ጠንካራዎቹ የደቡብ ክልል ክለቦች
ጥር 14, 2007

ክፍል አንድ 

ባለፈው ሳምንት የደቡብ ኢትዮጵያ ክለቦችን ጥንካሬ በተመለከተ ቀጣይ ጽሁፍ ይዘን እንደምንቀርብ ቃል ገብተን ነበር። በገባነው ቃል መሰረትም ዛሬ የመጀመሪያውን ክፍል ይዘን ቀርበናል።

 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚወዳደሩ 14 ክለቦች መካከል የደቡብ ክልል አራት ክለቦችን በማሳተፍ ከክልሎች ቀዳሚው ነው። ክልሉ ከሚወከልባቸው አራት ክለቦች መካከል ሶስቱ ከመሪዎቹ መካከል የሚመደቡ ናቸው። ሃዋሳ ከነማም ቢሆን ለጊዜው በደረጃው ግርጌ አካባቢ መሰንበቻውን ያደረገ ቢሆንም ካለው የቡድን ስብስብና የቆየ ታሪክ በመነሳት በቅርቡ ወደ መሪዎቹ የመመለስ እድል እንዳለው በርካቶች ግምታቸውን ይሰጣሉ። የክልሉ ክለቦች ከሰበሰቡት ነጥብ በተጨማሪ በፕሪሚየር ሊጉ ትልቅ ልምድና ውጤት ያላቸውን ለቦች ሳይቀር ማሸነፍ ችለዋል። ለአብነት ያህል የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና መከላከያን፣ ደደቢትንና ኢትዮጵያ ቡናን ሲያሸንፍ አርባ ምንጭ ከነማ በበኩሉ በሜዳው ቅዱስ ጊዮርጊስንና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፎ ከሜዳው ውጭ ደግሞ ከደደቢትና መከላከያ ጋር ነጥብ ተጋርቶ ተመልሷል። ወላይታ ድቻም ተመሳሳይ ገድል አለው።  

የክለቦቹ ጥንካሬ ምንጭ ምንድን ነው?

ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ መስጠት ባይቻልም በርካቶችን የሚያስማሙ ነጥቦችን ብቻ እናንሳ። የመጀመሪያው ነጥብ የክልሉ ክለቦች የተዋቀሩት ከፍተኛ የአካል ጥንካሬ ባላቸው ተጫዋቾች መሆናቸው ነው። ለዚህ ደግሞ ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበው በአካባቢው ያለው የአመጋገብ ባህል ከሌሎች አካባቢዎች የተለየ ነው። ይህ በመሆኑ ደግሞ ክለቦቹን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ለመጫወት ሙሉ አቅም ባላቸው ተጫዋቾች የተገነቡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
Wolayta Dicha Supporters Out Side Addis Ababa Stadium

ሌላው ለክለቦቹ ጥንካሬ ምክንያት ተደርጎ የሚነሳው የተጫወዋቾች የመጫወት ፍላጎት ነው። በዚህ በኩል ተጠቃሽ የሚሆነው የጎረቤታማቾቹ የወላይታ ድቻና አርባ ምንጭ ክለብ ተጫዋቾች ናቸው። የተጠቀሱት ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ያሰባሰቧቸው ከፍተኛ ገገንዘብ ለፊርማ በመክፈል ሳይሆን ከአካባቢው የሚገኙ የኳስ ክህሎት ያላቸውን ወጣቶችን በማሳደግ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ቢራና ደደቢት እያንዳንዳቸው በየዓመቱ ለተጫዋች ዝውውር የሚያወጡት ገንዘብ ሶስቱ የደቡብ ክልል ክለቦች ማለትም ሲዳማ ቡና፣ አርባ ምንጭ ከነማና ወላይታ ድቻ በአንድ ላይ አያወጡትም። በፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ጎል አግቢዎች ደረጃ ከሚመሩት አምስት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የወላይታ ድቻው ባዬ ገዛኸኝ ነው። ወላይታ ድቻ ይህንን አጥቂ ለመግዛት ሚሊዮን ብሮችን በደላላ ተበልቶ ልጁን አላስፈረመም ነገር ግን በብሔራዊ ሊጉ ከሚወዳደረው አላባ ከነማ በመናኛ ሳንቲም ነው ያስፈረመው። ባዬ ግን ረብጣ ብሮችን ለፊርማ ተከፍሎባቸው ምንም ጎል ማስቆጠር ካልቻሉት የኢትዮጵያ ቡና አጥቂዎች የተሻለ ተጫዋች ሆኗል። 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክለቦችን ጠንካራ እንዲሆኑ ካስቻሏቸው ምክንያቶች አንዱ ደግሞ በሜዳቸው ሲጫወቱ ከከተማው ነዋሪ የሚደረግላቸው ድጋፍ ነው። በዚህ በኩል አርባ ምንጭ ከነማና ወላይታ ድቻ ተጠቃሽ ናቸው። በተለይ አርባ ምንጭ ከነማ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በተደጋጋሚ ሲሸነፍ አይታይም። ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ካደገበት ዓመት አንስቶ አንድ ቀን ብቻ ያሸነፈውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም እንኳ ማሸነፍ የቻለው በሜዳው ነው። ከደጋፊዎች ከሚደረግላቸው ድጋፍ በተጨማሪ ደግሞ ክለቦቹ የሚገኙበት አካባቢ የአየር ንብረትም አስተዋጽኦ ሳያደርግላቸው እንዳልቀረ የሚናገሩ አስተያየት ሰጭዎችም አሉ። ለዚህ ሃሳባቸው ማስረገጫ የሚያቀርቡት ነጥብ ደግሞ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚደረጉ ሁሉም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ የሚካሄዱ በመሆናቸውና በዚያ ሰዓት ደግሞ የጸሃይዋ ግለት ጠንካራ በመሆኑ ባለሜዳዎቹ በለመዱት አየር ሳይቸገሩ ሲጫወቱ ለእንግዳ ክለቦች ግን አየሩ ፈታኝ ይሆናል። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
FootieFan [1126 days ago.]
 Right on all points. What the national team always needed: players strong physically and that can last 90-minutes if not longer. No wonder the current national team squad has got quite lot of players from the south.

yishak tomaS [1125 days ago.]
 Sil AMC. FC degaf bengr tirunew

Asefa Ayele [1125 days ago.]
 እዉነት ነዉ !!!!የተጠቀሱ ምክንያቶች ምንም የተጋነኑ አይደሉም ፡፡ ምናልባት ተራ ቁ.1 ላይ ያለዉን አልስማማም አንደኛ የኢ/ት ህዝብ የምግብ ባህላችን ተመሳሳይ ነዉ ሁለተኛ የተጨዋቾች ስብጥር የአንድ መንደር ወይም ወረዳ ስብስብ አይደሉም. ሌላዉግን እንደክልል የአዋሳ ከነማን መታደግ አለብን.ክልሉን የወከለ የመጀመሪያዉ ክለብ ነበር አሁን በዉጤት ወደታች የመሄዱ ምስጥር ምን እንደሆነ ማኔጅመንቱ በጥልቀት ማየት አለበት ከክልሉ ስፖርት ፌ/ሽንም ጋር ቢወያይ

Asefa Ayele [1125 days ago.]
 የሲዳማ ቡና ደጋፊ የክልሉን ስምና የክለቡን የፊታዉራሪነት ሞገሱን እያበላሸ ስለሆነ ይታረም፡፡ ክለቡ ጨዋ የሲዳማ ስምን ይዞ በአንዳንድ ግብረ-ገብ በጎደለዉ ተራ ደጋፊ ነኝ በሚለዉ ግለሰብ በሜዳ ዉስጥ በሚያሳየዉ ብልግናና ድርጊት መሰደብ የለበትም ፡፡ይህ የኳስም የክለብም ፍቅር አይደለም፡፡ በይ/ዓለም ሜዳ በሚደረገዉ ጨዋታ ሁልዜ ግጭት አይጠፋም፡፡ስለዚህ ቢታረም አሰፋ አየለ ከአ/አ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!