የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተዘጋጀ
ጥር 26, 2007

1ኛው የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከመጋቢት 5 እስከ 9, 2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚያካሂድ በጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዘጋጅ ኮሚቴው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
Sport Exhibition 2007

የኤግዚቢሽን እና ባዛር ስራ አስኪያጅ አቶ ብዙአየሁ ወንድሙ እንደገለፁት የኤግዚቢሽኑ እና ባዛሩ ዓላማ በሀገራችን በስፖርቱ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች፣ የስፖርት ማህበራት፣ ፌዴሬሽኖችና የስፖርቱ አጋር አካላት ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ሰፊ እድል በመፍጠር ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ ስፖርቱንና የስፖርት ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት መሆኑን በመግለፅ ዓላማውና ግቦቹን እንደሚከተለው አብራርተዋል፡፡

- የስፖርት ፌዴሬሽኖች፣ ቢሮዎችና ማህበራት ስፖርቱን የሚያስተዋውቁበትና የሚያስፋፉበትን እድል መፍጠር፤

-የተለያዩ የስፖርት ክለቦች አዳዲስ ደጋፊዎች የሚያገኙበት እንዲሁም ማልያዎችንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ በማቅረብ የገቢ ምንጭ መሆን፤

-የስፖርት ቤተሰቡ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ ማድረግ፤

-በስፖርት ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁና የገበያም እድል እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም የስፖርት ኢንቨስትመንት ላይ ግንዛቤ መፍጠር፤

-በስፖርቱ ዘርፍ ታዋቂነትን ያተረፉ የሀገራችን ታላላቅ ስፖርተኞች ከህብረተሰቡ ጋር የሚገናኙበትንና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት መድረክ ይሆናል፡፡

-በስፖርቱ ዘርፍ የተጀመሩትን የልማት ጉዞ ለህብረተሰቡ ማስተዋወቅና ህብረተሰቡ ቀጣይ የስፖርቱ የልማት እንቅስቃሴዎችን እንዲደግፍ ማድረግ እንደሆነ በሰፊው አብራርተዋል፡፡

በዚህ የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ ለመካፈል ከእግር ኳስ ክለቦች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ፣ ደደቢት እግር ኳስ ክለብ እና የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን እና ሌሎችም የተመዘገቡ ሲሆን ከአትሌቲክስ የተለያዩ ማህበራት እና ፌዴሬሽኖች እንደተመዘገቡ በመግለፅ በቀጣይ መመዝገብ ለሚፈልጉት የስፖርት ማህበራት እና ክለቦች የስፖርት ትጥቅ አምራቾች እና ሻጮች ከስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው ይሓ ሲቲ ሴንተር  ህንፃ 9ኛ ፎቅ መመዝገብ ይችላሉ ወይም በ0911 12 65 60 ደውለው መጠየቅ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!