የባህርዳርና ድሬዳዋ ስታድየሞች በካፍCAF እውቅና እንዲያገኙ ጥያቄ ቀረበ።
ጥር 29, 2007

የባህርዳርና ድሬዳዋ ስታድየሞች ከአዲስ አበባው ስታዲየም በተጨማሪ አለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮችን ማድረግ የሚያስችላቸውን እውቅና ከካፍ እንዲያገኙ ጥያቄ ማቅረቡን የኢ.እግ.ኳስ.ፌ አስታወቀ።
BahirDar Stadium

ጥያቄውንም ተከትሎ በሚቀጥለው ሳምንት የካፍCAF ባለሞያዎች ስታዲየሞቹን ለመጎብኘትና ለመገምገም አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ብቸኛው  ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ውድድሮችን ለማስተናገድ በካፍCAF እውቅና ያለው የአዲስ አበባ እስታዲየም ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው  12ተኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዝግጅት እድሳት እየተደረገለት በመሆኑ በየካቲት ወር በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን  አህጉራዊ ጨዋታዎች ማስተናገድ አይችልም፡፡ በመሆኑም ፕሮግራም የታያዘላቸው የቅዱስ ጊዮርጊስና የደደቢት የእግር ኳስ ቡድኖች የአፍሪካ ሻምፒዮን የመልስ ጨዋታዎቻቸውን እንዲሁም ከ23ት አመት በታች የብሄራዊ እግር ኳስ ቡድኑን ጨዋታ የሚከናወኑባቸው ስታዲየሞች የካፍCAFን ውሳኔ የሚጠብቁ ይሆናል።

የኢ.እግ.ኳስ.ፌ ለካፍCAF ያቀረበው ጥያቄ ምንም እንኳን የዘገየ ቢሆንም  ጥያቄውን ማቅረቡ ተገቢና ወቅታዊ ነው። ጥያቄውን የካፍCAF ባለሞያዎች እንዲቀበሉት የሚያስችለውን በቂ ዝግጅት ፌዴረሽኑ እንደሚያደርግ  ይታመናል። ለወደፊቱም ቢሆን  ከካፍCAF የሚመጡትን ባለሞያዎች ግምገማ  ውጤት መሰረት በማድረግ  በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች  የተገነቡትንና እየተገነቡ ያሉትን ስታዲየሞች ደረጃStandard ለማሻሻል የበኩሉን ጥረት በማድረግ  እውቅና እንዲያገኙ ጥያቄውን እንደሚያቀርብ ይጠበቀላል።ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!