ከፈረሰኞቹ ውድቀት ሰማያዊዮቹ ምን ይማራሉ?
የካቲት 23, 2007

በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና የአልጄሪያው አል ኤልማ 180 ደቂቃ ፍልሚያ አድርገው ሁለት እኩል ተለያዩ። ነገር ግን ከሜዳ ውጭ ባገባ የሚለው አሳዛኝ ህግ ፈረሰኞቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ኮርቻቸውን ስበው “መጭ” እንዳይሉ እንቅፋት ሆነባቸው። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ባህር ዳር ላይ ሲካሄድ ባለሜዳዎቹ ፈረሰኞቹ በተጋጣሚያቸው ላይ የጨዋታ የበላይነት ይዘው እንደነበረ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ውጤቱ የሚያሳየውም ይህንኑ ነው ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሽርፍራፊ ደቂቃዎች እስኪቀሩት ድረስ ሁለት ለባዶ ሲመሩ ነበር። 

ከቅዱስ ጊዮርጊስና ኤል አሉማ ጨዋታ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ደግሞ ደደቢትና የሲሸልሱ ኮትዲኦር በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ተገናኝተው ሰማያዊዮቹ ሁለት ለባዶ ማሸነፋቸው ይታወሳል። አሁን ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ውድድር የሚወክላት ብቸኛው ክለብ ደደቢት ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በጥቃቅን ስህተትና በተጋጣሚው ታክቲካል ብልጠት ከውድድር ውጭ ሆኗል። ነገር ግን ሰማያዊዮቹ ከፈረሰኞቹ ውድቀት ምን ይማራሉ የሚለው ትኩረት የሚሻው ጥያቄ ሊሆን የሚገባ ይመስለናል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም የኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ ቡድን በመድረኩ ምን ያህል ርቀት ሊጓዝ እንደሚችልና ጉዞውን በአጭሩ እንዳይቋጭ ለማድረግ ምን ማድረግ አለበት የሚለውን ነጥብ አንስተን ከአንባቢያን ጋር እንወያያለን። በዚህ ነጥብ ላይ አንባቢያን የተለመደ ገንቢና ጠቃሚ ነጥብ እንዲሰጡን በአክብሮት እንጋብዛል። 

የፈረሰኞቹ ውድቀትና የሰማያዊዮቹ ቀጣይ ተጋጣሚ

ደደቢት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያለው ደረጃ ከዋንጫው ፉክክር ውጭ መሆኑን በጊዜ አውቆ እንዲቀመጥ የሚያደርግ ነው። በእሱና በመሪዎቹ ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ከፍተኛ በመሆኑ ደደቢትን ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ እንዳይጫወት ያደርገዋል። በጥሎ ማለፉ ዋንጫም በጊዜ በመሸነፉ ብቸኛ የዋንጫ ተስፋው የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ብቻ ነው። ሰማያዊ ለባሾቹ ይህንን ዋንጫ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ በቀጣዩ ዓመት በአህጉራዊ ውድድር የመሳተፍ እድል አይኖራቸውም። ለዚህም ሙሉ ትኩረታቸውን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል ደግሞም ሊያደርጉ ይገባልም። 

ፈረሰኞቹ በዚህ ዓመት ከውድድሩ የወጡት ከሜዳ ውጭ በተቆጠረ ጎል ምክንያት ነው። ከሶስት ዓመት በፊትም በተመሳሳዩ በእለተ ፋሲካ ጨዋታ ከግብጹ ክለብ ጋር ባደረጉት ጨዋታ በሜዳቸው በአለቀ ሰዓት በተቆጠረ ጎል ከውድድር ውጭ መሆናቸው ይታወሳል። ደደቢትስ ከዚህ ምን ይማራል? 

የደደቢት ቀጣይ ተጋጣሚ የናይጄሪያው ወሪዎልቨር የተባለው ክለብ ነው። በዚህ ጽሁፍ ስለ ወሪዎልቨር መረጃ ለመስጠት ባንችልም ደዲቢት ከተጋጣሚው ጋር በደርሶመልስ ሲገናኝ ምን ሊያደርግ ይገባዋል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ተገቢ መስሎ ይታየናል። ካለፉት ስህተቶችና ከሌሎች ቡድኖች ስህተት ትምህርት መውሰድ ጠቃሚነቱ አያጠያይቅም። በመሆኑም ደደቢት ናይጄሪያ ላይም ሆነ አዲስ አበባ ላይ በሚኖረው ሁለት ወሳኝ ፍልሚያዎች ላይ ጥንቃቄ የተሞላበትና ፕሮፌሽናሊዝምን የተላበሰ ጨዋታ ያደርጋል ብለን እንጠብቃለን። በተለይ በዲስፒሊን በኩል ከባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ትምህርት ሊወስድ ይገባዋል እንላለን። የቡድን ጥልቀቱንና የተጫዋቾቹን ማች ፊትነስም በሚገባ መከታተል ይኖርበታል። ቀሪውን ለአንባቢያን ብንተወውና አስተያየታችሁን ብትሰጡን ወደድን። 

መልካም ጊዜ ለእግር ኳሳችን መልካም የውድድር ጊዜ ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ!!

ዘገባ፦ ይርጋ አበበ 
ኢትዮ ፉትቦልethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!