ቡና ዳሽንን ደደቢት ድቻን ሲያሸንፉ፤ ጊዮርጊስና መከላከያ አቻ ተለያይተዋል
ህዳር 17, 2007

ትላንት በተከናወኑት በአራተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚይ ሊግ ጨዋታዎች፥ ኢትዮጵያ ቡና ዳሽንን በሜዳው 2ለ1 አሸንፏል።  ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ ለቡና የመጀመሪያ ድሉ መሆኑ ነው።  ቢኒያም አሰፋ ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱንም ጐሎች ሲያስቆጥር ለዳሽን ይተሻ ግዛው አንዷን ጎል አስቆጥሯል። ጨዋታው ብዙ ትእይንትን ያስተናገደ ነበር።  ከኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾች  በቀይ ካርድ ተባረዋል።  ሰአት ለመግደል ሲሞክር በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ዳኛው ያባረሩት ሙሴ ገብረኪዳን ቀይ አይገባኝም ሲል ከዳኛው ጋር ግብግብ ለመግጠም ጓንቱን አውልቆ ሲጋበዝ ታይቷል። ሌላው ከቡና በቀይ የተባረረው ሮቤል ግርማ ነው። ቡና የጐል ማግባት ችግሩን ለመፍታት ከምእራብ አፍሪካ ያስመጣቸው አጥቂዎች በትላንቱ ጨዋታም ውጤት አላመጡለትም። ቡድኑን ከሜዳው ውጪ ሙሉ ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስቻለው ከጉዳት ወደ ጨዋታ የተመለሰው ጐል አዳኙ ቢኒያም አሰፋ ነበር።
 
Samuel Sanumi
አዲስ አበባ ላይ በተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች፥ በቅድሚያ የተገናኙት ደደቢትና ወላይታ ድቻ ነበሩ።  ጨዋታው ተመጣጣኝ ጨዋታና የግብ ሙከራዎች የታዩበት ነበር። ደደቢቶች የመጀመሪያዎቹን 25 ደቂቃዎች ጥሩ እንቅስቃሴ በማድር 20ኛው ደቂቃ ላይ በሳሙኤል ሳኑሚ አማካኝነት ጐል አስቆጠሩ። ብዙም ሳይቆዩ በ25ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛውን ጐል በመስፍን ኪዳኔ አማካኝነት ደገሙ። ድቻዎች በማያቋርጠው የደጋፊዎቻቸው ጩኸት ተበረታታው ወደ ደደቢት ጐል መጠጋት የጀመሩት ሁለኛው ጐል እንደተቆጠረባቸው ነበር። በ29ኛው ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ ከክንፍ ወደመሃል የተሻገርን የአየር ኳስ በትላንትናው እለት ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የወላይታ ድቻው አላዛር ፋሲካ በጭንቅላት በመግጨት ድንቅ ጐል አስቆጠረ። ጨዋታው በይበልጥ መሟሟቅ የጀመረው ይሄኔ ነበር። የድቻ ደጋፊዎች ቡድናቸውን ተጨማሪ ጐል አንዲያስቆጥር በጩኸት ድጋፋቸውን መስጠት በቀጠሉበት በመጀመሪያው አጋማሽ መጨረሻ 46ኛው ደቂቃ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ በአየር የተሻገረን ኳስ አላዛር በጭንቅላት በመግጨት ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ አቻ የምታደርውን ጐል አግብቶ ሁለቱ ቡድኖች 2ለ2 እረፍት ወጡ።

ከረፍት መልስ በሁለቱም በኩል ብዙ የግብ ሙከራዎች የተደሩ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ብዙ ጐል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶች አባክነዋል። ደደቢቶች የጨዋታውን የበላይነት በያዙበት በ60ኛዎቹ ደቂቃዎች  ሳሙኤል ሳኑሚ በግራ ክንፍ ጥላፎቅ በኩል ኳስ ብቻውን ይዞ ገብቶ ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ የማሸነፊያዋን የድቻው በረኛ በቆመበት ለማግባት ችሏል።

የጐል የበላይነቱን የተረከቡት ደደቢቶች የጨዋታውን እንቅስቃሴ ለቀሪዎቹ 25 ደቂቃዎች በመቆጣጠር ሶስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት ችለዋል። ውጤቱ ደደቢቶችን በ3 ጨዋታና በ9ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ እንዲቀመጡ አስችሏቸዋል። 
Stgeorge Vs Defence


በሁለተኛው ጨዋታ የተገናኙት ቅዱስ ጊዮርጊስና መከላከያ ነበሩ። በትላንቱ ጨዋታ ብዙም ጥሩ ያልነበሩት ጊዮርጊሶች በ9ኛው ደቂቃ ላይ ሳላዲን በርጊቾ ከቅጣት ምት የተተፋን ኳስ በጭንቅላት በመግጨት የመጀመሪዋን ጐል  አስቆጥሮ ጨዋታው ጊዮርጊሶች መምራት ችለው ነበር። በቀሪዎቹ   35ት ደቂቃዎች ብዙም ጥሩ እንቅስራሴ በሁለቱም በኩል ሳይደረግ 1ለ0 በሆነ ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል። 

በሁለተኛው አጋማሽ የመጀሪያው ደቂቃ ላይ መከላከያዎች ያገኙትን ቅጣት ምት በመሐመድ ናስር አማካኝነት ወደ ጐል መቀየር ቻሉ። ጊዮርጊሶች የገባባቸውን ጐል ለመካስ ጨዋታውን አፍጥነው  ለመጫወት ቢሞክሩም በቀድሞው የጊዮርጊስ ግብ አዳኝ በነበረው ገብረመድህን ሀይሌ  የሚሰለጥኑት መከላከያዎች በኳስ ቁጥጥር የተሻሉ ስለነበሩ የተሻለ የግብ ሙካራ ሲያደርጉ ያመሹት መከላከያዎች ነበሩ። ጨዋታው 1ለ1 ከመጠናቀቁ በፊት በ65ኛው በ69ኛውና በ91ኛው ደቂቃ ላይ ጐል ሊሆኑ የሚገባቸውን ኳሶች መከላከያዎች ባይስቱ ኖሮ ጊዮርጊሶች ተሸንፈው የሚወጡበት እድል ሰፊ ነበር።

 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!