው ማንን በቋሚነት ለማሰለፍ ያስባሉ” የሚለው ነጥብ መሆኑን አስፍሮ ነበር። ኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ለአራት የአማካይ ቦታዎች 12 ተጫዋቾችን ይዟል። ከእነዚህ 12 ተጫዋቾች መካከል ደግሞ በተለይ ጋቶች ፓኖም መስዑድ መሃመድ ኤሊያስ ማሞ እና አስቻለው ግርማ በቋሚነት አሰላለፍ የሚጫወቱ እንደሚሆኑ ይገመታል። እንደ እያሱ ታምሩ እና ያቡን ዊሊያም በአጥቂ አማካይነት የመሰለፍ እድላቸው የሰፋ ነው። አስራት መገርሳ ደግሞ ከሚታወቅበት የአማካይ ተከላካይነት ሚና እና የአማካይ አቀጣጣይነት ተጫዋችነቱ ሲታይ በቡና ከእነዚህ ተጫዋቾች በተለይ ከመስዑድ ኤሊያስ እና ጋቶች ፓኖም ቀድሞ የመሰለፍ እድል ያገኛል ወይ የሚለው ጥያቄ አስራትን ሳይገፋው አልቀረም።

በአንድ ቦታ ላይ የሚጫወቱ ተጫዋቾች በቡና ከመብዛታቸው በተጨማሪ በደደቢት ደግሞ ቦታው ሰው አልባ ነው ማለት ይቻላል። ያሬድ ዝናቡ ለሁለት ዓመታት ያልተሳካ ጊዜ ከሰማያዊዮቹ ጋር ካሳለፈ በኋላ ወደ ደቡብ አቅንቶ ሃዋሳ ላይ ማረፊያውን አድርጓል። በደደቢት የተገፋው የያሬድ መርከብ መልህቁን ሀዋሳ ላይ ያሳረፈ መሆኑን ተከትሎ ከፈረሰው ዳሽን ቢራ የለቀቀው አስራት የደደቢትን የአማካይ ተከላካይ ቦታ በብቃት የመሸፈን እድሉ ሰፊ ነው።

የአስራቶች መገናኘት

ከዓመታት በፊት መብራት ኃይልን ለማሰልጠን ተስማምቶ ኮረንቲዎቹን ተቀብሎ የነበረው አስራት ኃይሌ ከክለቡ አመራሮች ከገጠሙት ፈተናዎች መካከል አንዱ አስራት መገርሳን ከስብስቡ እንዲቀንሰው የሚያሳስበው ትዕዛዝ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ሆኖም ካመነበት ጉዳይ ወደኋላ የማይለው ጎራዴው አስራት መገርሳ ከለቀቀ እሱም እንደሚለቅ በአቋሙ ጸና።  ሁለቱ አስራቶች በመብራት ኃይል አብረው የቆዩበት ጊዜ አጭር ቢሆንም የእግር ኳስ ህይወታቸው ግን የተቆራኘ ጥብቅ አንድነትን የፈጠረ ነው። በተለይ በአንድ ወቅት ከዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ የነበረው አስራት ኃይሌ በተለይ እንደ አስራት መገርሳ ሳላዲን ባርጌቾ ኡመድ ኡክሪ እና ፋሲካ አስፋው የእግር ኳ ስኬት ሀሴት እንደሚያደርግ ተናግሮ ነበር። አስራት መገርሳም ቢሆን በአንድ ወቅት ከአንድ የአገራችን መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የአስራት ኃይሌ ስልጠና ለቁም ነገር እንዳበቃው ተናግሮ ነበር።

ከላይ የተጠቀሰው የሁለቱ ግለሰቦች የእግር ኳስ ግንኙነት አሁን በድጋሚ እንዲገናኙ የሚያደርገውን እድል የፈጠረው ደደቢት ነው። ደደቢት ከወራት በፊት አስራት ኃይሌን ቴክኒክ ዳይሬክተር አድርጎ የቀጠረ ሲሆን አሁንም አስራት መገርሳ የቡናን ጥያቄ ወደ ጎን ብሎ ለደደቢት እንዲፈርም የአስራት ኃይሌ ተጽእኖ ሳይኖርበት አይቀርም። ይህ ደግሞ ወደ ፊት የሚታይ ይሆናል።

የጥቅማ ጥቅም ጉዳይ

ኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ እንደዘንድሮው የዝውውር መስኮት በተጫዋቾች ፊርማ ተሳትፎ አያውቅም ማለት ይቻላል። ክለቡ የተጫዋቾችን የዝውውር መስኮት ሪከርድ ለአራት ጊዜ መስበር የቻለ ሲሆን በተለይ ለአስቻለው ታመነ መስዑድ መሀመድ ኤሊያስ ማሞ እና ሳሙኤል ሳኑሚ የከፈለው ዝውውር እጅግ ከፍተኛ የሚባለ ገንዘብ ነው። ከእነዚህ ውድ ፈራሚ አራት ተጫዋቾች በተጨማሪ ተከላካዩን ኤፍሬም ወንድወሰንን ግብ ጠባቂውን ዮሃንስ በዛብህን አማካዩን አብዱልከሪም ሁሴንን እና መጠኑ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከፍሎ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ናቸው። የውል ኮንትራቱ ሊጠነቀቅ ስድስት ወራት ብቻ የቀረው አማካዩ ጋቶች ፓኖም ከቡና እንዳይለቅ በጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፍል የሚያውቀው ቡና ለአስራት መገርሳ ተጨማሪ ከፍተኛ ገንዘብ መክፈል የክለቡን ፋይናንስ የሚፈታተነው ሳይሆን እንደማይቀር አላጣውም።

ቡና ለአስራት መገርሳ ሊከፍለው ከሚችለው በላይ ደደቢት መክፈል በመቻሉ አስራት ደደቢትን ምርጫው ሊያደርግ ይችላል። ይህ መላምትም ወደ ፊት የሚታወቅ ነው የሚሆነው። ግን ከግምት በዘለለ እግር ኳሳዊ ምክንያት መሆኑ ግን ሊታወቅ ይገባል።


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
Duresa [528 days ago.]
 ቡና የተባለ ነቀርሳ ክለብ እያለ የኢትዮጵያ ፉትቦል ሰላም አይኖረውም አመራሩ ፍንዳታ ደጋፊው ፍንዳታ ተጫዋቹ ፍንዳታ ይህ ክለብ በ 2008 በየ ክፍለሃገሩ ሄደው ፀብ ጭረው ተጣልተው ነው ሲመለሱ የነበረው ዘንድሮስ ?!!! ያው ምንም የተለየ ነገር የሚኖር አይመስለኝም ምክንያቱም ለዘመናት እናውቃቸዋለን ቡናዎችን ድንጋይ መወርወር ውስጣቸው ነው ያለው !!!

Gezegeta [528 days ago.]
  9 why i hate Bulla Gellebba fc ?! this is my reason የቡና ደጋፊ እንዲህ ናቸው ሲሸነፍ ድንጋይ ወርዋሪ ባስ ሰባሪ ! ሲያሸንፍ አስቸጋሪ ! ፖሊስ ሲያይ ደንባሪ ! ለጨዋ ሰው ደባሪ ! ለግሩፕ ፀብ ተባባሪ ! ስራ የለ ቺክ አባራሪ ! ለቤተሰብ በጣም አስቸጋሪ ! የሰፈር ፀብ ጫሪ ! በዛ ላይ አጭበርባሪ ሰካራም በረንዳ አዳሪ ! አረቄ ቤት አስተባባሪ ! . ደግሞ በጣም ለፍላፊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲጫወት ለውጭ ደጋፊ !!!

ሙሌ [527 days ago.]
 ቡና የተባለ ክለብ እንደሚያስጠላኝ የሆነ አይሲሲ አሸባሪ የሆነ የመንደር የቀበሌ ቲም ነገር ነው ወይ ችለው አይፎካከሩ በየአመቱ ድንጋይ መወርወር ብቻ ፕሪምየር ሊጉ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የወረወራችሁት ድንጋይ ቢጠራቀም ኖሮ ስታዲየም ትሰሩበት ነበር !

Samiflex [527 days ago.]
 "የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ለሚከታተል እግር ኳስ ተመልካች ሁሉ ግልጽ የሚሆነው ነገር ቢኖር አስራት መገርሳ ለኢትዮጵያ ቡና የመጫወት ፍላጎቱ ከፍተኛ መሆኑ ነው " ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ኧረ ኢትዮ ፉትቦሎች shame on you ! ምን ለማለት ፈልጋችሁ ነው ግልፅ ድጋፍ እኮ ነው የሚያስመስልባችሁ favour እስቲ እውነቱን መሬት ላይ ስላለው እውነት እናውራ እውነት የትኛው ተጫዋች ነው ቡና ገብቶ ለመጫወት የሚደፍረው ምክንያቱም ቡና ገብቶ መጫወት ማለት መቃጠል መሰደብ መደብደብ ባጠቃላይ እራስ ላይ እባብ መጠምጠም ማለት ነው ታዲያ እውነት አስራት መገርሳ እነዚህን የምድር ላይ ስቃዮች ፍለጋ ነው ቡና ገብቶ መጫወት የሚፈልገው ኧረ ኢትዮ ፉትቦሎች ቡና ገብቶ ለመጫወትና ለማሰልጠን ማን ይደፍራል ምክንያቱም ቡና ሄዴክ የሆነ ክለብ ስለሆነ እኮ ነው አስራትም ለደደቢት የፈረመው :: ግን ይህ ዜና የጊዮርጊስ ቢሆን ኖሮ እንዴት ልትዘግቡት ነበር ምክንያቱም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሃገር ውስጥ ካሉ ክለቦች ቅድሚያ ለመጫወት የሚፈልገው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ እንደሆነ ለቡናዎች እራሱ ግልፅ የሆነ ነገር ነው ::

Mamush Koren - Sefer [526 days ago.]
 የሃዋሳ ከነማ ደጋፊ ነኝ ዘንድሮ ጥሩ ሆነን ቀርበን ለዋንጫ ነው የምንጫወተው መልካም እድል ለሃዋሳ ከነማ ቡድን :: በመቀጠል ፌዴሬሽኑ ስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ትልቅ ስራ መስራት ይጠበቅበታል እንደ ቡና ገበያ አይነት ባለጌ ጋጠወጥ ስድ መረን ደጋፊዎችን እሹሩሩ ማለቱን ማቆም አለበት :: ሁሉንም ክለቦች በእኩል አይን ማየትና ፍትሃዊ የሆነ ዳኝነት ለሁሉም ክለቦች መስጠት ይገባዋል ፌዴሬሽኑ :: ማንም ክለብ ከማንም አይበልጥምም አያንስምም ! ያለፈው አመት ብዙ ፍትሃዊ ያልሆኑ ጉዶችን አሳይቶን አልፏል :: 2008 እንደ ቡና አይነት ክለብ በዳኞች ፔናሊቲ እየታገዘ ከወራጅ ቀጠና ከፍ እንዲል የተደረገበት ዘመን ነበር :: ምን እሱ ብቻ ያልተገባ ተጫዋች እያሰለፉ ሲያጫውቱም ፌዴሬሽኑ ባላየ ሙድ አልፏቸዋል :: ይሄንን ነገር ግን ሌላ ክለቦች ያደረጉ ቢሆን ኖሮ ፌዴሬሽኑ ሳይውል ሳያድር ክለቦቹን ነጥብ ቀንሶና ቀጥጦ ነበር ክፕሪምየር ሊጉ የሚያባራቸው :: ቡና የተባለ ክለብ በ 2008 በየ ክፍለሃገሩ ሄደው ፀብ ጭረው ተጣልተው የስፖርት ተመላካቹን ደም አፍስሰው ተሳድበው ነው ሲመለሱ የነበረው ዘንድሮስ ? ያው ነው ባለጌ ያገግማል እንጂ .................

Abiti [523 days ago.]
 አስራት መገርሳ ብልህና አስተዋይ ልጅ መሆኑን ያሳያል ቡና አለመፈረሙ ማን ሞኝ ነው ሰላም የሌለው በብዙ ውስብስብ ችግሮች መከራዎች የተተበተበ ሲዖል የሆነ በየአመቱ ኡኡኡኡኡኡ የሚል ክለብ ውስጥ ገብቶ የጨጓራ የደም ብዛት የራስ ምታት በሽተኛ የሚሆነው ማን ሞኝ ነው

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!