አዲሱ የተጫዋቾች ዝውውር መመሪያ ማኑዋል ማንን ተጠቃሚ ያደርጋል?
ጥር 16, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ የተጫዋቾችን ዝውውር የሚመለከት ማኑዋል አዘጋጅቶ ለውይይት ማቅረቡ ይታወሳል። ፌዴሬሽኑ ያዘጋጀው ማኑዋል እስካሁን ሲሰራበት የቆየው የተጫዋቾች ዝውውር አካሄድ ለአገሪቱ እግር ኳስም ሆነ የእግር ኳሱን እደገት ለሚሹ አካላት በሙሉ ጠቃሚ ስላልሆነ መቀየር አለበት ብሎ ተነስቷል። በፌዴሬሸኑ የተዘጋጀው የተጫዋቾች ዝውውር ማኑዋል ቀደም ሲል ለተጫዋቾች ይከፈል የነበረውን የፊርማ ክፍያ የሚያስቀር ሲሆን ክለቦች ተጫዋቾችን የሚያዘዋውሩት ለተጫዋቹ የፊርማ ክፍያ በመክፈል ሳይሆን ለነበረበት ክለብ የዝውውር ክፍያ በመክፈልና ለተጫዋቹም ደመወዝ በመክፈል ይሆናል። 

ለውይይት የቀረበው አዲስ የተጫዋቾች የዝውውር ማኑዋል ተጠቃሚ የሚያደርገው የትኛውን ወገን ነው? ለሚለው ጥያቄ ፌዴሬሽኑ “ክለቦች በርካታ ገንዘብ አውጥተው ተጫዋቾችን አሳድገው ከዝውውር ምንም ሳይጠቀሙ ይሸጣሉ፣ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣባቸው ተጫዋቾችም ለአዲሱ ክለባቸው የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ሳይሰጡ የውላቸውን ዘመን ያጠናቅቃሉ፣ እግር ኳስ አንድ የሥራ ዘርፍ ቢሆንም መንግሥት ከዚህ ዘርፍ ማግኘት የሚጠበቅበትን የገቢ ግብር ማግኘት አልቻለም። ስለዚህ አዲሱ መመሪያ ተጠቃሚ የሚያደርገው እነዚህን አካላት በሙሉ ነው” ሲል ይመልሳል። 

አንዳንድ ተጫዋቾች ደግሞ አዲሱ መመሪያ ማኑዋል “ክለቦችን እንጅ ተጫዋቾችን ተጠቃሚ አያደርግም” ሲሉ ማግረምረም ጀምረዋል። “አንድ ተጫዋች በጉዳት አቋሙ ቢወርድ ክለቡ ተጫዋቹን እንደምናምንቴ አውጥቶ ሊጥለው ስለሚችል ይህ ማኑዋል የተጫዋቾችን ተጠቃሚነት አያረጋግጥም” ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል። የክለብ አመራሮች በበኩላቸው አዲሱ የተጫዋቾች የዝውውር ማኑዋል መጽደቁን በጉጉት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። ምክንያታቸውን ሲያብራሩ “ለክለቦች ህልውና እና ለእግር ኳሱ እድገት ትክክለኛው አካሄድ ይህ ነው። ከእኛ ቀድመው እግር ኳሳቸውን ያሳደጉ አገሮች የሚጠቀሙበት መመሪያ ስለሆነ በእኛ አገር መተግበሩም አግባብ ነው” ሲሉ የአውሮፓንና የሌሎች አፍሪካ አገሮችን ልምድ ይጠቅሳሉ። 

ደጋፊዎችና ጋዜጠኞችስ ስለ አዲሱ ማኑዋል ምን ይላሉ? አንባቢያን ያላችሁን አስተያየት ከዚህ በታች ባለው የአስተያየት መስጫ ቦታ ላይ ብታስቀምጡልን እንወያይበታለን። 

መልካም ጊዜ ለእግር ኳሳችን !!! 
ይርጋ አበበ 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
agere wubshet [1124 days ago.]
 በጣም ደስ የሚል ደንብ ነው።ለብዙ ግዜ ክለቦቻችን ተጎድተው ነበረ፤ ይህ ለውጥ ቢዘገይም ጥሩ ጅምር ነው በርቱ

Motuma [1123 days ago.]
 ሳይሠራ ወይም ሳይጫወት ሊበላ የሚፈልግ ተጫወች ላይቀበለዉ ይችላል፤ለኢትዩጵያ እግር ኳስ እድገት የሚያስብ ከሆነ ግን በደስታ ነዉ የሚቀበለዉ።

dcf [1116 days ago.]
 rfrefgertrggt

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!