ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ላይ ባዛርና ኤግዚቢሽን እያካሄደ ነው
ታህሳስ 10, 2007

ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ እሁድ ምሽት ድረስ የሚቆይ ኢግዚቪሽን እያካሄደ መሆኑነ ከክለቡ የደረሰን መረጃ ገለጸ። የክለቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ ምልልስ እንደገለጹት ክለቡ ኢግዚቪሽኑን ማካሄድ ያስፈለገው በአዳማ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩና በአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ባቀረቡለት ጥሪ መሰረት ነው። “መጀመሪያም ቢሆን በክልል የሚገኙ ደጋፊዎቻችንን የማደራጀትና በመደጋፊዎች ማህበር የማሰባሰብ እቅድ ነበረን። በአዳማ ከተማ ዋና ጎዳና እያካሄድን ያለውም በከተማው ነዋሪ የሆኑ ደጋፊዎቻችንን መመዝገብና የክለቡ አርማ ያረፈባቸውን እቃዎች የመሸጥ ሥራ ነው የምንሠራው” ብለዋል። 

የክለቡ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ አያይዘውም “ከአዳማው በምናገኘው ልምድ ወደፊት በሁሉም ክልሎች ለጨዋታ በምንንቀሳቀስበት ሁሉ በተመሳሳይ የደጋፊ ማብዛትና የክለቡ አርማ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች የመሸጥ ሥራ መስራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል። ክለቡ የኢግዚቪሽን ሥራውን እየሰራ የሚገኘው በአዳማ ከተማ ፖስታ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ መሆኑንም አቶ ገዛኸኝ ጨምረው ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ቡና የፊታችን እሁድ ከቀኑ 9፡00 ከአዳማ ከነማ ጋር በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጫወታል። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!