የዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር፦ የተተኪዎች መፍለቂያ ምቹ መድረክ
ጥር 26, 2007

             
ክፍል አንድ

የኢትዮጵያ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ ይገኛል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም በውድድሩ እየተካፈሉ ከሚገኙ ተማሪዎችና አሰልጣኞች ጋር ተገናኝቶ አስተያየታቸውን ተቀብሎ ነበር። በተለይ የእግር ኳስ ተወዳዳሪዎችና አሰልጣኞች መድረኩን ትልልቅ ክለቦችና የወጣት ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ተተኪዎችን ለማግኘት ቢጠቀሙበት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል። ዝግጅት ክፍላችንም ከዛሬ ለተከታታይ ቀናት አስተያየቶቹን ይዞ ይቀርባል።

የመጀመሪያውን ክፍል እነሆ።

ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየታቸውን ከሰጡ ባለሙያዎችና ተጫዋቾች መካከል ዲላ ዩኒቨርስቲን እያሰለጠነ የሚገኘው ማቲዎስ ኦሲሶ አንዱ ነው። አሰልጣኙ ቀደም ባሉት ዓመታት ለወላይታ ቱሳ እና ለሌሎች ክለቦች በመጫወት በእግር ኳስ ላይ የካበተ ልምድ አለው። በእግር ስብራት የተነሳ ከእግር ኳስ በጊዜ ቢገለልም ወደ ትምህርቱ በመዞር ሁለተኛ ዲግሪውን በስፖርት ሳይንስ ሰርቶ ልምዱንና በትምህርት ያገኘውን እውቀቱን ለወጣቶች እያካፈለ ይገኛል። ስለ ውድድሩና ትልልቅ የአገሪቱ ክለቦች ሲናገር “የዩኒቨርስቲዎች ውድድር አላማ አድርጎ የተነሳው ተተኪዎችን ለብሔራዊ ቡድንና ለክለቦች ማብቃት እና በዩኒቨርስቲዎች አካባቢ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባት ነው። በዚህ በኩል ካየነው ይህ ውድድር ወጣቶች ችሎታቸውን አውጥተው ለማሳየት ትልቅ መድረክ ሆኗቸዋል። ነገር ግን የታላላቅ ክለቦች ወኪሎችና መልማዮች ውድድሩን ትኩረት ሰጥተው ሲመለከቱት አይታይም” ይላል።

አሰልጣኝ ማቲያስ አክሎም
“ስፖርት በዚህ ዘመን ሳይንስ ነው በተለይ እግር ኳስ። ክለቦች ደግሞ በትምህርታቸው የገፉ ወጣት ተጫዋቾችን ቢመለምሉ ተጠቃሚ የሚሆኑን እነሱ ናቸው ምክንያቱም እነዚ ልጆች እግር ኳሱን በሚገባ ስለሚያውቁት እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው። እኔ በእነዚህ ጥቂት ቀናት እንዳየሁት እንኳ ከእኔ ቡድንም ሆነ ከሌሎች ቡድኖች በርካታ ክህሎት ያላቸውን ልጆች ማየት ችያለሁ” ብሎ የተመለከታቸውን ተጫዋቾች ስም ይናገራል። 

ሌላው ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም አስተያየቱን የሰጠው ለኮተቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የሚጫወተው
ዮሴፍ ደቦ
ነው።

ዮሴፍ ደቦ በኮተቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ተማሪ ሲሆን ትናንት ኮተቤ ዩኒቨርስቲና ዲላ ዩኒቨርስቲ ተጫውተው ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ተጋጣሚውን ሶስት  ለሁለት ሲያሸንፍ ሁለቱን የኮተቤ ጎሎች ያስቆጠረ ተጫዋች ነው። ተጫዋቹ የእግር ኳስ ክህሎቱና ለጎል ያለው እይታ በጣም የሚገርም ነው። ከተክለሰውነቱ ጀምሮ ፍጥነቱና የኳስ አገፋፉ ለረጅም ጊዜ ተጫውቶ ያለፈ እንጅ ገና ወጣት አይመስልም። ያለው ልዩ ችሎታም ቡድኑ አሸንፎ እንዲወጣ ወሳኝነታቸው የጎላ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮለታል። ውድድሩን በተመለከተ ላቀረብንለት ጥያቄ  “ውድደሩ በጣም አሪፍ ነው በተለይ ለእኛ ለወጣቶች። ከዚህ በፊትም በመድረኩ ተሳትፌ ስለማውቅ የውድደሩን አስፈላጊነትና ጠቃሚነት እረዳዋለሁ።” ሲል አስተያየቱን ይሰጥና አያይዞም “እኔ ያደኩት ፕሮጄክት ተጫውቼ ነው። እኔ ብቻ ሳልሆን ከእኛ ቡድን እንኳ ብናይ ግብ ጠባቂውን ጨምሮ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ልጆች በፕሮጄክት አልፈው የመጡ ናቸው። ክለቦች ደግሞ ውድድሩን በትኩረት ቢመለከቱት ተተኪዎችን ለማግኘት ምቹ አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋል” ይላል። ዮሴፍ አድናቆቱን የቸረው የኮተቤ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ግብ ጠባቂ በእለቱ በርካታ የጎል እድሎችን ያዳነ ሲሆን በተለይ በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ ዲላ ዩኒቨርስቲዎች ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት ጎል ከመሆን የታደገ ግብ ጠባቂ ነው። ግብ ጠባቂውን አግኝተን ማናገር ባለመቻላችን አስተያየቱን ማቅረብ አልቻልንም።

ዮሴፍ ደቦ ሲናገር ክለቦች ከክለብ ክለብ በሚዞሩ ተጫዋቾች ላይ ቡድኖቻቸውን ከሚገነቡ በዚህ መድረክ የሚጫወቱ ወጣቶችን መልምለው የሙከራ እድል ቢያቀርቡላቸው ለሁለቱም ወገን ጠቃሚ መሆኑን አበክሮ ይናገራል።

ይቀጥላል።

ሪፖርታዥ፦ ይርጋ አበበ
ኢትዮ ፉትቦል

ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
YOSEF DEBO [1109 days ago.]
 Ethiofootball thanks for all! special thanks to reporter YIRGA ABEBE because he is wonderful wish for Ethiopia football groth to all Ethiopian clubs and also for Ethiopia National team. GOD bless u reporter Yirga Abebe!

jon [1096 days ago.]
 in these way are its a big chance to all young players so jest stay on the way spatially the reporter are very good man b/c he doing to investigate young players whatever my fired josey debo kotba football player is he personal appearance is so nice and also know all reporters to search josi debo haw is he doing know generally tanxs to support he and also to the others spatial tanxs to reporter yerga abebe (legend of reporters )

yonatan bejiga [1093 days ago.]
 for all supporters to young players I went to sey tanxs spatial. tanxs to the reporter yerga. so know all. reporters to search young players and how his playing and also where is he. Yosi Debo generally I sey tanxs very match to support him@@

Yewlsew Girmachew [1093 days ago.]
 I would first like to thank the reporter who is encouragoing the next generation of Ethiopian football. But, however encouraging them is important, following their every next activities is needed. So keep on going doing so.

feyiso [1084 days ago.]
 first of all I would like to say tnx reporter abebe for your nice work on university student players .Suddenly i know the guy u make interview he is a well performed skill by foot ball these boy must be growth he may contribute some thing for our country .And also tnx for your biriliant work.

feyiso [1084 days ago.]
  i wana to remind u specialy on yoseph Debo

Elias [1084 days ago.]
 bemejemeriya reporter abeben mamesgen efelegalehu lewetatoche yaregut degaf teru nw endante degaf yemiyadergu sewch binoru bezu wetatochen maferat yechal neber lemesale yosef debo ene dembosco senemar awkewalehu betam gobez leje nw tekuret setachihu betayut elalehu tnx abebe

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!