በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት ቅ.ጊዮርጊስ ሊጉን መምራት ጀመረ
መጋቢት 06, 2015

- ወደ ቦታችን ተመለስን ፈረሰኞቹ 
- ከክለባችን ደረጃ በታች የሆኑ ተጫዋቾች ውጤታችንን እያበላሹብን ነው ቡናማዎቹ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ከአርብ ጀምሮ በተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባና በክልል ስታዲየሞች ቀጥሎ ውሏል። ከሁለት ወራት ላላነሰ ጊዜ በእረፍት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ፕሪሚየር ሊጉ ሲጀመር የተገናኙት ኤሌክትሪክና መከላከያ ነበሩ። በውጤቱም መከላያ በሲሳይ ደምሴ ፍጹም ቅጣት ምት ጎል እና የኤሌክትሪኩ ተከላካይ በራሱ ላይ ባገባት ጎል ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ሁለተኛውን ዙር በድል ጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር የመጨረሻዎቹ አራት ሳምንታት ተከታታይ ሽንፈት ላስተናገደው ገብረመድህን ሀይሌ ቡድን ድሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አሰልጣኙ ተናግሯል። 

ፕሪሚየር ሊጉ ጎንደር ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ባለሜዳው ዳሽን ቢራ በእንግዳው ወላይታ ድቻ አንድ ለባዶ ተሸንፎ ደጋፊዎቹን አንገት አስደፍቷል። ወላይታ ድቻ ሙሉ ሶስት ነጥብ ያገኘባትን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው አጥቂው ባዬ ገዛኸኝ ሲሆን ጎሏ በዓመቱ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ድምር ስድስት አድርሳለታለች። 

ትናንት በተካሄዱ ሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ያለፈው ዓመት ሻምፒኖቹ አዳማ ከነማን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ከሲዳማ ቡና ላይ ተረክበዋል። ለፈረሰኞቹ ሁለቱን የማሸነፊያ ጎሎች ያስቆጠሩት አዲሱ ዩጋናዳዊ የክለቡ አጥቂ ብሪያን እና አማካዩ ምንተስኖት ኣዳነ ናቸው። ከድሉ በኋላ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ክለባችን ወደ ቦታው ተመለሰ ሲሉ አስተያታቸውን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ገልጸዋል። መሪነቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ የተነጠቀው ሲዳማ ቡና ወደ አሰላ ተጉዞ ከሙገር ሲሚንቶ ጋር ያለ ግብ አቻ ተላያይቶ ተመልሶአል። 

አርባምንጭ ላይ በተካሄደ የአርባምንጭ ከነማና ሃዋሳ ከነማ ጨዋታ እንግዳው ቡድን ሁለት ለባ አሸንፎ ተመልሶአል። በቅርቡ ለሃዋሳ ከነማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ የተሸመው ውበቱ አባተ በመጀመሪያ ጨዋታው ከሜዳው ውጭ ድል በማስመዝገቡ አጀማመሩን አሳምሯል።  

ትናንት በተካሄደ ሌላ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓመቱ ለሶስተና ጊዜ ኢትዮጵ ቡናን ያሸነፈበትን ውጤት አስመዝግቧል። ንግድ ባንክ አሸናፊ የሆነባትን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው የመስመር አማካዩ ሲሳይ ቶላ ነው። ከጨዋታው በኋላ አስተያታቸውን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ገለጹ የኢትጵያ ቡና ደጋፊዎች ለሽነፈቱ የክለባቸውን አሰልጣኘና ተጨዋቾች ተጤያቂ አድርገዋል። የክለባችንን ደረጃ የማይመጥኑ ናቸው ሲሉም አምርረው ተናግረዋል። 
ካሳ ሀይሉ ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
nesredin omer [992 days ago.]
 i like it very good .............

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!