አበበ ቢቂላ ስታዲየም ባጣ ቆየኝ የሚሆነው እስከ መቼ?
ታህሳስ 30, 2007

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱ ሁሉንም የእግር ኳስ ውድድሮችና የአትሌቲክስ ውድድሮችን በማስተናገድ ብቸኛ የሆነው አዲስ አበባ ስታዲየም የፊታችን የካቲት መጀመሪያ ላይ 12ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር እንዲያስተናግድ ፕሮግራም ወጥቶለታል። በዚህ የተነሳም ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የአትሌቲክስ ውድደሩ እስከሚያልቅ ድረስ የሚካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮች በሙሉ ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተዘዋውረዋል። አበበ ቢቂላ ስታዲየምም አስታዋሽ አገኘ ማለት ነው። 
ላለፉት ረጅም ዓመታት የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን እያቆራረጠ በማካሄዱ ለተደጋጋሚ ትችት ሰለባ ሲዳረግ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአትሌቲክሱ ውድድር የተነሳ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እንዳይቋረጡ ለማድረግ የወሰደው መፍትሄ በመሆኑ በአንድ በኩል ሊያስመሰግነው የሚገባ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ለትችት ይዳርገዋል። በርካታ የአገራችን ክለቦች ተጫዋች ሲያስፈርሙም ሆነ የዓመት በጀታቸውን ሲያዘጋጁ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ እንዲሆናቸው አስበው በመሆኑ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በመቆራረጥ ሲካሄዱ ውድድሩ እስከ ሃምሌ የሚደርስበት አጋጣሚ ሲፈጠር ክለቦችን ተጎጅ ሲያደርጋቸው ቆይቷል። በዚህ በኩል ካየነው እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ለአንድ ወር ውድድር ከማቋረጥ ለጊዜውም ቢሆን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ማካሄዱ ይበል የሚያሰኝ ድርጊት ሆኖ አይተነዋል። 
Abebe Bekila Stadium


በሌላ በኩል ደግሞ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ችግሮችን መፍትሄ ሳያበጁ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮችን በዚያ ስታዲየም ማካሄድ ለተጫዋቾች ደህንነት ፈታኝነቱ አልተጤነም። በመጀመሪያ ደረጃ ስታዲየሙ የተነጠፈለት ሣር አርቲፊሻል በመሆኑ ከፍተኛ ጉልበት ይጠይቃል። ሌላው የስታዲየሙ ችግር ደግሞ ለረጅም ጊዜ አስታዋሽ አጥቶ በመቆየቱ ለተመልካች አመቺ አይደለም። ለእነዚህ ሁኔታዎች መፍትሄ ሳያዘጋጁ የአገሪቱን ትልቅ ሊግ በዚያ ስታዲየም ማካሄድ ስታዲየሙን “ባጣ ቆየኝ” እንጅ በቋሚነት ለአገር የሚጠቅም ሀብት አላስመሰለውም። ፌዴሬሽኑም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲካሄዱ መወሰኑ ክለቦች ከሜዳው አመቺ አለመሆን የተነሳ ለሚደርስባቸው የተጫዋቾች ጉዳት መልስ መስጠት ይችላል ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚችል አይመስለኝም። 

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ሆነ በስፖርቱ ላይ የሚመለከታቸው ማንኛውም አካላት ትልቅ የአገር ሃብት የሆነውን አበበ ቢቂላ ስታዲየምን ለችግር ጊዜ መፍትሄ አድርጎ ከማየት ይልቅ በዘላቂነት ለመጠቀም እንዲቻል ለስታዲየሙ አስፈላጊውን እድሳትና እንክብካቤ ቢደረግለት መልካም ነው እንላለን። 
 
ዘገባ፦ ይርጋ አበበ
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mesfin [1068 days ago.]
 Good point. It looks like this stadium has no owner and is deteriorating with time. The plastic seats are worn out and tear your cloths. The environment is dirty and unhygenic and no one is ceaning this place. The toilet looks awful. The federation shoul allocate at least three buses to take the spectators in three different direction after the games because it is very difficult to get transport after the games unless ofcourse you own your own car.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!