የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ውሎ
ህዳር 15, 2007


-  ወልድያ በሜዳው ያለመሸነፍ ሪከርዱን ገፍቶበታል
-  አርባምንጭና ሶስት ነጥብ እንደተነፋፈቁ ቀጥለዋል
-  አራቱም ጨዋታዎች ያለመሸናነፍ ተጠናቅቀዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለማለፍ በነበረበት ጨዋታ ምክንያት ለአንድ ሳምንት ተቋርጦ የነበረው ፕሪሚየር ሊጉ ትናንት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች አራት ጨዋታዎችን በማካሄድ ቀጥሎ ውሏል። በትናንቱ ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ከበርካታ የአዲስ አበባ ደርቢዎች አንዱ የሆነው የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ነው። በዚህ ጨዋታ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም የሚሰለጥነው ንግድ ባንክ ከእረግፍ በፊት ፍሊፕ ዳውዝ ባስቆጠራት ግብ መምራት ችሎ ነበር ለእረፍት የተለያዩት። በዚህ የጨዋታ ክፍለጊዜ በሁለቱም በኩል ለተመልካች ማራኪ ያልሆነ የኳስ ፍሰት የታየ ቢሆንም ከእረፍት መልስ ግን የተሻለ እንቅስቃሴ ለማሳየት ሞክረዋል። 
EEPCO VS CBE

የአሰልጣኝ አጥናፉ አባታ ልጆች ከእረፍት መልስ በተጋጣሚዎቻቸው ላይ ተደጋጋሚ የግብ ሙከራ በማድረግ የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። አሰልጣኝ አጥናፉ አባተ በእለቱ ጥሩ ሲጫወት ያላመሸውን ፕሮፌሽናሉን ፒተርን ቀይረው ጌዲዮን ታደሰን ካስገቡ በኋላ ይበልጥ ተጭነው መጫወት ችለዋል። በዚህ ክፍለጊዜም በአማካዩ ዊሊያም ኣሳጆ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል። ይህ ውጤትም ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን በፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ ካሸነፈ በኋላ በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት እንዲያጠናቅቅ ሲያደርገው መብራት ኃይል ደግሞ በአዲስ ዓመት ያደረጋቸውን ሶስቱንም ጨዋታዎች ሳይሸነፍም ሳያሸንፍም እንዲወጣ አስችሎታል።
 
ከጨዋታው በኋላ የሁለቱም ክለቦች አሰልጣኞች ለኢትዮፉትቦል ዶት ኮም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ “ቡድኔ ገና መደራጀት ላይ ሰለሆነ ውጤቱን በጸጋ ተቀብየዋለሁ” ሲሉ የንግድ ባንኩ አቻቸው አሰልጣኝ ፀጋዬ በበኩላቸው “በዚህ ወቅት ሁሉም ክለቦች በሙሉ ኃይላቸው ስለሚጫወቱ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች አስቸጋሪ መሆናቸው የታወቀ ነው” ብለዋል። 
ክልል ላይ የተደረጉ ሶስቱም የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በተመሳሳይ በአቻ ውጤት ተጣነናቅዋል። አዳማ ላይ አዳማ ከነማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሃዋሳ ከነማን አስተናግዶ አንድ እኩል ሲለያዩ ወልድያ ላይ ወልድያ ሙገር ሲሚንቶን ገጥሞ በተመሳሳይ አንድ እኩል በሆነ ውጤት  ተለያይተዋል። ከእረፍት በፊት እንግዳው ቡድን መምራት ችሎ የነበረ ቢሆንም ከእረፍት መልስ የአጨዋወት ሚና ይዘው የገቡት የአሰልጣኝ ንጉሴ ኃይሌ ልጆች በአብይ በየነ አማካኝነት አቻ መሆን ችለዋል። 

አርባምንጭ ላይ የተካሄደውን የአርባምንጭ ከነማና ሲዳማ ቡና የደቡብ ደርቢ ጨዋታ ግብ የሚያስቆጥር ጠፍቶ ያለ ግብ ተለያይተዋል። በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚሰለጥነው የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዚህ ዓመት ከሜዳው ያካሄዳቸውን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል። ባለ ሜዳው አርባምንጭ ከነማ በበኩሉ በዓመቱ ያካሄዳቸውን አራቱንም ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ያጠናቀቀ ሲሆን ከአካሄዳቸው አራት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሶሰቱን ያካሄዳቸው ከክልሉ ደርቢዎች ጋር ነው። 

ፕሪሚየር ሊጉ ነገም ቀጥሎ ውሎ ሁለት ጨዋታዎች አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ሲካሄዱ አንድ ጨዋታ ደግሞ ክልል ላይ ይካሄዳል። አዲስ አበባ ላይ በዘጠኝ ሰዓት የጥሎ ማለፉ አሸናፊ ደደቢት ከወላይታ ድቻ ሲጫወቱ 11 ሰዓት ላይ ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ይጫወታሉ። ክልል ላይ ደግሞ ዳሽን ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በፋሲለደስ ስታዲየም ይጫወታሉ። 

ፕሪሚየር ሊጉን በአራት ጨዋታዎች ስምንት ነጥብ የሰበሰበው የዘላለም ሽፈራው ቡድን ሲዳማ ቡና በመሪነት ላይ ሲቀመጥ በአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ የሚሰለጥነው ደደቢት በስድስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ኢትዮጵያ ቡና ምንም ነጥብ ባለመያዙ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ሁለት ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ተጫዋቾች የደደቢቱ ሳሙኤል ሳኖሜ በአራት ግቦች ሲመራ የኢትዮጵያ ንግብ ባንኩ ፍሊፕ ዳውዝ በሶስት ግቦች ይከተለዋል። 


ዘጋቢ፦ ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
habib jemal [1184 days ago.]
 zegebaw temechtonal ketlubet zirzrun sefa btaregut demo yebelete... :mngizem woldia:

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!