የዋሊያዎቹ ደረጃ መሻሻል የተገኘው ከውጤት ወይስ ከጊዜ ቆይታ?
ህዳር 07, 2007

የዛሬ ጽሁፌን የምጀምረው አንባቢያንን ለውይይት በመጋበዝ ይሆናል። ስለሆነም የተከበራችሁ የድረገጻችን አንባቢያን በዚህ መጣጥፍ ዙሪያ ያላችሁን አስተያየት እንደተለመደው በአስተያየት መስጫ ቦታ ወይም በኢሜይል አድራሻችን info@ethiofootball.com ወይም ለዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ በኢሜይል አድራሻው abebeyirga56@gmail.com ሃሳባችሁን ብትሉክልን ብትልኩልን  የምናስተናግድ ይሆናል።? 

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የበላይ ጠባቂ ፊፋ የጥር ወር የአገራትን የእግር ኳስ ደረጃ ትናንት ይፋ አድርጓል። በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ መሰረት በአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀድሞ ከነበረበት 109ኛ ደረጃ ሰባት ደረጃዎችን በማሻሻል 102ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ያመለክታል። ነገር ግን ፊፋ የአገራትን ደረጃ ሲያወጣ መስፈርቱ ምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ሲነሳ በወሩ አገሮች ያደረጉትን የነጥብና በፊፋ እውቅና ያላቸው የወዳጅነት ጨዋታዎችን ሲያደርጉ በሚመዘገብ ውጤት ተመርኩዞ ነው። 

Ethiopian National Team Bamako under Bareto

            ኢትዮጵያ በፊፋ የተሰጣት ደረጃ መመዘኛው ምንድን ነው?

ከላይ እንደገለጽነው የፊፋ የደረጃ መመዘኛ ነጥብ ውድድርን መሰረት ያደረገ ነው። በዚህ በኩል 30ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ አስተናግዳ አራተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው ኢኳቶሪያል ጊኒ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 79ኛ ደረጃን የያዘችው በአፍሪካ ዋንጫ አራተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ነው። የዓለምን እግር ኳስ ደረጃ የምትመራው የዓለም ዋንጫው አሸናፊ ጀርመንም ብትሆን በጥር ወር መጀመሪያ አካባቢ የፊፋን እውቅና ባገኘ የወዳጅነት ጨዋታ ባስመዘገበችው ውጤት ተመርኩዞ እንዲሁም ቀድሞ ከሰበሰበችው ነጥብ ጋር ተደምሮላት ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግን ለ30ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር በህዳር የመጀመሪያ ሳምንት ከተጫወተ በኋላ አንድም የነጥብም ሆነ የወዳጅነት ጨዋታ ሳያደርግ ሁለት ወር ሞልቶታል። ታዲያ የደረጃ ለውጡ ከየትና እንዴት  መጣ? 

ብሔራዊ ቡድኑ ደረጃውን እንዲያሻሽል ምን መደረግ አለበት?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካለው ደካማ ጎን አንዱና ዋናው ተብሎ የሚወሰደው የጌም ልምድ የሌለው መሆኑ ነው። በተለይ ወሳኝነት ላለው የነጥብ ጨዋታ እንዲጠቅመው ፊፋ በሚያዘጋጀው የኢንተርናሽናል ጨዋታ ብሬክ ላይ የተመዘገበ ውድድር አያካሂድም። ይህን ባለማድረጉ ወዲህ በአገሪቱ ውጤት ላይ ወዲህ ደግሞ በፊፋ ለሚሰጣት ደረጃ ዝቅተኛ መሆን የራሱን ተጽእኖ እያሳረፈ ይገኛል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ወደፊት ለእግር ኳሱ እድገት ይበጃል ተብሎ የሚታሰበውን የወዳጅነት ጨዋታ ከታላላቅ የእግር ኳስ አገሮች ጋር የሚያካሂድ ይመስለናል። 

የብሔራዊ ቡድናችን ደረጃ ዝቅተኛ መሆን በተጫዋቾቻችን ላይ ያሳረፈው አሉታዊ ተጽእኖ ታላላቆቹ የአውሮፓ ሊጎች የሚሳተፉ ክለቦች ተጫዋቾችን ማስፈረም ሲሹ የሚያደርጉት የመጀመሪያ መመዘኛ “ተጫዋቹ እየተጫወተበት ያለው ሊግ ደረጃው ምን ያህል ነው አገሪቱ ያላት የፊፋ ደረጃስ ምን ይመስላል?” የሚለውን ነው። በዚህ መሰረት ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ችሎታው የቱንም ያህል እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ቢሆንም ታላለቆቹ የአውሮፓ ክለቦች ግን እጃቸውን ወደ ኪሳቸው ሰድደው ተጫዋቹን ለማስፈረም አይሞክሩም። ምክንያቱም ያ ታዕምረኛ የተባለው ተጫዋች በሊጋቸው እንዲጫወት እምነት አይሰጡትም። 

በዚህ የተነሳም የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው ፍቅሩ ተፈራ የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ በሞግዚትነት ለሚያስተዳድረው የህንዱ አትሌቲኮ ካልካታ ክለብ ለመፈረም እንደ ታዳጊ ተጫዋች በሙከራ ታይቶ ነበር የፈረመው እንጅ በቀጥታ የዝውውር ጥያቄ አልቀረበለትም ነበር። ልክ እንደ ፍቅሩ ሁሉ ሌሎች የአገራችን ተጫዋቾችም ተመሳሳይ እድል ቢያገኙ የሚጠብቃቸው ከፍቅሩ የባሰ እንጅ የተሻለ ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው ምክንያቱም ፍቅሩ ቢያንስ ለደቡብ አፍሪካ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን ሌሎቹ ግን ከኢትዮጵያ ሪሚየር ሊግ የተጫወቱ በመሆናቸው ነው።  

 ይርጋ አበበ 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!