የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በ2006 ዓ.ም ባለ ድል ያደረጉትን የቡድን አባላት ሸለመ
መጋቢት 03, 2007

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቦርድ አመራሮች የ2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን እንዲያነሳ ያስቻሉትን የቡድኑን አጠቃላይ አባላት ዛሬ መሸለሙን አስታወቀ። በሽልማቱ  አሰልጣኞችን ጨምሮ ተጨዋቾች፣ ኳስ አቀባዮች፣ እንዲሁም ሹፌሮች የሽልማቱ ተቋዳሽ ሆነዋል። የሽልማቱ  ስነስረአት የተካሄደው በዛሬው እለት  በተጨዋቾች መኖርያ ሆስቴል ሲሆን ሽልማቱን ለማበርከት የክለቡ አመራሮች በስፍራው ተገኝተዋል።  በዚህ የሽልማት ስነ ስርአት ላይ ከ500‚000 ብር በላይ ወጪ የሆነ ሲሆን ከፍተኛው ተሸላሚ 40‚000 ብር ዝቅተኛው ደግሞ 15‚000 ብር ነው።
St.George

ሽልማቱ  የተከናወነው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያስቆጭ ሁኔታ ባህርዳር ላይ ከአፍሪካ ሻምፒዮንስ በተሰናበተበት ሰሞን መሆኑ የቡድኑን አባላት ሞራል ከመጠበቅ አንጻር ክተኛ ድርሻ ይኖረዋል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!