አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው አዲስ አበባ ገቡ።
ጥር 27, 2007

ከኢትዮጵያ ፉትቦል ፌደሬሽን በተኘው መረጃ መሰረት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ  ከሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ክለብ ጋር የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው አዲስ አበባ ገብተዋል። ኤዴሬሽኑአያይዞም ቆይታቸውን በተመለከተ በመጪው ዓርብ ጥር 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታውቋል።
Webetu Abate

የኢትዮጵያ ፉትቦል ፌደሬሽን  የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጠኝ ማሪያኖ ባሬቶን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በሾመበት ወቅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በምክትል አሰልጠኝነት እንዲሰሩ መርጧቸው እንደነበር የሚታወስ ነው። ውበቱ አባተ በሀገር ወስጥ አሰልጥነዋቸው ከነበሩት ከዋና ዋና ክለቦች ከደደቢት እንዲሁም ከባንክ ቆይታቸው በበለጠ ስማቸው ኢትዮጵያ ቡናን  የ2003ት ዓ.ም የፕሪሚይ ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ  ከማድረጋቸው ጋር በብዛት ይነሳል።


ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!