የ3ለ0ው የኡጋንዳው የወዳጅነት ጨዋታ ሽንፈት ለወሳኙ የአልጀርስ ጨዋታ ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረት እንዳያዳክም ያስፈልጋል።
ህዳር 01, 2007

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ኡጋንዳ ላይ በኔልሰን ማንዴላ ብሄራዊ ስታዲየም  ከኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ0 ተሸንፏል። በስፍራው ተገኝተው የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ እንደዘገቡት ጐሎቹ የተቆጠሩት በመጀመሪያው ግማሽ ጨዋታ ማብቂያ ጭማሪ ደቂቃ ላይ እና ከረፍት መልስ በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ውስጥ ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በጨዋታው የነበረው እንቅስቃሴ ደካማ መሆንን ጨምሮ የተከላካዮች ስህተት መብዛት፣እንዲሁም  ንቁ ሆኖ ያለመጫወት ለሽንፈቱ አስተዋጽዎ ማድረጉን አቶ ወንድምኩን አላዩ ጨምረው ገልጸዋል። 

Walias at traing

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ እንዲሆነው ከኡጋንዳ ጋር ያደረገው የትላንቱ ጨዋታ አጥቂዎቹን ጌታነህ ከበደ፣ሳላዲን ሰይድንና ኡመድ ኡክሪን ያላካተተ  መሆኑ ጐል ለማስቆጠር ሊከብደው እንደሚችል መገመት ባያዳግትም  የተከላካዩ ክፍል ከሞላ ጐደል ከአበባው ቡጣቆ በስተቀር የተሟላ ስለነበር በሰፊ 3ጐል ልዩነት ይሸነፋል የሚል ግምት ብዙም አልነበረም። ሽንፈቱን በተለይ አስደንጋጭ የሚያደርገው ከአንድ ሳምንት በኋላ ከጠንካራው የአልጄሪያ ቡድን ጋር አልጀርስ ላይ ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ እርማት  ዝግጅት ለማድረግ  ብዙም ጊዜ ስለማይሰጥ ነው።  

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ያሳየውን ደካማ አቋም በአለው አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መቀየር ካልቻለ በአሁኑ ጊዜ ከአፍሪካ ጠንካራ ከሚባሉት ቡድኖች ተርታ የሚሰለፈውን የአልጄሪያን  ብሄራዊ ቡድን አልጀርስ ላይ  አሸንፎ ይወጣል ማለት እንደ ኳስ ተአምር የሚቆጠር ይሆናል። ይህን የፈጠጠ እውነታ ስንገነዘብ አሰልጣኝ ባሬቶ  በመጪው እሁድ በሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ የተጫዋቾች አጠቃቀማቸው ላይ ለውጥ በማድረግ  ለአጭር ጊዜ ወይም ለአንድ ጨዋታ ውጤታማ  ሊያደርጋቸው የሚችል እንዲሆን ማድረግ ይኖርባቸዋል እንላለን። የረጅም ጊዜ ስትራቴጂን ለማሳካት እንደዚህ ያሉ ጊዜያዊ ነገር ግን ወሳኝና ፈታኝ የሆኑ ጨዋታዎችን በብቃት መወጣትን ይጠይቃል። 

አሰልጣኝ ባሬቶ  ቡድናቸው የማሊን ብሄራዊ ቡድን ማንም ባልጠበቀበት ሁኔታ በሜዳው 3ለ2 ያሸነፉበትን የሞራል ጥንካሬ፣የታክቲካል ዲሲፕሊን እንዲሁም ተስፋ ያለመቁረጥ ዝንባሌ ተጫዋቾቻቸው  በመጪው እሁድ ከአልጄሪያ ጋር በሚደርጉትው ጨዋታ ለመድገም እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። 

Walias


እግር ኳስ ከኳስ ጥበብ በተጨማሪ የማሸነፍ ወኔን የሚጠይቅ የእስፖርት አይነት እንደመሆኑ የብሄራዊ ቡድኑ ተሰላፊ ተጫዋቾቻችን የሀገራቸውን ማሊያ ለብሰው ሲጫወቱ በወኔ ለ90 ደቂቃ መጫወት ይኖርባቸዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪ የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች የሚጠብቃቸው ጨዋታ ከባድነትን በሚገባ የሚረዳ ቢሆንም ተጫዋቾቹ በኋላፊነት በሚችሉትን ሁሉ እራሳቸውን ዝግጁ በማድረግ ተስፋ ሳይቆርጡ ለሀገራቸው  ጥሩ ውጤት ለማምጣት እስከ መጨረሻው እንዲጫወቱ ይጠብቃል።  

ማሊ ላይ የተገኘውን አይነት ውጤት በአልጀርስ ለመድገም የትላንቱ ሽንፈት  በሁሉም ወገን ሊያስነሳ የሚችለውን ሰጣገባ ለጊዜው እረስቶ በቀረው ጊዜ  ለአልጄሪያው ጨዋታ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ዝግጅት ማድረግን ይጠይቃል። ለብሄራዊ ቡድኑ  ድጋፍ የሚሰጡ አካላት በሙሉ አቅማቸውን በማስተባበር ለቡድኑ ድጋፋቸውን ከመቼውም ጊዜ በተጠናከረ ሁኔታ ሊሰጡት ይገባል እንላለን። 
ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Aweke [1200 days ago.]
 Tnx ethiofootball.com owners

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!