መስዑድ መሃመድና ኢትዮጵያ ቡና ይለያዩ ይሆን?
የካቲት 09, 2007

- “የመልቀቂያ ጥያቄውን በጽሁፍ ሳይሆን በቃል አቅርቤያለሁ   ቆይታዬ ወደፊት የሚታወቅ ነው።” መሰዑድ መሃመድ ከኢትዮ ፉትቦል ዶትኮም  በሰጠው የስልክ ቃለ ምልልስ 

ኢትዮጵያ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ባነሳበት 2003 ዓ.ም ከቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረውና በአሁኑ ወቅት የክለቡ ምክትል አምበል የሆነው መስዑድ መሃመድ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ሊለያይ መሆኑን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። ለጊዜው ማረፊያው ባይታወቅም አማካዩ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ኮንትራት አቋርጦ ለመልቀቅ ፍላጎት ማቅረቡ ተገልጿል። 
Mesu Mohamed

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአቋሙ ላይ መጠነኛ መዋዠቅ የታየበት አመለ ሸጋው የቀድሞ የመብራት ሀይልና የደደቢት አማካይ ውሉን ጨርሶ ከቡና የሚለይ ከሆነ የአማራ ክልሎቹን ዳሽን ቢራ እና ወልድያ ከነማን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ፊርማውን ለማግኘት ፍላጎት ማሳየታቸው ተገልጿል። 
Mesud Mohamed

መሰዑድ መሃመድ ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር ባደረገው የስልክ ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገረው የመልቀቂያ ጥያቄውን በጽሁፍ ሳይሆን በቃል ማቅረቡንና ቆይታውም ወደፊት የሚታወቅ ነው ሲል ተናግሯል። መስዑድ መሃመድ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው በ2003 ዓ.ም ሲሆን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ከቡና ጋር ለመቆየት ውሉን ያደሰው ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ ነበር።  

በተያያዘ የዝውውር ዜና ከክለቡ ጋር መስማማት ያልቻለው ተከላካዩ ቶክ ጀምስ በጥር ወር የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ቡናን ሊለቅ እንደሚችል ተነግሯል። ቶክ ጀምስ ከቡና የሚለቅ ከሆነ የቀድሞ አሰልጣኙ ጸጋዬ ኪዳነማሪያም ለሚያሰለጥነው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊፈርም እንደሚችል ግምቶች አሉ። 

ዘገባ፦ ይርጋ አበበ
ኢትዮ ፉትቦልethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!