መከላከያ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ጨበጠ
ታህሳስ 06, 2007

በርካታ ያልተጠበቁ ውጤቶች በተመዘገቡበት የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መከላከያን በመሪነት ርካቡ ላይ ሲያስቀምጥ ወልድያን ደግሞ ወደታች ገፈቶታል። ፕሪሚየር ሊጉ ትናንትና ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባና በክልል ሰባት ጨዋታዎች የተስተናገዱ ሲሆን ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ እንዲሁም አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
 
የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ የተካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲየም መብራት ሀይልና ዳሽን ቢራ ያደረጉት ጨዋታ ነው። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የተጠናቀቀው በመብራት ሀይል አሸናፊነት ሲሆን ለመብራት ሀይል ግቦቹን አዲስ ነጋሽና ከ11 ዓመታት በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመጀመሪያ ግቡን ያስቆጠረው ዮርዳኖስ አባይ ናቸው። ለዳሽን ቢራ በባዶ ከመሸነፍ ያዳነችዋን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ደግሞ ይተሻ ግዛው ነው። ዮርዳኖስ አባይ ተቀይሮ ሲገባ በስታዲየም ከተገኙ ደጋፊዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል። 

ቅዳሜ ከአመሻሹ 11፡30 የተካሄደውን የኢትዮጵያ ቡና እና የደደቢት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና ሁለት ለባዶ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ግቦቹን የደደቢቱ አዳሙ መሃመድ በራሱ ላይ እና የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ ቢኒያመ አሰፋ ደግሞ ሁለተኛዋን አስቆጠሯል። ቅዳሜ ድል የቀናቸው ቡና እና መብራትሀይል በ12 ነጥብ የፕሪሚየር ሊጉ መሪዎች ተርታ አሰለፏቸዋል። 

ትናንት በተካሄዱ አምስት ጨዋታዎች ደግሞ ገብረመድህነ ሀይሌው መከላከያ ሃዋሳ ከነማን በመሃመድ ናስር ብቸና ግብ አንድ ለባዶ አሸንፎ የሊጉን መሪነት ተረክቧል። መከላከያ ነጥቡን 13 ያደረሰ ሲሆን ካደረጋቸው ሰባት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችም ሽንፈትን አልቀመሰም። እስከሰባተና ሳምንት በተካሄዱ ጨዋታዎች መብራተ ሀይልና መከላከያ ሽንፈት ያልቀመሱ ብቸኞቹ ክለቦች ሲሆኑ ወልድያ ደግሞ ማሸነፍ የተሳነው ብቸኛ ክለብ ሆኗል። 

ፕሪሚየር ሊጉን የሚመራው መከላከያ ካደረጋቸው ሰባት ጨዋታዎች በአንዱም አይሸነፍ እንጅ ያስቆተረው የግብ ብዛት የፕሪሚየር ሊጉ ግርጌ ላይ ከተቀመጠው ወልድያ ያነሰ ነው። እንዲሁም ክለቡ እሳካሁን ካስቆጠራቸው አራት ግቦች ሶስቱን ከመሃድ ናስር ቀሪዋን አንድ ግብ ደግሞ ከሙሉኣለም ጥላሁን ነው። 

CBE VS StGeorge


ከአመሻሹ 11፡30 ተገናኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን አንድ እኩል ጨረሰዋል። ፈረሰኞቹ ወጣቱ አማካይ ናትናኤል ዘለቀ ባስቆጠራት ግብ ጨዋታውን አብዛኛውን ጊዝ መምራት ችለው የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ፍሊፕ ዳውዝ ተቀየሮ ገብቶ ቡድኑን አቻ ያደረገች ግብ አስቆጠራል በፍጹም ቅጣት ምት። 

CBE VS StGeorge

CBE VS StGeorge

ክልል ላይ ሶስት ጨዋታዎች ተከሂደው ይርጋለም ላይ አዳማ ከነማ ባለምዳውን ሲዳማ ቡናን በሱሌይማን መሃመድና በቢኒያም ሀይሉ ግቦች ሁለት ለባዶ አሸንፎ ተመልሷል ነጥቡንም ዘጠኝ በማድረስ ደረጃውን አሻሽሏል። አሰላ ላይ የተካህደውን ጨዋታ ደግሞ ባለሜዳው ሙገር ሲሚንቶ በእንግዳው አረባምንጭ ከነማ አንድ ለባዶ ተሸንፏል። ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻና ወልድያ ያደረጉትን ጨዋታ ባለምዳው ወላይታ ደቻ ሁለት ለባዶ አሸንፏል።  

ፕሪሚየር ሊጉን 13 ነጥብ የያዘው መከላከያ ሲመራ መብራት ሀይልና ኢትዮጵያ ቡና በአንድ ነጥብ ዠቅ ብለው ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ወልድያ በሁለት ነጥብ ደረጃውን ግርግ ሲይዝ ትናንት በመከላከያ የተሸነፈው ሃዋሳ ከነማ በአምስት ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ደረጃ ደደቢቱ ሳሙኤል ሳኑም በስድስት ግቦች ሲመራ የኢትጵያ ቡናው ቢኒያም አሰፋ በአምስት ግቦች ሁለተኛ ሆኖ ይከተለዋል። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!