ኢትዮጵያ ቡና በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1ለ0 አሸነፈ
ህዳር 29, 2007

በፕሪሚየር ሊጉ ሁሌም በተመልካች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የአዲስ አበባው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና የአዲስ አበባ የደርቢ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ደጉና ዳዊት የመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት አርማ የታተመበትን ካኒቴራ  በመልበስ ለመቄዶኒያ የአረጋውያን መርጃ ድርጅት የቡድኖቻቸውን  አጋርነት ገልጸዋል። 
Mekedinya Haregaweyane Merja Dirjit

ለቡና የማሸነፊያዋን ጐል   በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ በ49ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው አስቻለው ግርማ ነበር። አስቻለው  ለቡና የማሸነፊያዋንና የጨዋታውን ብቸኛ ጐል ያስቈጠረው በረዥሙ ከኋላ ተሰንጥቆ የተሻገረለትን ኳስ  ከጊዮርጊስ ተከላካዮች መሃል ሾልኮ በማለፍ በጥሩ የኳስ ቁጥጥር      ጊዜ ሳያባክን ወደጐል የመታት ኳስ የግብ ክልሉን ለቆ የወጣውን የቅዱስ ጊዮርጊሱን በረኛ ሮበርት ኦዶንኮራን  አልፋ መረብ ላይ በማረፏ ነው።

Aschalew


 በአብዛኛው የመፈራራትና ሽኩቻ በበዛበት፣ በዳኛ ፊሽካ ስድስት ቢጫ ካርድ በተመዘዘበት  የመጀመሪያው አጋማሽ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ብዙም የረባ የጐል ሙከራ ባይደረግበትም በኳስ ቁጥጥር ቡናዎች  በዳዊት እስጢፋኖስ መሪነት ከጊዮርጊሶች የተሻሉ ነበሩ። ቡናዎች  በተለይ 24ኛው ደቂቃ ላይ ከመሃል ጀምሮ ጥሩ የኳስ ቅብብል አድርገው ለጥላሁን ወልዴ ሴንተር ላይ የጣሉለትን  ኳስ መቆጣጠር አቅቶት ሳይጠቀምበት ቀረ እንጂ ለቡናዎች ከረፍት በፊት ካደረጉት ወደ ጐል የመቅረብ ሙከራ የተሻለ አጋጣሚን ያመቻቸ  ነበር። ጨዋታው በሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች የህብረ ዝማሬ ድጋፍና ማበረታቻ ታጅቦ አስከ እረፍት ቢቀጥልም  ተመልካቹ ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ ለማየት የቻለው የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ብቻ ነበር።

Aschalewየሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን በተለይ ቡናዎች በአስቻለው ግርማ አማካኝነት በ49ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ካስቆጠሩ በኋላ የጨዋታው ፍጥነት  ሊጨምር ችሏል። ጊዮርጊሶች የገባባቸውን ጐል ለመመለስ ከ60ኛው ደቂቃ ጀምሮ በካታንጋ ቀኝ ክንፍ በኩል  በተደጋጋሚ ኳሶችን በማደራጀት ወደጐል ለመቅረብ ችለው ነበር። ፍጹም ገብረመድህን በ64ኛው ደቂቃ  ላይ በቡና ተከላካዮች ስህተት ወደኋላ የተመለሰን ኳስ እንዲሁም በ70ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ ክንፍ ወደመሃል የተሻማን የአየር ኳስ ሳይጠቀምባቸው የቀሩ ጊዮርጊሶችን አቻ ሊያደርጉ የሚችሉ አጋጣሚዎች ነበሩ።

ቡናዎች ጐል አስቆጥረው መምራት ከጀመሩ በኋላ በድጋሚ ወደ ጐል በመቅረብና የተሻለ የጐል ሙከራ ማድረግ የቻሉት  አስቻለው ግርማ በ76ኛው ደቂቃ ላይ  የመሃል ዳኛው የጨዋታ አድቫንቴጅ  በመጠበቃቸው የተገኘን  ኳስ ወደ ግብ ክልል ብቻውን ይዞ ገብቶ ወደ ጐል የሞከራት ኳስ ኢላማውን ስታ ወደ ውጪ በወጣችበት ጊዜ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊሶች  አሉላ ግርማን ወደሜዳ ቀይረው ካስገቡ ቧኋላ የበለጠ የማጥቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ።  81ኛው ደቂቃ ላይ ጫና በበዛበት የቡና ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ጥላሁን ወልዴ የጊዮርጊስ ተጫዋች ላይ ጥፋት በመስራቱ ዳኛው ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተው ጥፋቱን የሰራውን ጥላሁንን በቀይ ካርድ ከሜዳ አስናብተውታል።  የፍጹም ቅጣት ምቱ ተገቢነት ያልተዋጠላቸው ቡናዎች በደጋፊዎቻቸው ያልተቋረጠ የተቃውሞ ጩኸት  ታጅበው  ከዳኛው ጋር ለደቂቃዎች በመከራከር ቅሬታቸውን አሰምተዋል።  የፍጹም ቅጣት ምቱን  ለጊዮርጊሶች ፍጹም ገብረመድህን ቢመታም ቄንጠኛው ናይጄሪያዊ የቡና በረኛ ኔልሰን ሊያድንበት ችሏል። ጨዋታው እንደተጋጋለ ቀጥሎ  ዳኛው  በባከነ ሰአት የጨዋታውን ማብቂያ ፊሽካ ከመንፋታቸው ከጥቂት ሰኮንዶች አስቀድሞ ጊዮርጊሶች  በ93ኛው ደቂቃ ላይ ጐል ሊሆን የሚችል አጋጣሚ አግኝተው ኳስ በግቡ አግዳሚ ስር ለጥቂት  ሊወጣባቸው ችሏል። 

Coffee1-0 St.George


ከጨዋታ ጨዋታ ጥንካሬያቸውን እያሳደጉ የመጡት በጥላሁን መንገሻ የሚሰለጥኑት ኢትዮጵያ ቡናዎች የዛሬውን ጨዋታ ጐል አግብተው መምራት እስከቻለበት ሰአት ድረስ የተሻለ የኳስ ቁጥጥርና የጨዋታ የበላይነት እንደማሳየታቸው ያገኙትን ድል ከደጋፊዎቻቸው ጋር ማጣጣም አይበዛባቸውም። 

በስድስተኛ ሳምንት በተመሳሳይ በክልል ከተሞች በተካሄዱ ሌሎች ጨዋታዎች ዳሽን ቢራ ሙገር ሲሚንቶን ፣ወላይታ ድቻ ሃዋሳ ከነማን በተመሳሳይ ውጤት 1ለ0 ሲያሸንፉ፤ ንግድ ባንክ በአርባ ምንጭ እንዲሁም ወልዲያ ከነማ በመብራት ሀይል በተመሳሳይ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል። አዳማ ከነማና መከላከያ አዳማ ላይ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
abebe [1169 days ago.]
  I am more than happy,because I saw coffee wearing their old time jersey.We do not want yellow jersey, which is almost the same jersey our rivals are wearing.I am also delighted with their current winning mentality.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!