Recently Posted News
  በተጫዋቾች ዝውውር ዘግይቶ የተነሳው ደደቢት የአገሪቱን ሪከርድ የሰበረ ዝውውር ፈጸመ
00, 0000

በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተወዳዳሪ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነውና የ2005 ዓ.ም ሻምፒዮኑ ደደቢት እግር ኳስ ክለብ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ካስፈረማቸው ተጫዋቾች ይልቅ ያሰናበታቸው ይልቃሉ። በተለይ ተከላካዩን ተካልኝ ደጀኔን፣ አማካዩን ያሬድ ዝናቡን እና አጥቂውን ሳሙኤል ሳኑሚን መልቀቁ የክለቡን ጉዞ ወዴት? አስብሎት ነበር። ሆኖም አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት የብሔራዊ ቡድን ወሳኝ ተጫዋቾችን ማለትም አስራት መገርሳን እና የ2017 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያው ኮከብ ጎል አግቢውን ጌታነህ ከበደን አስፈርሞ ስብስቡ ላይ ጥራት ጨምሮበታል። ለጌታነህ ዝውውር አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በመክፈል የአገሪቱን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።

ከንግድ ባነክ ጋር ሁለት ዓመታትን ያሳለፈውና ለሲዳማ ቡና ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ኤፍሬም አሻሞ በዝውውሩ የመጀመሪያ ሳምንታት ሰማያዊ ለባሾቹን የተቀላቀለ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የሳኑሚን ቦታ በብቃት መሸፈን የሚችለው ጌታነህ ከበደ ወደ ቀድሞ ክለቡ እንዲመለስ ያስቻለውን ዝውውር ፈጽሟል። ደደቢት ለጌታነህ ወይም “ሰበሮም” በወር 125 ሺህ ብር እንደሚከፍል ያስታወቀው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ ይህ የገንዘብ መጠንም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውዱ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች አድርጎታል።

በደደቢት በነበረበት ወቅት ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር የሚታወቀው ጌታነህ ከበደ በቀድሞው የክለቡ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አወል “ሰበሮም” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል። ሰበሮም ክለቡ ደደቢት በ2005 የሊጉ ሻምፒዮን ሲሆን 22 ጎሎችን በስሙ አስቆጥሮ ኮከብ ጎል አግቢ ተብሎ ከመሸለሙም በተጨማሪ የኮከብ ተጫዋችነት ዘውድንም በድጋሚ መጎናጸፍ ችሎ ነበር። ላለፉት ሁለት ዓመታት ግን ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ ለቪድስ ዌትስ ክለብ ፈርሞ ለአንድ ዓመት ከተጫወተ በኋላ በውሰት ለፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ሲጫወት ከርሟል።

በሌላ ዜና የሊጉ የ13 ጊዜ አሸናፊዎቹ የአማካይ ክፍላቸውን ድክመት ለማጠናከርና ክፍተቱንም ለመሙላት ምዕራብ አፍሪካዊ ተጫዋች አስፈርመዋል። በደቡብ አፍሪካ ሊጎች ተጫውቶ ያሳለፈውን አማካይ በምን ያህል ገንዘብ እንዳስፈረሙ ግን ቅዱስ ፈረሰኞቹ ይፋ አላደረጉም።


ethiopianathletics.net
 
Share this News/Article on your facebook page:    
 
MuleSanjawe [518 days ago.]
  @ Adego are you silly man ?! አስቂኝ ቂል ሰው ነገር ነህ ቡናን የሚደግፈው ደሃው ነው ጊዮርጊስን የሚደግፈው ደግሞ ሀብታሙ ነው ማለትህ ያሳፍራል ስፖርትና ፖለቲካ የተምታታብህ ነፈዝ ነገር ነህ ይልቅ ጊዮርጊስ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ስለሚደገፍ ቡናዎች የተቃጠላችሁ ያረራችሁ ነው የሚያስመስልባችሁ !

Sirak [466 days ago.]
 ከአንተ የባሰ ቂል የለም ነፃነት ሳይኖርህ ቡና ጊዪርጊስ እያልክ ጊዜህን የምታጠፋ

ter [417 days ago.]
 ewedachihualehu

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text)

arachni_name [65 days ago.]
 arachni_text

arachni_name) [65 days ago.]
 arachni_text

Your Comment /አስተያየት
Name:
Email:
 
 
Comment:  *
 
 
 
 
Copyright© 2014 Ethiopianathletics.net All rights reserved!