ሳላዲን ባርጌቾ የፕሪሚየር ሊጉን የመጀመሪያው ዙር ማራኪ ግብ አስቆጠረ
ጥር 18, 2007

በ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ተካሂደዋል። ትናን በአዲስ አበባ ከተካህዱ ሁለት ጨዋታዎች መካከል ያለፈው ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጥሎ ማለፉ አሸናፊ ደደቢት ጋር ያደረጉት ጨዋታ ይገኝበታል። በርካታ ተጨዋቾቹን በጉዳትና በቅጣት ለትናንቱ ጨዋታ ማግኘት ያልቻለው ደደቢት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በቀላሉ እጁን እንዲሰጥ ተገዷል። ፈረሰኞቹ በሰማያዊዮቹ ላይ ከፍተኛ የበላይነት ወስደው ነው ያሸነፉት። በሁለቱም ጨዋታ ክፍለ ጊዜ የበላይነቱን እንደመውሰዳቸው ሁለት ለባዶ በሆነ ውጤት ብቻ ማሸነፋቸው የሚያንስባቸው እንጅ የሚበዛባቸው አይደለም። ለፈረሰኞቹ ግቦቹን ሳላዲን ባርጌቾና አሉላ ግርማ ያስቆጠሩ ሲሆን በተለይ ሳላዲን ባርጌቾ በመቀስ ምት ያስቆጠራት ድንቅ ጎል  የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች በብዛት የሚከታተሉ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች እንደሰጡት  አስተያየት  ከሆነ ጎሏ  የፕሪሚየር ሊጉ  የመጀመሪያው ዙር ማራኪ ግብ እንደሆነች ተስማምተውበታል። 
 
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ12 ጨዋታ 24 ነጥብና አስር ንጹህ የጎል ክፍያ በመያዝ ከመሪው ሲዳማ ቡና በሶስት ነጥብ ብቻ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀራቸው ሲሆን የፊታችን አሁድ ወደ ቦዲቲ ተጉዘው ከወላይታ ድቻ ጋር ይጨዋወታሉ። በዚያ ጨዋታ ድል የሚቀናቸው ከሆነ የመጀመሪያውን ዙር የፕሪሚየር ሊግ ሰንጠረዥ በመሪነት በመጨረስ ያጠናቅቃሉ። 

በእለቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት ጨዋታ ቀደም ብሎ ኤልክትሪክ ክለብና ወላይታ ድቻ ያደረጉት ጨዋታ አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተናቋል። ኤልክትሪክ ከተከታታይ አራት ጨዋታ ሽንፈት በኋላ አንድ ነጥብ ያገኘበትን ጨዋታ አስመዝግቧል። ክልል ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ ሃዋሳ ከነማን ሁለት ለአንድ፣ አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ መከላከያን አንድ ለባዶ ሲያሸንፉ አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከነማና አዳማ ከነማ ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል።

ፕሪሚየር ሊጉን ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ ሲመራ ፈረሰኞቹ በሶስት ነጥብ ብቻ ዝቅ በለው ይከተላሉ። ኢትዮጵያ ቡና በ21 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዜና ዘገባ፦ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
sefaden [1050 days ago.]
 enamesagenalen mareja selasetahun bazew katelu yamral

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!