ወልድያ ከነማ ከመውረድ ለመትረፍ ፊቱን በውጭ አገር ተጫዋቾች ላይ አድርጓል
ጥር 27, 2007

 በተያዘው የውድድር ዓመት ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው ወልድያ ከነማ በመጣበት እግሩ ወደ ብሔራዊ ሊግ ላለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተነገረ። ለክለቡ ቅርበት ያላቸው የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብርን ተከትሎ ወልድያ ከነማም ፊቱን በተጫዋቾች ዝውውርት ላይ አድርጓል። ለዚህም ከስድስት የማያንሱ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ክለቡን ለመቀላቀል ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሎ እየተነገረ ይገኛል።
Woldya Kenema

በፕሪሚየር ሊጉ 13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ወልድያ ከነማና ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወቱ ወልድያ አምስት ለሁለት በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት መሸነፉ ይታወሳል። ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን ለጋዜጠኞች የሰጡት የክለቡ አሰልጣኝ አቶ ሰብስቤ ይባስ “በሁለተኛው ዙር የተሻለ ቡድን ይዘን በመቅረብ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ይኖርብናል። ለዚህም በሁሉም ቦታ ክለባችንን ከውድቀት የሚታደጉ ተጫዋቾን ለመግዛት ወደ ገበያ እንገባለን” ብለው መናገራቸው የሚታወስ ነው።

ከክለቡ የሚወጡ ሌሎች መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ደግሞ ወልድያ ከነማ ከአምስት በላይ ተጫዋቾችን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በውሰት ለመውሰድ መስማማቱን ያመለክታሉ። የተጫዋቾቹን ማንነት ከመግለጽ የተቆጠቡት ምንጮቻችን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ወልድያ ከነማ የሚዘዋወሩት ተጫዋቾች ግን ክለቡን ከወራጅነት ለመታደግ የሚሆኑ እንደሚሆን ተናግረዋል። ከአምናው ሻምፒዮን ወደ ወልድያ ከነማ በውሰት ተዘዋውረው ይጫወታሉ ተብለው የሚገመቱ የፈረሰኞቹ ኮከቦች ማንነት የተገለጸ ባይሆንም አንዳንድ ምንጮች ግን አጥቂዎቹ ዳዋ ሁጤሳና ፍጹም ገብረማሪያም እንዲሁም አማካዮቹ ተስፋዬ አለባቸውና ምንያህል ተሾመ እና ተከላካዮቹ መሃሪ መና እና ሳላዲን ባርጌቾ ናቸው ሲሉ የሚናገሩ ምንጮች አሉ።

የሳላዲን ባርጌቾና ፍጹም ገብረማሪያም ከፈረሰኞቹ ለቀው ወደ ወልድያ መጓዛቸውን ለማመን አስቸጋሪ ቢሆንም አማካዩ ምንያህል ተሾመ ግን በቅርቡ ክለቡ በዲስፕሊን የቀጣው በመሆኑ ወደ ወልድያ የመሄዱ ጭምጭምታ ለእውነት የቀረበ ይመስላል። የተከላካይ አማካዩ ተስፋዬ አለባቸው በበኩሉ ተወልዶ ያደገበትን ከተማ ክለብ ከወራጅነት ለመታደግ ወደ ወልድያ ለመጓዝ ፍላጎት እንዳለው ለክለቡ አሳውቋል ተብሏል። ወልድያ ከነማ በአምስት ነጥብና በርካታ የጎል እዳ ተሸክሞ በፕሪሚየር ሊጉ ግርጌ ላይ ይገኛል።

በሌላ ዜና ደደቢት እግር ኳስ ክለብ አማካዩን ሽመክት ጉግሳን በዲስፕሊን ግድፈት ለረጅም ጊዜ መቅጣቱን ከክለቡ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። ሽመክት ለቅጣት የተዳረገበት የዲስፕሊን ጉድለትም ሆነ ክለቡ ለምን ያህል ጊዜ እንደቀጣው ለማወቅ ያደረግነው ጥረት የተሳካ ባለመሆኑ ዝርዝሩን ወደፊት ይዘን እንመለሳለን። ከሽመክት ቀደም ብሎ የቀድሞውን ግብ ጠባቂ ሲሳይ ባንጫንም ክለቡ በዲስፕሊን መቅጣቱ የሚታወስ ነው።

ዜና ዘገባ፦ ይርጋ አበበ
ኢትዮ ፉትቦል

ethioootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
yosi debo [1085 days ago.]
 it is very good the report on ur news page so plz continue this interesting news. special thanks to reporter Yirga Abebe i wish all the best for u and also GOD with u!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!