በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ወራት ጉዞ
ታህሳስ 16, 2007

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሶስት ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 14 ክለቦች መካከል ውድድሩን እያካሄደ ይገኛል። በሊጉ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በሁለት ሁለት ክለቦች ሲወከሉ ደቡብ ኢትዮጵያ በአራት ክለቦች በመወከል ቀዳሚው ነው። አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስድስት ክለቦችን በአንድ ስታዲየም በማጫወት ላይ ይገኛል። እስካሁን ድረስ ስምንት ክለቦች እያንዳንዳቸው ስምንት ስምንት ጨዋታዎችን ያደረጉ ሲሆን ስድስት ክለቦች ደግሞ አንድ አንድ ተሰተካካይ ጨዋታ ይቀራቸዋል። ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ያለፈው ዓመት ሻምፒዮን ፈረሰኞቹ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ሀይል፣ ደደቢት፣ ወላይታ ድቻና ሀዋሳ ከነማ ናቸው። 

ፕሪሚየር ሊጉን የደቡብ ኢትዮጵያው ተወካይ ሲዳማ ቡና በ14 ነጥብ ሲመራ ሶስት ክለቦች ማለትም መብራት ሀይል፣ ኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ እኩል 13 ነጥብ ይዘው ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል። ፈረሰኞቹ ከተደጋጋሚ ነጥብ መጣል በኋላ ሙገር ሲሚንቶን በማሸነፋቸው በ12 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል። 

በውድድር ኣመቱ ከተካሄዱ ጨዋታዎች መካከል በአንድ ጨዋታ በርካታ ግብ የተቆጠረው ደደቢት ወልድያን ሰደስት ለአንድ ሲያሸንፍ የተቆጠሩ ሰባት ግቦች ናቸው። ከዚህ ጨዋታ ቀጥሎ በርካታ ግብ የተቆጠረው አዳማ ከነማና ኢትዮጵያ ቡና ሶስት እኩል ሲለያዩ የተቆጠሩ ስድስድ ግቦች ናቸው። ብዙ ግቦችን በተጋጣሚዎች መረብ ላይ በማሳረፍ ቀዳሚው ክለብ ደደቢት ሲሆን 12 ግቦችን አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ ቡና 11 ግቦችን በማስቆጠር ይከተላል። ደደቢትና ቡና በተጋጣሚዎቻቸው ላይ 12 እና 11 ግቦችን ቢያስቆጥሩም ዘጠኝ ግቦችም ተቆጠረውባቸዋል።

የአማራ ክልሉ ተወካይ ወልድያ በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ክለብ በመሆን ቀዳሚ ነው። ወልድያ ስምንት ጨዋታዎችን አካሂዶ በስድስቱ መረቡን ያስደፈረ ሲሆን በድምሩ 16 ግቦች ተቆጥረውበታል። ክለቡ የተቆጠሩበትን 16 ግቦች ስድስት ግቦችን በተጋጣሚዎች መረብ ላይ በማሳረፍ ለማወራረድ ሙከራ እያደረገ ቢሆንም አስር የግብ እዳ ተሸክሟል። 

በአሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ የሚሰለጥነው መብራት ሀይል በአዲሱ ስሙ ኤልክትሪክ ክለብ ሰባት ጨዋታዎችን አካሂዶ አንድም ጊዜ ሳይሸነፍ በመጓዝ ብቸኛው ክለብ ነው። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሙገር ሲሚንቶ፣ ሀዋሳ ከነማና ወልድያ ደግሞ አንድ አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፉ ክለቦች ናቸው። በአንጻሩ መከላከያ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና አርባ ምንጭ ከነማ አንድ አንድ ጨዋታ ብቻ ተሸነፈዋል። 

የኢትዮጵያ ቡናው ቢኒያም አሰፋ አምስት ጨዋታዎችን አካሂዶ ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ከደደቢቱ ሳሙእል ሳኑም ጋር በጣምራ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ደረጃ መያዝ ችሏል። ቢኒያም ስድስት ግብ ያስቆጠረው አምስት ጨዋታዎችን ብቻ አካሂዶ ሲሆን የደደቢቱ ሳሙእል ደግሞ በሰባት ጨዋታ ነው።

ኢትዮጵያ ቡና አራት ተጫዋቾቹ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመሰናበታቸው 20 ሺህ ብር በመቀጣት የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል። እስካሁን ድረስም አራት ተጫዋቾቹን በቀይ ካርድ ያጣ ክለብ የለም ከቡና በስተቀር። ደደቢትና ወልድያ አሰልጣኞቻቸውን በጊዜ በማሰናበት የመጀመሪያዎቹ ክለቦች ሲሆኑ በሊጉ በውጭ አገር አሰልጣኝ የሚሰለጠነው ብቸኛ ከለብ ቅዱስ ጊዮረጊስ ነው። ኢትዮጵያ ቡናው ጥላሁን መንገሻ እና የኤልክትሪክ ክለቡ አጥናፉ አለሙ የተሻለ ወጥነት ያለው ቡድን በመሥራት በንጽጽር የተሻሉ አሰልጣኞች ሆነው ተገኝተዋል።  

ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
shibesh shibru [1152 days ago.]
 sundays game sidama buna VS WOLAYITA DICHA WINNING FOR SIDAMA BUNA

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!