ዋሊያዎቹ ከአልጀርስ ምን ይዘው ይመለሳሉ?
ህዳር 05, 2007

30ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያዘጋጀው አገር አልታወቀም። በውድድሩ ከሚሳተፉ 16 አገሮች መካከል አንዳንዶቹ የሚሄዱበትን አገር ባያውቁም ወደ ውድድሩ ቦታ የሚያደርሳቸውን አውሮፕላን ለመሳፈር ትኬት ሊቆርጡ ካቆበቆቡ ሳምንታት ተቆጥረዋል። ከእነዚህ አገሮች መካከል አልጀሪያ ቀዳሚዋ ናት። ልክ እንደ አስተናጋጅ አገር አለመታወቅ ሁሉ በውድድሩ መካፈልና አለመካፈላቸውን ያላወቁ አገሮችም የመጨረሻ ሙከራቸውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። 

አስተናገጁ ባልታወቀበት 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 30 አባላትን ይዞ ትናንት ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ተጉዟል። ፖርቹጋላዊው አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ከአልጀርስ አንድ ነገር ላገኝ እችልባቸዋለሁ ብለው ያመኑባቸውን 20 ተጫዋቾች ይዘው ወደ ስፍራው የተጓዙ ሲሆን አጥቂዎቹ ሳላሃዲን ሰይድ በጉዳትና ጌታነህ ከበደ በቅጣት ከቡድኑ ጋር አለመጓዛቸው በስብስባቸው ላይ አንዳች ክፍተት እንዳለ የስፖርት አፍቃሪው ቤተሰብ ይስማማል። ፖርቹጋላዊው የዋሊያዎቹ አለቃ ግን በስብስቡ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። 

ዋሊያዎቹ በ30ኛው  የአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል በሂሳብ ስሌት ከፊታቸው የተደቀኑትን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሌላው የምድባቸው ተስፈኛ ማሊም ቢያንስ በአንዱ ጨዋታ መሸነፍ ይኖርባታል። ይህ ደግሞ የዋሊያዎቹን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የሚያደርጉትን ጉዞ ፈታኝ የሚያደርግባቸው ሲሆን በተለይ ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አልጀርስ ላይ ከአልጀሪያ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀላሉ ያሸንፋሉ ወይ? የሚለው ጥያቄ ነው። 

ከሁለት ወራት በፊት ተኩላዎቹ አዲስ አበባ ላይ ከዋሊያዎቹ ሙሉ ሶስት ነጥብ እንደወሰዱት ሁሉ ዋሊያዎቹስ በሰው ቤት ሶስት ነጥብ ይዘው ይመለሳሉ? መልሱን ነገ ቅዳሜ ከምሽቱ አራት ሰአት ከሰላሳ ላይ  የምናየው ይሆናል። እስከዚያው ድረስ ግን ዝግጅት ክፍላችን ለዋሊያዎቹ መልካም ውጤት ይመኛል። 

 ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!