ድሬዳዋ የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታን ልታስተናግድ ነው።
የካቲት 13, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረሰን መረጃ መሰረት የምስራቅ ኢትዮጵያዋ ከተማ ድሬዳዋ ስታዲየም የኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ለሚያደርገው የማጣሪያ ጨዋታ ተመርጣለች። 12ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለማዘጋጀት የተመረጠችው ኢትዮጵያ ውድድሩ የሚካሄድበትን አንድ ለእናቱ የሆነውን አዲስ አበባ ስታዲየምን እድሳት እንዲደረግለት በመወሰኑ የእግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለአገር ውስጥ የእግር ኳስ ጨዋታዎች “ባጣ ቆየኝ” የሆነውን አበበ ቢቂላ ስታዲየምን በጊዜያዊነት እየተጠቀመ ቆይቷል። ነገር ግን ከአገር ውስጥ የሊግ ውድድር በተጨማሪ አህጉራዊ የክለቦችና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በመምጣቱ ፌዴሬሽኑ እነዚህን ሶስት ጨዋታዎች የሚያካሂድበት ስታዲየም ሲያስስ ቆይቶ ከካፍ አንድ የሜዳ ጥራት ባለሙያ አስመጥቶ ሁለት ስታዲየሞችን ውድድር እንዲያካሂዱ አስጸድቋል።
Diredawa Stadium

በኬኒያዊው የካፍ የሜዳ ጥራት ባለሙያ መመዘኛ መሰረት የካፍ እውቅና የሚሰጣቸው ውድድሮችን በኢትዮጵየya ለማካሄድ ብቁ ናቸው ተብለው የተመረጡት ሁለቱ ስታዲየች ግንባታው ያልተጠናቀቀው የባህር ዳሩ ብሔራዊ ስታዲየምና ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን ካካሄደ ዘመናት ያስቆጠረውና ተረስቶ የነበረው የድሬዳዋ ስታዲየም ናቸው። በዚሁ መሰረት በአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ለማለፍ የሱዳን አቻውን በድሬዳዋ ስታዲየም የሚያስተናግድ ይሆናል።

በፀሀይ መውጫዋ ከተማ የሚካሄደውን ጨዋታ ኬኒያውያን ዳኞች እንዲመሩት ከካፍ የተመደቡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሁለቱ ምስራቅ አፍሪካውያን አገሮች የሚያካሂዱትን ጨዋታ የምስራቅ አፍሪካዋ ኬኒያ ዳኞች በዳኝነት እንዲመሩት ሲደረግ የጨዋታው ኮሚሽነርም ከዚሁ ቀጠና አልወጡም ጂቡቲያዊ ናቸው።
ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!