በፕሪሚየር ሊጉ አስረኛው ሳምንት
ታህሳስ 29, 2007

  • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ከሶስት ነጥብ ጋር ተገናኙ
  • ኢትዮጵያ ቡና ከስድስት ጨዋታ በኋላ ጎል ሳያሰቆጥር ወጣ
  • ፈረሰኞቹና ሲዳማ ቡና ሃትሪክ ሰሩ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስረኛ ሳምንት ከተካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች መካከል አበበ ቢቂላ ስታዲየም ሶስቱን በማስተናገድ አራት ጎሎችን አስቆጥሯል። በእዚህ ስታዲየም የተካሄዱ ሶስቱም ጨዋታዎች በመሸናነፍ የተጠናቀቁም ሆነዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሶስት ከተሞች ማለትም የወላይታዋ ቢዲቲ፣ የጋሙጎፋዋ አርባምንጭና የክልሉ ርዕሰ መዲና ሃዋሳ ሶስት ጨዋታዎችን አካሂደው አራት ጎሎችን አስተናግደዋል። ከተካሄዱት ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱ በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ አንዱ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ምንም ጎል ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በሳምንቱ ከተካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች ያለ ምንም ጎል የተጠናቀቀ ብቸኛው ጨዋታም ይህ ጨዋታ ነው።

ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስና የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጠንካራነታቸውን ያስመሰከሩበት ሳምንት ሆኗል። በተለይ ፈረሰኞቹ በእነዚህ ሶስት ጨዋታዎች መረባቸውን ሳያስደፍሩ የወጡበት ሳምንት በመሆኑ የተከላካይ መስመራቸውን ጥንካሬም አስመስክረዋል።

አዳማ ከነማና ኢትዮጵያ ቡና በበኩላቸው ያለፉትን ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ማግኘት ከነበረባቸው ዘጠኝ ነጥብ ስድስቱን በትነዋል። በተለይ ኢትዮጵያ ቡና ካለፉት ስድስት ጨዋታዎች በኋላ ጎል ሳያሰቆጥር የወጣበት ጨዋታ አስረኛው ሳምንት ሆኗል። ለዚህም የቀረበው ምክንያት ኮከብ ጎል አግቢው ቢኒያም አሰፋንና አስቻለው ግርማን አለማሰለፉ ነው።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ከሶስት ነጥብ ጋር የተገናኙትም በአስረኛው ሳምንት መርሃ ግብር ሲሆን ሰባት ጨዋታዎችን ያለሽንፈት የተጓዘው ኤሌክትሪክ ለሁለተኛ ጊዜ የተሸነፈውም ባሳለፈነው ሳምንት መርሃ ግብር ነው። ኤሌክትሪክ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ከመሸነፉም በላይ ጎል ሳያስቆጥር የወጣባቸው ጨዋታዎች ሆነዋል።

በአጠቃላይ በአስረኛው ሳምንት መርሃ ግብር አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። በእነዚህ ሰባት ጨዋታዎችም አስር ጎሎች ተቆጥረዋል።

ዘገባ፦ ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
yonas molla [1140 days ago.]
 Yerga hule eketatelehalew betam des YElale Yemetakerebachew kuterawi mereja akatebete

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!