የካፍ ባለሙያዎች አዲስ አበባ ገቡ፤ጊዮርጊስ የሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም ሊያደርግ ይችላል።
የካቲት 03, 2007

ከ50ሺ በላይ ተመልካች እንዲይዝ ተደርጐ የተሰራው የባህር ዳር ስታዲየም እንደሁም የድሬዳዋ ስታዲየም የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንዲችሉ እውቅና እንዲያገኙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ CAF ጥያቄ ባቀረበው መሰረት  የካፍ ገምጋሚ ባለሞያዎቸ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተው ስራቸውን ለመጀመር ወደ ድሬዳዋ  ማቅናታቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
Bahirdar Stadium


 በኢትዮጵያ ብቸኛው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን ለማካሄድ በፊፋ FIFAና በካፍ  CAF እውቅና ያለው የአዲስ አበባ ስታዲየም  ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ምክንያት  ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት የሚያደርጉትን የአፍሪካ ሻምፒንስ ሊግ የመልስ ጨዋታዎችን ጨምሮ ከ23 አመት በታች ወጣት ብሄራዊ ቡድን የሚያደርገውን ኢንተርናሽናል ጨዋታ  ማስተናገድ እንደማይችል ፌዴሬሽኑ ማስታወቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ  ፌዴሬሽን መግለጫን ተከትሎ  የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በድረ-ገጹ  እንዳስነበበው    ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአልጄርያው ኤም ሲ ኤል ኡልማ ጋር የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም የሚያደርገውን የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ በባህር ዳር ስታዲየም ያደርጋል ሲል ዘግቧል።
St.George

 የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ለበርካታ አመታት በአፍሪካ መድረክ ያለውን ተሳትፎ በውጤት ለማጀብ ከፍተኛ ጥረትና ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ ነው። በመሆኑም ዘንድሮ ለሚሳተፍበት የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ከፍኛ ዝግጅት አድርጐ ከዚህ ቀደም የነበረውን ሪከርድ የተሻለ ደረጃን በማግኘት ደጋፊዎቹ ሲናፍቁት የኖሩትን የኢንተርናሽናል ውጤት ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመልስ ጨዋታውን በባህር ዳር ስታዲየም የሚያከናውን ከሆነ ለስታዲየሙ የመጀመሪያ የኢንተርናሽናል ጨዋታ የሚሆነው  ቅዱስ ጊዮርጊስ  ከአልጄርያው ኤም ሲ ኤል ኡልማ ጋር የሚያደርገው  ጨዋታ  የክልሉን በተለይ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ስፖርት አፍቃሪ  ህብረተሰብን ትኩረት ይስባል ተብሎ ይጠበቃል። የክልሉ ስፖርት ኮሚሽንም ህብረተስቡ ጨዋታውን በብዛት በስታዲም በመገኘት ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚጫወተው  ለቅዱስ ጊዮርጊስ ድጋፉን እንዲሰጥ የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ዳኛው [938 days ago.]
 ደስ ይላል ካፍም መልሱ እሺ ይሁን

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!