ዛሬና ነገ በሚደረጉት የ12ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ተቀራራቢ ነጥብ ባላቸው ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ፉክክር ይጠበቃል።
ጥር 10, 2007

አዲስ አበባ- 12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ዛሬ /ቅዳሜ/ ና ነገ /ዕሁድ/ ይቀጥላል።በዚህ መሰረት ክልል ላይ ስድስት ጨዋታዎች ሲደረጉ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

አዲስ አበባ ላይ ዕሁድ ሊካሄዱ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩት ደደቢት ከአርባምንጭና መከላከያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕሁድ የከተራ በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለጨዋታ ስለማይመች በሚል ዛሬ ቅዳሜ /እንድካሄዱ አዘጋጁ አካል ወስኗል።

ነገ ዕሁድ ደግሞ ክልል ላይ ሀዋሳ ከነማ ከኤሌክትሪክ፣ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከዳሸን ቢራ፣ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና እንድሁም ቦዴቲ ላይ ወላይታ ዲቻ ከሙገር ሲሚንቶ ይጫወታሉ።

ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች የደረጃ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል ይጠበቃል።ምክንያቱም ከመሪው ሲዳማ ቡና ሰባተኛ ደረጃ ላይ እስከተቀመጠው አዳማ ከነማ ያሉት ክለቦች ነጥባቸው ተቀራራቢ በመሆኑ ነው ሲዳማ ቡና 23 ነጥብ ሲኖርው አዳማ ከነማ 15 ነጥብ አለው ።በዚህም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት፣ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና፣አራተኛ ደረጃ ላይ ያለው ወላይታ ዲቻ፣አምስተኛ ደረጃን የያዘው አርባ ምንጭ፣ስድስተኛው መከላከያና ሰባተኛ ላይ ያለው አዳማ ከነማ እስከ ሁለተኛ ያለውን ደረጃ ማግኘት የሚችሉበት ዕድል ይኖራል።

ወልዲያ ላይ ወልዲያ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ሆኗል።ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመሪዎቹ ተርታ ሲቀመጥ አዲሱ የፕሪሚየር ሊጉ ማህበርተኛ ወልዲያ ከተማ ደግሞ አምስት ነጥቦችን ብቻ ይዞ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል።አሰልጣኙን ያሰናበተው ብቸኛው የክልል ሻምፒዮን ሀዋሳ ከነማ ደግሞ አሁንም ወልዲያ ከተማን ብቻ በልጦ ግርጌ ላይ ነው።

መብራት ሃይል ከሦስት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ አሸናፊነት ይመጣ ይሆን? ወልዲያ ከተማስ በሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስን ይፈትን ይሆን? የቡና ደርቢ በይርጋለምስ ማን የበላይ ይሆናል?የሚሉትን 12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚመልሳቸው ይሆናል።

የደረጃ ሰንጠረዡን ሲዳማ ቡና በ23፣ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና በ18 ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው ሲመሩት ሀዋሳ ከነማና ወልዲያ ከተማ በ7 እና በ5 ነጥቦች የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች ይዘዋል።የኢትዮጵያ ቡናው ቢኒያም አሰፋ በ8 እንዲሁም የደደቢቱ ሳሙኤል ሳኖሚ በ6 ግቦች ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመሩት ይገኛሉ።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!