ደደቢት የመጀመሪያ የቤት ስራውን በድል ሲወጣ ጊዮርጊስ ደግሞ በጠባብ ጎል ተሸነፈ
የካቲት 08, 2007

ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግና ጥሎ ማለፉ ውድድር አሸናፊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት አገራቸውን ወክለው በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተወዳደሩ ይገኛሉ። ክለቦቹ ሰሞኑን ወደ ሰሜን አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ተጉዘው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን አካሂደው ፈረሰኞቹ አንድ ለባዶ ተሸንፈው ሰማያዊዮቹ ደግሞ ሶስት ለሁለት አሸንፈው ተመልሰዋል። 
St.George players in Algeria

ወደ ሰሜን አፍሪካ ተጉዘው ከአልጄሪያው ኤም ሲ አል ኤሉማ ጋር የተጫወቱት ፈረሰኞቹ በጠባብ የጎል ልዩነት መሸነፋቸው በመልሱ ጨዋታ በሜዳቸው ውጤት የመቀየር እድል ስላላቸው ሽንፈቱ እንደ ውድቀት ሊቆጠር አይገባውም የሚሉ አስተያየቶች ለዝግጅት ክፍላችን የተሰጡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ የገጠመው ክለብ በአልጄሪያ ሊግ ያለው ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ ከመሸነፍ ይልቅ ቢያንስ አንድ ነጥብ እንኳ ይዞ መመለስ ነበረበት የሚሉ ሌሎች ወገኖችም አስተያየታቸውን ገልጸዋል። ፈረሰኞቹን ያሸነፈው የአልጄሪያው ክለብ በአገሩ ሊግ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፈረሰኞቹ በበኩላቸው የአገራቸውን ሊግ ከመሪው ሲዳማ ቡና በሶስት ነጥብ ዝቅ ብለው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። 

ያለፈው ዓመት የጥሎ ማለፉ አሸናፊዎች ሰማያዊዮቹ በበኩላቸው ወደ ምዕራብ አፍሪካ ተጉዘው ከሲሸልሱ ኮት ዲኦር ኤፍ ሲ ጋር ተጫውቶ ሶስት ለሁለት አሸንፎ ተመልሷል። ደደቢት ያሸነፈባቸውን ሶስት ወሳኝ ጎሎች አጥቂዎቹ ዳዊት ፈቃዱ ሁለት እና ሳሙኤል ሳኖሜ አንድ ጎል አስቆጥረዋል። ከቡድኑ ቋሚ ተሰላፊዎች መካከል አራቱ ምዕራብ አፍሪካውያን ተጫዋቾቹ ወደ ሲሸልስ እንዳይገቡ ቪዛ የተከለከለበት ደደቢት በጨዋታው በርካታ ተጠባባቂ ተጫዋቾቹን መጠቀሙን መረጃዎች አመልክተዋል። 

ፈረሰኞቹና ሰማያዊዮቹ የመልስ ጨዋታቸውን ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በባህር ዳሩ ሁለገብ ብሔራዊ ስታዲየም ያካሂዳሉ። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!