በአምላክ ተሰማ በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለ ብቸኛዳኛ
ጥር 20, 2007

ገና ከጅምሩ ጀምሮ ውስብስብ አጥሮች የከበቡት 30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ታናሿ አገር ኢኳቶሪያል ጊኒ የካፍን ጭንቀት ያስተነፈሰች አገር ሆና ቀርባለች። ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሌላት ምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር የሰሜን አፍሩካዊቷን ሞሮኮን እምቢተኛነት በይሁንታ በመመለስ ካፍን እፎይ ያሰኘች ቢሆንም በውድድሩ ተካፋይ የሆኑ 15 አገሮችን ግን በምቾት ልታስተናግድ አልቻለችም። በዝግጅት ማነስ እየተብጠለጠለ ባለው በዚሁ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ምስራቅ አፍሪካን የወከለ አገር አልተገኘም።
Beamlak Tessema

ሶስቱ የውድድሩ መስራች አገሮች ማለትም ግብጽ፣ኢትዮጵያና ሱዳን ባልተካፈሉበት በኢኳቶሪያል ጊኒው ውድድር ኢትዮጵያ በእግር ኳስ ቡድኗ ባትወከልም በአንድ ዳኛ መወከሏ ይታወሳል። በዚህ ውድድር ምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር ወክለው አገራቸውን ማስጠራት የቻሉት ደግሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ናቸው። ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በምድብ ሶስት ምዕራብ አፍሪካውያኑ ካሜሩንና ጊኒ ያካሄዱትን ጨዋታ በብቃት መርተዋል። ሁለቱ አገሮች አንድ ለአንድ በተለያዩበት ጨዋታ ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ጨዋታውን በብቃት መርተው ያጠናቀቁ ቢሆንም ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሽርፍራፊ ደቂቃዎች ውስጥ ጊኒዎች ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት መከልከላቸው ለትችት ዳርጓቸዋል ሲሉ ጨዋታውን የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን አስተያየታቸውን ለኢትዮፉትቦል ዶት ኮም ሰጥተዋል።       ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!