ደደቢት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታን አሰናብቶ ዮሃንስ ሳህሌን ቀጠረ
ታህሳስ 07, 2007

የደደቢት እግር ኳስ አመራር አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታን ከአሰልጣኝነት ሥራቸው ማሰናበቱንና በምትካቸው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ የመሃል ተጫዋች እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ታዳጊ ቡድን በአሰልጣኝነት እየሰሩ የነበሩትን አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌን  እንዲተኳቸው ማድረጉን አስታውቋል። አዲሱ አሰልጠኝ  ቡድኑን እስከ ሰኔ 2007 ዓ.ም.  እንደሚያሰለጥኑት ክለቡ ጨምሮ አስታውቋል።

ክለቡ ለአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ መሰናበት ምክንያት ሲገልጽ፤ አሰልጣኙ በ2006ዓ.ም. የነበራቸውን የሥራ ውጤት  አጥጋቢ አለመሆንና በዘንድሮውም የውድድር አመት ቡድናቸው ያሳየውን ጥሩ አጀማመር ማስቀጠል አቅቶት  ከሳምንት ሳምንት ቡድኑ ውጤት እያጣ መምጣቱን ተከትሎ እንደሆነ አስረድቷል። 


በአሰልጠኝ ንጉሴ ይመራ የነበረው ደደቢት በዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ አዲስ አበባ ላይ ካደረጋቸው 6ስት ጨዋታዎች የመጀመሪዋዎቹን ሶስት ጨዋታዎች በሰፊ ጐል ልዩነት ማሸነፍ ቢችልም በቀሪዎቹ  ጨዋታዎች በተከታታይ በመከላከያና በሲዳማ ቡና እንዲሁም በመጨረሻ  በኢትዮጵያ ቡና ሽንፈትን አስተናግዷል።

Dedebit Vs Coffee


 ደደቢት በፕሪሚየር ሊጉ በ6ት ጨዋታ 9ኝ ነጥብ እና 3የግብ ክፍያ ይዞ በ6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የቡድኑ ዋና አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ  በ6ስት ጐል የፕሪሚየር ሊጉን ኮኮብ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!