የ14ቱ ክለቦች የዘጠኝ ሳምንታት ጉዞ
ታህሳስ 22, 2007

ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኤሌክትሪክና መከላከያ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ጊዜ የተሸነፉ ክለቦች። ወልድያ ከነማ፣ ሀዋሳ ከነማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቃራኒው አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፉ። በርካታ ቀይ ካርዶችን ያየ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ሲሆን አምስት ተጫዋቾቹ ቀይ ካርድ አይተዋል። 

ዳሽን ቢራ በአንድ ጨዋታ ከአንድ ግብ በላይ ማስቆጠር ያልቻለ ክለብ ሲሆን ደደቢት ደግሞ ከስምንት ጨዋታዎች መረቡን ሳያስደፍር የወጣው በአንዱ ጨዋታ ብቻ ነው ከንግድ ባንክ ጋር ባዶ ለባዶ ሲለያይ። በአንድ ጨዋታ ከአንድ ጎል በላይ ያልተቆጠረበት ክለብ መከላከያ ሲሆን ካደረጋቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች በአጠቃላይ የተቆጠረበት የጐል ብዛትም ሁለት ብቻ ነው። መከላከያ ላይ ጎል ያስቆጠሩ ክለቦች ፈረሰኞቹና ወላይታ ድቻዎች ብቻ ናቸው። 

በርካታ ግብ የተቆጠረበት ክለብ ወልድያ ከነማ ሲሆን 12 የጎል እዳ ተሸክሟል። ስድስት ጎሎችን ባያስቆጥር ኖሮ የጎል እዳው 18 ይደርስ ነበር። ደደቢት ከወልድያ ቀሎ ያለውን ደረጃ ይዞ ይከተላል። ቡና ሶስተኛ ነው። በርካታ ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ያጠናቀቀ ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ስድስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ጨርሷል። ብዙ ጨዋታዎችን የተሸነፈው ደግሞ ወልድያ ከነማ ነው ስድስት ጨዋታዎችን በመሸነፍ። 

የፕሪሚየር ሊጉን የመጀመሪያ ጎል ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቡናው ዴቪድ በሻሀ በራሱ ላይ ሲሆን የመጀመሪያውን ቀይ ካርድ የተመለከተው ደግሞ የወልድያ ከነማው አብይ በየነ ነው። የመከላከያው አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ በቀይ ካርድ በመባረር የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በአንድ ጨዋታ ሁለት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ የተሰናበቱበት የመጀመሪያው ክለብ ሆኗል። 

ኤሌክትሪክ በአንድ ጨዋታ በርካታ የውጭ ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች በመጠቀም ቀዳሚ ነው። ትናንት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሲጫወት አምስት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች ተጠቅሟል። 

ይርጋ አበበ 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!